ኢትዮጵስት በዓለም ዙሪያ

ከውክፔዲያ
Jump to navigation Jump to search

ኢትዮጵስት በዓለም ዙሪያኢትዮጵያ ጥናት ፡ ይህ ጥናት አጠቃላይ የሆነ የኢትዮጵያ የታሪክ ፣ የጆግራፊ፣ የዘር፣ የቋንቋ፣ የስነፅሁፍ፣ የባሕልየተፈጥሮ ሐብት፣ የኤኮኖሚ፣ የፖለቲካና የሶሻል፣ ጥናቶችን ያጠቃልላል። ይህ ነጻ የሆነ ሳይንሳዊ ጥናት በቅርቡ ተጠናክሮ የቀጠለ ቢሆንም በቅድመ ጥናቶች የተደረጉ ስራወች እንደሚያሳዮት ጥናቶች የተከሃዱት ባጠቃላይ ፖቶሎጅካል የታሪክ፣ የቋንቋ፣ የባህልና በሀገሪቱ የሚኖሩ ጎሳወችን በተመለከተ ነበር። በመጀመሪያ የኢትዮጵስት ጥናተቶች የወጡት በ17ኛዉ ክፍለ ዘመን መጨረሻ ሲሆን በ20ኛዉ ክፍለ ዘመን በአዉሮፓዉያን ቋንቋ በመጀመሪያ ጊዜ በኢጣሊያንኛ ከዚያም በፈረንሳይኛና በእንግሊዝኛ ስለትዮጵያ ጥናታዊ ጽሑፎች ብቅ ማለት ጀመሩ። ስለዚህም እንደምሳሌ የሚጠቀሰዉ ‘የኢትዮጵያ ጥናት‘ በሚል /studi etiopici; etudes ethiopiennes; Ethiopian studies/ በኢጣሊኛ ቋንቋ የሚታተም ጽሑፍ ነበር። የኢትዮጵስት የኢትዩጵያ ጥናት የሚለዉ ሀሳብ በተለይም ከመጀመሪያዉ ዓለም አቀፍ የኢትዮዽያ የጥናት ኮንፍረስ በሁዋላ ታዋቂ ሆኗል። {1959 በሮም ኢጣሊ} በአሁኑ ጊዜ ከ16 ያላነሱ ኮንፍረንሶች ተካሂደዋል። በነዚህም ኮንፍረንሶች ላይ አያሌ ኢትዮጵስት ምሁራን በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ብዛት ያላቸዉ ጥናቶችን አቅርበዋል። በመካከለኛዉ ዘመን ኢትዮዽያ የሚባለዉ አካባቢ በተጨማሪ ‘የቅዱስ ዮሐንስ የክርስቲያኖች ሀገር በሚል በብዛት ይታወቅ ነበር። እንዲሁም አቢሲንያ በመባልም ይታወቃል። በ4ኛዉ ክፍለዘመን ክርስትናአክሱም በመስፋፋቱ በኢትዮጵያና በኗሪወቿ ለይ ከፍተኛ ለዉጥ አስከትሏል። ለዉጭዉም ዓለም ትኩረትን አሳይቷል። ስለሆነም የቤዛንቲያን፣ የአርሚያን፣ የሮማዉያን ፣የፖርትጋል ኤፔስ ኮፖሳት በ6ኛዉ ክፍለዘመን በኢትዮዽያ ጉብኝቶችን አድርገዋል።

አረቦች ከኢትዮዽያና ከሕዝቦቿ ጋር በጥሩ ሁኔታ ይተዋወቃሉ። ይሄም እስልምና ከመፈጠሩ በፊት በነበረዉ የንግድና የባህል ልዉዉጦችና ግንኙነቶች ነበር። ከእስልምና በሁዋላም ቢሆን ችግር ባጋጠማቸዉ ጊዜ የመሐመድ ተከታዮች በስደት ወደ ኢትዮጽያ መጥተዋል። የአረብ የታወቁ የጆግራፊና የታሪክ ጽሐፊወች ያኩቢማሱዲኢባን ሀያካሊያያኩዬታኢባን ሱኢዳ ከ9ኛዉ እስከ 14ኛዉ ክፍለዘመን በተደረጉ የጥናት ስራወቻቸዉ በጣም ከፍተኛ ታሪካዊ ዋጋ ያላቸዉና ስለ መካከለኛዉ ዘመን ኢትዮጽያ ታሪክ፣ ጆግራፊ፣ ኤትኖግራፊ የተጻፉ ስራወቻቸዉ ከፍተኛ የታሪክ ማጣቀሻወች ናቸዉ።


