መስከረም ፳፩

ከውክፔዲያ
(ከመስከረም 21 የተዛወረ)

መስከረም ፳፩ ቀን በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የዓመቱ ፳፩ኛው ዕለት ነው። ከዚህ ቀን በኋላ እስከ ዓመቱ ፍጻሜ ድረስ በዘመነ ሉቃስ ፫፻፵፭ ቀናት ሲቀሩ በዘመነ ዮሐንስዘመነ ማቴዎስ እና ዘመነ ማርቆስ ደግሞ ፫፻፵፬ ዕለታት ይቀራሉ።

በዚህ ዕለት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የቅድስት ማርያምን በዓል በማሰብ ትዘክረዋለች።


ዓቢይ ታሪካዊ ማስታወሻዎች[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

  • ፲፱፻፶፬ ዓ.ም - የምስራቅ እና የምዕራብ ካሜሩን ክፍሎች ተዋህደው፣ የካሜሩን ፌዴራላዊ ሪፑብሊክን መሠረቱ።
  • ፲፱፻፶፬ ዓ.ም - በአሜሪካ የጥቁሮች ሰብዓዊ መብት ትግል ጄምስ መሬዲዝ የተባለውን ጥቁር ተማሪ ወደ ሚሲሲፒ ዩኒቨርሲቲ መግባት በተከሰተው ግጭት ሁለት ሰዎች ሲሞቱ ሰባ አምሥት ሰዎች ደግሞ የአካል ጉዳት ደረሰባቸው።
  • ፲፱፻፷፪ ዓ/ም - ለሟቹ የግብጽፕሬዚደንት ጋማል አብደል ናስር የቀብር ስርዓት የወጡ ወደ አምሥት ሚሊዮን የሚገመቱ አዘነተኞች በተነሳ ግርግር እና ግፊያ ብዙ ሰዎች ተጨፍልቀው ሞቱ።
  • ፲፱፻፷፯ ዓ/ም - በፊሊፒንስ ከተማ ማኒላ ላይ በተካሄደው የቡጢ ውድድር ሞሐመድ አሊ ባላጋራውን ጆ ፍሬዘርን ከአሥራ አራት ዙር ግብግብ በኋላ በነጥብ ብልጫ አሸነፈ።


ልደት[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

ዕለተ ሞት[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

ዋቢ ምንጮች[ለማስተካከል | ኮድ አርም]


የኢትዮጵያ ወራት
መስከረም - ጥቅምት - ኅዳር - ታኅሣሥ - ጥር - የካቲት - መጋቢት - ሚያዝያ - ግንቦት - ሰኔ - ሐምሌ - ነሐሴ - ጳጉሜ