ታኅሣሥ ፩

ከውክፔዲያ
(ከታኅሣሥ 1 የተዛወረ)

ታኅሣሥ ፩ ቀን በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የዓመቱ ፺፩ኛው ቀን እና የወሩ መጀመሪያ ቀን ነው። ከዚህ ዕለት በኋላ እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ፣ በ ዘመነ ሉቃስ ፪፻፸፭ ቀናት በ ዘመነ ዮሐንስ፤ በ ዘመነ ማቴዎስ፤ እና በ ዘመነ ማርቆስ ደግሞ ፪፻፸፬ ቀናት ይቀራሉ።

ዓቢይ ታሪካዊ ማስታወሻዎች[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

፲፰፻፲ ዓ/ም የአሜሪካ ኅብረት በዛሬው ዕለት የሚሲሲፒን ግዛት ሃያኛ የማኅበር ዓባል አድርጎ ተቀበለ።

፲፰፻፷፩ ዓ/ም በዓለም የመጀመሪያው የመንገድ ተሽከርካሪዎች መቆጣጠሪያ መብራት በእንግሊዝ ዋና ከተማ በለንደን ላይ የፓርላማ ሕንጻ (የዌስትሚንስተር ቤተ መንግሥት) ‘Palace of Westminster’ ፊት ለፊት ተተክሎ አገልግሎት ላይ ዋለ።

፲፰፻፺፬ ዓ/ም ለመጀመሪያ ጊዜ የኖቤል ሽልማቶች ተሸለሙ።

፲፱፻፳፱ ዓ/ም በብሪታንያ በንጉሡ የፍቅረኛቸውን ምርጫ ምክንያት በተከሰተው ቀውስ፥ ንጉሥ ኤድዋርድ ስምንተኛ ሥልጣናቸውንና ዘውዳቸውን መልቀቅ የሚያስችላቸውን ህግና ስምምነት ፈረሙ።

፲፱፻፶፯ ዓ/ም በኖርዌይ ዋና ከተማ ኦስሎ ላይ በተካሄደ ሥነ ሥርዐት ላይ ጥቁር አሜሪካዊው የሰብአዊ መብት ዋና ተሟጋችና ሰማዕት ማርቲን ሉተር ኪንግኖቤል ሰላማዊ ሽልማት ተቀበሉ።

፲፱፻፸፩ ዓ/ም የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስቴር ሜናኽም ቤጊን እና የግብጽ ፕሬዚደንት አንዋር ሳዳትኖቤል ሰላማዊ ሽልማት ተካፋዮች ሽልማቱን ተቀበሉ።

፲፱፻፸፬ ዓ/ም የብሪታንያቢ.ቢ.ሲ.አሜሪካ አሥራ አምሥት ግዛቶች ውስጥ ‘ሰዶማውያን’ን የሚያጠቃ ያልታወቀ አዲስ በሽታ እንደገባ እና በእነኚሁ ግዛቶች ውስጥ ሰባ አምሥት ሰዎች፥ በእንግሊዝ አገር ደግሞ አንድ ሰው በዚሁ በሽታ መሞታቸውን ዘገበ። ይሄ በሽታ በኋላ ኤይድስ የተባለው በሽታ ሲሆን ሠላሣ ዓመታት እንኳን ባልሞላ ጊዜ ውስት በዓለም ላይ ወደ ሃያ አራት ሚሊዮን የሚጠጉ ሰዎችን ሕይወት ወስዷል።[1]

፲፱፻፸፯ ዓ/ም የደቡብ አፍሪቃው ጳጳስ ዴዝሞንድ ቱቱኖቤል ሰላማዊ ሽልማት ተቀበሉ።

፲፱፻፹፩ ዓ/ም በቀድሞው የሶቪዬት ሕብረት ግዛት ውስጥ በአርሜኒያ ክልል ውስጥ በተከሰተው የምድር እንቅጥቅጥ አርባ አምሥት ሺህ ሰዎች ሲሞቱ ወደ ግማሽ ሚሊዮን የሚጠጉ ሰዎች ደግሞ መኖሪያ ቤታቸውን አጥተዋል። ስፒታክ የምትባል የሃያ አምሥት ሺህ ነዋሪዎች ከተማ በዚሁ እንቅጥቅጥ ፈጽማ ወድማለች።

፲፱፻፹፯ ዓ/ም የፍልስጥኤም መሪ ያሲር አራፋት እና የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስቴር ይስሐቅ ራቢን እንዲሁም የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴሩ ሥምዖን ፔሬዝ በጋራ የተሰጡትን የኖቤል ሰላማዊ ሽልማት ተቀበሉ።

ልደት[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

፲፱፻፵፩ ዓ/ም የፍልስጥኤም ነጻነት ግንባር የሚባለውን ድርጅት የመሠረቱት አቡ አባስ

ዕለተ ሞት[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

፲፰፻፹፱ ዓ/ም ደማሚትን የፈጠረውና በኋላም በስሙ የተመሠረተውን የኖቤል ሽልማት ያቋቋመው የስዌድ ተወላጅ አልፍሬድ ኖቤልበዚህ ዕለት አረፈ።

፲፱፻፷ ዓ/ም ጥቁር አሜሪካዊው ዘፋኝ ኦቲስ ሬዲንግ በተወለደ በሃያ ስድስት ዓመቱ በአውሮፕላን አደጋ ሞተ።

፲፱፻፺፰ ዓ/ም ጥቁር አሜሪካዊው የቀልድ ባላባት እና የፊልም ተዋናይ ሪቻርድ ፕራየር በተወለደ በ ስድሳ አምሥት ዓመቱ አረፈ።

ዋቢ ምንጮች[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

  1. ^ http://news.bbc.co.uk/onthisday/hi/dates/stories/december/10/newsid_4020000/4020391.stm