በመካከለኛዉ ዘመን አዉሮፓዉያን በተከታታይ ወደ ኢትዮጽያ ትኩረት አድርገዉ ነበር። ይሄዉም በ12ኛዉ ክፍለ ዘመን መጀመሪያ ላይ ነዉ። ለዚህም ዋናዉ ምክንያት በዓለም ላይ ከፍተኛ የሆነ የእስልምና መስፋፋት ስለነበር ይህንን ለመቋቋም በሚደረገዉ ትግል አጋዠ ለማድረግና የጋራ ግንባር ለመፍጠር ነበር። በዚህ የእስልምና መስፋፋት ዘመን ይህች የቅዱስ ዬሐንስ የክሪስታኖች ሀገር በሚል የምትታወቀዉ ኢትዮጵያ የበኩሏን አስተዋጦ አድርጋለች። ኢትዮጵያ በዚያን ጊዜ በእየሩስዓለምና በሮም የኢንፎርሜሽን ሴንተሮች ቤተክሪስታኖች ነበሯት።እንዲሁም በዚያን ጊዜ ካይሮ ታለቅ የንግድ ሴንተር ስለነበረች ኢትዮጵያም ታለቅ የንግድ ግንኙነት ስለነበራት እንደ ኢንፎርሜሽን ሴንተር ትገለገልበት ነበር። 16ኛዉና17ኛዉን ክፍለዘመን አዲሱ የኢትዮጵያ ጥናት የታሪክ ዘመን በማለት መጥራት ይቻለል። ይሄዉም የፖርቱጋሎች ወደ ኢትዮጵያ መምጣትና እንዲሁም የጽሐፋቸዉ ከፍተኛ ዋጋ ያላቸዉ የታሪክ ማስታወሻወችና መጽሐፍት ናቸዉ። ከነዚህም መካከል፡ አለባሪሽ ‘እዉነተኛ ታሪክ ስለ ቅዱስ ዩሐንስ የቅዱሳን ሀገር’ {1540} ካሽታኑዩዝ “የፖርትጋሎች ጉዞ ታሪክ በአቢሲኒያ’ {1564} እንዲሁም ፖርቱጋልን ያገለግል በነበተዉ የእስፓኒሽ ተወላጅ ፓይሱ ‘የኢትዮጽያ ታሪክ’ በመጀመሪያ አጠቃሎ የታተመዉ በ1945/46 እነዚህ የፖርቱጋል አገር ጎብኝወችና ታርክ ጸሐፊወች ኢትየጵያንና የሕዝቦቿን ታሪክ ለአዉሮፓዉያን በማስተዋወቅ ታላቅ ሚና ተጫዉተዋል ወይም ቀደምትነት ነበራቸዉ። በ17ኛዉ ክፍለዘመን መጨረሻ በአዉሮፓና በሌሎችም አገሮች ስለኢትዮዽያ ስለመሬቷ ለምነት፣ ስለሕዝቦቿ አኗኗር፣ ስለቋንቋዋና ባሕሏ ብዙ ጥናታዊ ስራወች ተሰርተዋል። ሆኖም እነዚህ ስራወች ብዙወቹ ስተቶች ያሉባቸዉና ያልተስተካከሉ ነበሩ። በአዉሮፓ የኢትዮጵያ ጥናት መስራች ተብሎ የሚታወቀዉ ኢትዮጵስት ጀርመናዊዉ ተመራማሪ ፔሩ ሉዶልፍ {1624-1704} ነዉ። የሱ ስራወችም የኢትዮጵያ ታሪክ መዝገበ ቃላቶች ናቸዉ ማለት ይቻላል። ስራወቹም በተለያዩ የታሪክ ክፍሎች ላይ የተመሰረቱ ናቸዉ። ለምሳሌ ኤትኖግራፊ/ሕዝብ /፣ ጆግራፊ፣ ታሪክ፣ ፍልስፍና ሌሎችም ነበሩበት። የእሱ የኢንፎርሜሽን ምንጭም ለብዙ ዓመታት በሮም ይኖሩ የነበሩት ኢትዮጵያዊ ቄስ መነኩሴ ግሪጎሪ ናቸዉ። ፔሩ ሉዶልፍ ታላላቅ ስራወቹን በፍራንክፈርት አሳትሟል ከእነዚህም መካከል። ‘የኢትዮጵያ ታሪክ’ {1681}፣ ‘አጠቃላይ የሆነ እርማት ከኢትዮጵያ ታሪክ’ {1691}፣ ‘የግዝ ቋንቋ ሰዋሰዉ /ግራመር/ {1661-1702}፣ ‘የአማርኛ ሰዋሰዉ /ግራመር/ና መዝገበ ቃላት’ {1698}፣ ‘የግዝ ስነጽሑፍ መስፋፋትና መዝገበ ቃላት’ {1699} የሚሉ ናቸዉ።

