ውክፔዲያ:ታሪካዊ ማስታወሻዎች/ኅዳር 8
Appearance
- ፲፭፻፶፩ ዓ.ም. - የእንግሊዟ ቀዳማዊት ንግሥት ማርያም ስትሞት እህቷ ቀዳማዊት ኤልሳቤጥ አልጋውን ወርሳ ዘውድ ጫነች።
- ፲፰፻፵፰ ዓ.ም. - ዴቪድ ሊቪንግስተን በዛሬዎቹ ዛምቢያና ዚምባብዌ ላይ የሚገኘውን ታላቅ ፏፏቴ በማየት የመጀመሪያው አውሮፓዊ ሆነ። ይሄንኑም ፏፏቴ ለንግሥቱ ክብር የቪክቶሪያ ፏፏቴ ብሎ ሰየመው።
- ፲፰፻፷፪ ዓ.ም. - የሜዲተራንያ ባሕርንና ቀይ ባሕርን ያገናኘው የሱዌዝ ቦይ በደመቀና በታላቅ ሥነ ስርዐት ተመረቀ።
- ፲፱፻፶፯ ዓ/ም - ፲፩ ነጥብ ፬ ‘ሜጋዋት’ የሚያመነጨው የጢስ እሳት መብራት ኃይል ማመንጫ በዚህ ዕለት ተመርቆ ሥራ ላይ ዋለ።
- ፲፱፻፷፩ ዓ/ም - የሶቪዬት ኅብረት፣ አሰብ ላይ በዓመት ፭፻ ሺ ቶን የድፍድፍ ነዳጅ ማጣሪያ ለመገንባት የሚያስችለውን ውል ከኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት መንግሥት ጋር ተፈራረመ።
- ፲፱፻፷፯ ዓ/ም - ሻለቃ መንግሥቱ ኃይለ ማርያም (በኋላ ኮሎኔል) የኢትዮጵያ ጊዜያዊ ወታደራዊ መንግሥት (ደርግ) አንደኛ ምክትል ሊቀ መንበር፤ ስማቸው ለመጀመሪያ ጊዜ ይፋ ተደረገ።
- ፲፱፻፺ ዓ.ም. - በግብጽ ስድስት አመጸኛ አክራሪዎች በሉክሶር ጥንታዊውን የ”ሀትሼፕሱት መቅደስ” ለመጎብኘት የመጡ ሠላሳ ስምንት የስዊስ፤ አሥር የጃፓን ፤ ስድስት የብሪታንያ እንዲሁም አራት የጀርመን ዜጎችን ረሽነው ገደሏቸው።
- ፲፱፻፺፮ ዓ.ም.- የአውስትሪያው ተወላጅና የፊልም ተዋናይ አርኖልድ ሽቫርትዘኔገር የካሊፎርኒያ ሠላሳ ስምንተኛው ገዥ በመሆን መሐላውን ሰጥቶ ስልጣኑን ተቀበለ።