ጌሾ
Appearance
?ጌሾ | ||||||||||||
---|---|---|---|---|---|---|---|---|---|---|---|---|
ሳይንሳዊ ደረጃ መስጫ | ||||||||||||
| ||||||||||||
''Rhamnus prinoides'' Eschsch. |
ጌሾ በአፍሪካ ብቻ የሚበቅል በተለይ በኢትዮጵያና በደቡብ አፍሪካ የሚገኝ ተክል ነው። በኢትዮጵያ ጠላና ለጠጅ ሲጠመቅ ጌሻ ይገባል። የሚበቅለውም ከባህር ወለል በላይ 1400-3200 ሜትር ላይ ነው።
- ቆረቆርና ሌሎች የፈንገስ በሽታወችን በደቀቀ ፍሬውና ቅጠሉ በመቀባት ለማዳን ይቻላል
- ህጻናት እንጥላቸው ከተቆረጠ በኋላ ህመማቸውን ለማስታገስ አፋቸው ውስጥ የጌሾ ቅጠል ይደረጋል
- ቂጥኝ በሽታን ለመከላከል
- ሆድ ድርቀት ለማስወገድ
- ሥሩ ደምን ለማጥራት ያገለግላል [1]
- ቅጠሉም ለአንቃር ብግነት ይታኘካል።
- ፍሬው ከብሳና ላፒስ ጋር እንድ ለጥፍ ለጭርት ይቀባል።[2]
- የቅጠሉ ለጥፍ በቅቤ ለችፌ ይለጠፋል።[3]
የጌሾ ግንድ በጣም ጠንካራ ስለሆነ ለተለያዩ የእንጨት ውጤቶች ሊያገለግል ይችላል። የጌሾ ዛፍ በምንጮች አካባቢ ቢተከል የመሬት መሸርሸርን ሊከላከል ይችላል። ከእርሻ ማሳ ዳርቻ ላይ በመትከልም የመሬትን ንጥር ነገር ከነፋስ እና ከዝናብ መከላከል ይቻላል። የጌሾ አበቦች በንቦች ዘንድ ከፍተኛ ተወዳጅነት ስላላቸው የጌሾ ተክል ለንብ እርባታና ለማር ምርት ከፍተኛ ግልጋሎት ሊሰጥ ይችላል።
- ^ አዘነ በቀለ ተሰማ፣ ጠቃሚ የኢትዮጵያ ዛፎችና ዳዋዎች (ቁጥቋጦና ሳር) ፣ ናይሮቢ ፲፱፻፹፭፣ ገጽ ፫፻፰
- ^ የፍቼ፣ ኦሮሚያ ባህላዊ መድሃኒት ጥናት 2006 ዓም ከዓቢዩ እኒየው እና ሌሎች፣ ጎንደርና አዲስ አበባ ኡኒቨርሲቲዎች ሥነ ፍጥረት ኮሌጆች
- ^ የዘጌ ልሳነ ምድር ባህላዊ መድሃኒት ጥናት 1999 ዓም ከጥላሁን ተክለሃይማኖት፣ ሚሩጸ ጊዳይ፣ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