የፔሩ ሉዶልፍ መጸረሐፍትና ስራወች በፈረንሳይ፣ በእንግሊዝና በሌሎችም የአዉሮፓዉያን ቋንቋወች ተተርጉመዉ ነበር። ለረጅም ጊዜም እንደ ቋንቋ መዝገበ ቃላትና የታሪክ መማሪያነት አገልግለዋል። ‘የኢትዮጵያ ታሪክ’ የሚለዉ መጽሐፍ በራሽያን ቋንቋ ተተርጉሞ ለታላቁ ፔትሮስ /ጴጥሮስ/ አንደኛ በስጦታ ተሰጧቸዉ ነበር።

ከፔሩ ሉዶልፍ በሁዋላ በኢትዮዽያ ጥናት ላይ መዳከም ታይቶ የነበር ቢሆንም በ18ኛዉ ክፍለዘመን መጨረሻና በ19ኛዉ ክፍለዘመን መጀመሪያ እንግሊዛዊያን ዠ- ቦርዩስ {1730-1794} እና ገ- ሶልት {1780-1827} አዲሱን የኢትዮጵያ ጥናት ጀመሩት። እረጅም ጊዜ የፈጀ ጉብኝትም አደረጉ ብዙ ጥናቶችንም አቀረቡ ቦርዩስ አባይጣና ይፈልቃል አለ። በ1790 ጉብኝቱ በጻፈዉ ጽሑፍ ብዙ የጆግራፊ፣ የኤትኖግራፊ፣የታሪክ ሪኮርዶችን ለመጥቀስ ሞክሯል። ብዙ የኢትዮጵያ የጅ ጽሑፎችንም ሰብስቧል። በሁዋላም ለኦክፎርድና ለማንችስተር ዩንበርስቲወች ሰጧቸዋል። ሶልት ሁለት ጊዜ ያህል ኢትዮጵያን ጎብኝቷል {1805-1810} በስራወቹ ትኩረት ያደረገዉ በሰሜን ኢትዮዽያ በተለይም በአክሱም በሚገኙት ሐወልቶችና ጸረሑፎች ላይ ነበር። በ19ኛዉ ክፍለዘመን ኢትዮጵስትና የኢትዮጵያ ጥናት በፍጥነት ተቀይሯል። ብዙ ጥናታዊ ተቋማትም ተመስርተዋል። በአዉሮፓ በሚገኙ የኢትዮጵያ ቅርሶች ላይም መሰረታዊ የሆኑ ሳይንሳዊ ምርምሮችና ጥናቶች ተካሂደዋል። እንዲሁም ብዙ ጥናታዊ ጉዞወች ወደ ኢትዮዽያ ተደርገዋል። በተደረጉትም ጉዞወች በርካታ ጥናቶች ተካሂደዋል። ስለ ሴሜትክኩሸቲክ ቋንቋወች ጥናቶች ተደርገዋል። በ19ኛዉ ክፍለዘመን አጋመሽ ጀርመናዊዉ ተመራማሪ አ-ዲሊማን መሪነት ስለ ጥንታዊ ኢትዮጵያ ታሪክ፣ ስለ መካከለኛዉ ዘመን ኢትዮጵያ ታሪክ፣ ስለግዕዝ ቋንቋ ሰዋሰዉ /ግራመር/ ስለ ሊቶግራፊና ሌሎችም ጥናቶችን አካሂደዋል። በነዚህና በመሳሰሉት ስራወች ላይ ከፍተኛ አስተዋጾ ያደረጉ ተመራማሪወችም፡ ፈ- ፐሪቶሪዮስኦ- ሙቲቦክስከ- ቢትሊድ፣ እንዲሁም አዉስትሪያዊዉ ኤ- ሊትማን ይገኙበታል።ኤ- ሊትማን በ1905፣1906 በአክሱም የተካሄደዉን የአርኪኦሎጅ ምርምርና የተመራማሪወች ቡድን መርቷል። የዚህ ጥናት ዉጤት በአራት ቶሞች በ1913 ታትሟል። ብዙ የአርኪኦሎጅና የኢፖግራዊ ስራወች ስለ ጥንታዊ ኢትዮጵያ ይዟል። ኤ- ሊትመን {1910-1915} ሌላ የጥናት ቡድንም በኢትዮጵያ መርቷል። ይህ የጥናት ቡድን ስለስነጽሑፍና ስለፍልስፍና ጥናት ያደረግ ሲሆን፤ በተለይ በትግሬኛ ቋንቋ ላይም ጥናት አካሂዷል። ኤ- ሊትማን በብራሴል ዩንበርስቲ በሴሚቶሎጅ ፋኮሊቴት ስለ ኢትዮጵያ ያስተምር ነበር።

