ከ«ሙሴ ቀስተኛ» ለውጦች መካከል ያለው ልዩነት

Jump to navigation Jump to search
4 bytes removed ፣ ከ10 ዓመታት በፊት
ሦስተኛውና የመጨረሻው ተልዕኮው በ [[ጥቅምት]] ወር [[1931|፲፱፻፴፩]] ዓ/ም ሲሆን [[በዳቄሮ]] በሚባል ሥፍራ ላይ ወደነበሩት ባላምባራስ (በኋላ ደጃዝማች) [[ገረሱ ዱኪ]] ነበር። እዚህ ሥፍራ ላይ ከሦስት ባላባቶች ጋራ የመጣው ቀስተኛ የሰባ አንድ ዓመት ሽማግሌ፣ ነጭ ጸጉር እና ባለሙሉ ጺማም ሲሆን አርበኞቹን ሰብስቦ በተጣራ አማርኛ ‘ንጉሠ ነገሥታችሁ እንኳን ትቷት የሄደውን አገር እናንተ በዚህ በልጅነት እድሜያችሁ ቅማል ወሯችሁ የማይቀርላችሁን ሞት ገደል ለገደል ከምታባርሩ ይልቅ ገብታችሁ ከኢጣልያ ጋር አገራችሁን በልማት ብታገለግሉ አይሻልም ወይ? መሣሪያችሁን አስረክባችሁ የገባችሁ እንደሆነ ኢጣልያ ትምራችኋለች፤ ሹመት እና ሽልማትም ትሰጣችኋለች” ብሎ ሲሰብካቸው ወጣት አርበኞቹም ቀደም ሲል በ፲፱፻፴ ዓ.ም ይኼው ሰላይ ወደ ራስ አበበ አረጋይ ዘንድ ሄዶ የጦሩን ኃይል ከሰለለ በኋላ ብዙ አርበኛ እንዳስፈጀ ሰምተው ስለነበር እነሱንም እንደዚሁ ለማስፈጀት እንደመጣ ተገንዝበውታል። ከሰበካው በኋላ ወደ እኩለ ቀን ሲሆን ተበተኑ።
 
ከዚህ በኋላ ሙሴ ቀስተኛ ወደሠፈረት ቦታ፣ በመጣባት በቅሎ በ[[ደጃዝማች ኪዳኔ ወልደ መድኅንወልደመድኅን|ባሻ ኪዳኔ ወልደመድኅን]]ታጅቦ ሲሄዱ፣ ባሻ ኪዳኔ ቀስተኛ የለበሰው ካፖርት በደም እንዳይበላሽ በማሰብ “አባቴ ሐሩር ፀሐይ ነውና እንዳይውብቅዎት ካፖርትዎን ያውልቁት” ሲሉት “ልጄ ልትገለኝ ነው” አላቸው። ይሄኔ ባሻ ኪዳኔ ወልደ መድኅን በመውዜር ጠመንጃ ሲመቱት 'ማማ ሚያ፤ ኢጣልያ ለዘለዓለም ትኑር ለኢጣሊያ ስል ሞትኩላት' ብሎ ሲፎክር በሽጉጥ ራሱን መትተው ገደሉት። የለበሰውንም ሙሉ ገበርዲን ልብስና ካፖርት እንዲሁም የ[[ንግሥት ዘውዲቱ|ንግሥተ ነገሥት ዘውዲቱ]] ምስል ያለበትን የብር ሰዐትና በቅሎውን ከነኮርቻው ማረኩት። እሱም እንደተገደለ አብረውት መጥተው የነበሩት ባላባቶች ለጄነራል ናዚ አስታውቀው ኖሮ ሃያ ዓምስት ባታሊዮን ወታደርና ሃያ ስምንት አውሮፕላን ወደበዳቄሮ ዘምቶ ተርታውን ለሦሥት ቀን ሲከላከሉ ከቆዩ በኋላ አርበኞቹ ተሸንፈው ጠላትም የሙሴ ቀስተኛን እሬሳ አንስቶ ወሰደ። አርበኞቹም ከዚያ ሥፍራ ሸሽተው ሶዶ ላይ እንደገና ለስምንት ቀን ተዋጉ። <ref>4 [[አዲስ ዘመን]] ጋዜጣ ፣ ፴፰ኛ ዓመት ቁጥር ፴፰፣ ቅዳሜ [[ጥቅምት 16|ጥቅምት ፲፮]] ቀን [[1972|፲፱፻፸፪]] ዓ/ ም </ref>
 
አንቶኒ ሞክለር (እንግሊዝኛ፤ Anthony Mockler) ስለቀስተኛ ሞት ሲያወሳን በስህተት በገረሱ ዱኪ ተሰቅሎ ሞተ ይለናል። ሆኖም የጣልያን መንግሥት ገረሱን ለሚገድልለት ሰው ፶ ሺህ ሊራ እንደሚሰጥ ማወጁንና በኋላ የጣልያን መንግሥት እንደራሴ፣ ዱካ ዳኦስታም ይሄንን ሽልማት እጥፍ እንዳደረገው ይነግረናል። <ref> Mockler, Anthony; Haile Selassie’s War (2003), p191</ref>
 
ሙሴ ቀስተኛ በዚያው በ[[1930|፲፱፻፴]] ዓ/ም ከሞት በኋላ የጣልያን መንግሥትን የወርቅ የጦር ጀብዱ ሜዳይ (ጣልያንኛ፤ Medaglia d'oro al valor militare) ተሸልሟል። የመዳልያውን አሰጣጥ የሚተነትነው ጽሑፍ በፋሽሽት ፕሮፓጋንዳ እና ሐሰት የተመረዘ ሲሆን ሙሴ ቀስተኛ በኢጣልያ መንግሥት ሥር የትውልድ አገሩን ሲያገለግል እንደሞተ ይነግረንና፣ “አንድ ፈሪ፣ አረመኔ የሽፍታ ዓለቃ (ገረሱ ዱኪን ማለቱ ነው!) ለውይይት ና ብሎ ጽፎለት በማታለል እጁን ሊይዘው መሆኑን ሲገነዘብ፣ እሱ ግን በዕድሜው የገፋ ቢሆንም እጁን ላለመስጠት ሲያመልጥ ተገደለ።” ይለናል።<ref> http://www.quirinale.it/elementi/DettaglioOnorificenze.aspx?decorato=13955</ref>
 
==ድምዳሜ==
3,107

edits

Navigation menu