በኢጣሊያ የኢትዮጵያ ጥናት[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

በኢጣሊያ የኢትዮዽያ ጥናት መስራች ኢትዮጵስት ኢ- ገቢድ {1844-1935} ነበር። ይህ ሰዉ ብዙ የቋንቋ የጥናት ጽሑፎችን ያበረከተ ነዉ። የሱ ተማሪ የነበረዉ ኮንቴኢኦሲን በኢትዮጵያ ኤትኖግራፊ ሕዝብና ቋንቋን በሚመለከት ስፊ ጥናቶችን አካሂዷል። የትግሬኛና የሀረሬኛ ቋንቋወችንም ይናገር ነበር። ኢጣሊ በኢትዮጵያ ሁለትዮሽ ባሕሪ ያለዉ ጥናት ስታካሂድ ቆይታለች። በቋንቋወችና በሌሎችም ጉዳዮች ላይ የሚደረገዉ ጥናት በጣም ተዳክሞ የኢጣሊያን የቅኝ ግዛት ታሪክ በተመለከተና የቅኝ ግዛት መስፋፋትን በተመለከተ ብዙ ስራወች ተካሂደዋል። በ1941ዓም በሮም የኢትዮጵያ ጥናት ጆርናል ይታተም ነበር። /Rassegna distudi etiopici/ ለዚህ ከፋተኛ አስተዋጦ ያደረጉ ምሁራን፡ራይኒሮ፣ ፐሮካች፣ ተሩሊትስ፣ ናቸዉ። በኢጣሊያ ስለ ኢትዮጵያ ጥናት የሚካሄድባቸዉ ተቋማት የኢትዮጵያ ሴንቴር በኢጣሊያ፣ የምስራቃዊያን ጥናት ፋኮሊቴት በሮምና እንዲሁም በኒኦፖሎስ ዩንበርስቲ ነበር። በማከታተልም ኤ- ቺሩሊ የተባለዉ በሁለት ተከታታይ ጽሑፎች ጥናቱን አዳብሮታል እነዚህም ‘ኢትዮዽያ በፓላስታይን’ {1943-47}፣ ‘የኢትዮዽያ ስነጽሑፍ ታሪክ’ {1956}፣

በፈረንሳይ የኢትዮጵያ ጥናት[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

በ19ኛዉ ክፍለዘመን መጨረሻ በመጀመሪያዉ አጋማሽ በ20ኛዉ ክፍለዘመን መጀመሪያ ኢትዮጵስት ዠ- ጋሊቢ የኢትዮጵያን ጥናት በፈረንሳይ መሰረተ። ዠ-ጋሊቢ በፈረንሳይ ዩንበርስቲ ሴሚቶሎግና ፕሮፌሰር ቢሆንም ጥናት በሚያደርግበት ጊዜ የፋኮሊቲዉ ሃላፊ ፈ- ሞንዶን ቢዳይ ይባል ነበር። ከዚያም ታዋቂዉ ሴሚቶሎግና የቋንቋ ምሁር ኢትዮጵስት መ- ኮኤን እነሱን በመተካት ፋኮሊቲዉን ይመራዉ ነበር። በፈረንሳይ የኢትዮጵያ ጥናት በተለያዩ የፓሪስ ዩንበሪስቲወች የምስራቅ ቋንቋወች ፋኮሊቲወች ጥናቶች ይካሄዳሉ፣ ጥናት ከአካሄዱ ምሁራን መካከል፣ የሚከተሉትን መጥቀስ ይቻላል፡ ሊክላን፣ አንፈሬ፣ ካኮ፣ ቱቢኦና፣ ዶርስስ ይገኙባቸዋል። በራሽያ የኢትዮጵያ ጥናት በ19ኛዉና በ20ኛዉ ክፍለዘመን በዓለም አቀፍ ኢትዮጵስቶች መካከል የራሽያ ተመራማሪወች ከፍተኛዉን ቦታ ይዘዉ ይገኛሉ። ይህም በታሪክ፣ በሐይማኖት፣ በአርኪኦግራፊ፣ በቋንቋ ከፍተኛ አስተዋጦ አድርገዋል። እነዚህ ከፍተኛ አስተዋጦ ያደረጉ ምሁራኖች፣ ቦሎቶብ፣ ኮባሌብስኪ፣ ኢሊሴባ፣ ባሮቢትስና፣ ቡልታቢች፣ አርታሞኖባ፣ እና ሌሎችም ሲሆኑ ከቅድመ አብዮት ስራወች መካከል ስለ ኢትዮጵያ ከፍተኛ በታ የሚይዘዉ ቱራዬብ መሰረታዊ የሆኑ የታሪክና የቋንቋ ጥናቶችን አካሂዷል። ከነዚህም መካከል፡

“የኢትዮዽያ ጥናት አርኪኦሎጅካል ማጣቀሻ”[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

“የአቢሲኒያ ስብስቦች 15ኛዉና16ኛዉ ክፍለዘመን” የሚሉ ሲሆኑ ቱራዬብ በዘመኑ በምስራቃዊ ጥናት ታዋቂ በነበረዉ የሐርከፍ ዩንበርስቲ ከታዋቂዉ የምስራቃዊያን ምሁር ከዶርኖም ጋር በመሆን የኢትዮጵን ቋንቋ ያስተምር ነበር። የኢትዮጵያን ጥናት በመቀጠልም የቱራዬብ ተማሪ የነበረዉ ኢትዮጵስት ኮራትኮብስኪ ብዙ ስራወችን አበርክቷል። በታሪክና በስነጽሑፍ ጥናት ከተሰሩት ስራወች መካከል በተለይም አማረኛ ቋንቋን በተመለከተ ዩሽማኖብ ከሚጠቀሱት ዉስጥ አንዱ ነዉ። በባቢሎብ {1927} የተመራዉ የቦታኒክና የአግሮኖሚ ኢክስፖዴሽን ኢትዮዽያ የእርሻን ምርት በመጠቀም የመጀመሪያዋ አገር መሆኗን አረጋግጧል ኢትዮዽያ በጣም ጥንታዊና የእርሻ ስራትን ቀድማ የጀመረች ሀገር ነች በማለት አረጋግጠዋል። የዚህ ጥናት ስራወች በራሽያ በ1930 በሊቢና፣ ሊሶብስኪ፣ኦሊዴሮጌ፣ በሚባሉ ምሁራን ተመራማሪወች ታትመዋል። በኢትዮጵስቶች የተሰሩ የኢትዮዽያ ጥናታዊ ስራወች ወደ አዉሮፖዉያን ቋንቋ በብዛት መተርጎም የጀመሩት በ20ኛዉ ክፍለዘመን ነዉ። እነዚህም ስራወች የተተረጎሙት ለብዙ ዘመን በአዉሮፖ በኖሩት ሰወች ነዉ። የታወቁት ጽሐፊ አፈወርቅ ገብረእየሱስ በኢጣሊያን ቋንቋ መጽሐፍቶችን አሳትመዋል። ‘የአማረኛ ቋንቋ ሰዋሰዉ /ግራመር/1905}፣ ‘የአማረኛ ግስ’ {1911} ከሁለተኛዉ ዓለም ጦርነት በፊት አለቃ ታዬ ገብረመድሕን በጀርመን ይሰሩ ነበር። አለቃ ታዬ ‘የኢትዮዽያ ሕዝብ ታሪክ’ የሚል መጽሐፍ ጽፈዋል። እንዲሁም ተክለ ማሪያም መሀሪ በግዝ ቋንቋ ጥሩ ስራወችን አሳትመዉ ነበር። ከሁለተኛዉ የዓለም ጦርነት በሁዋላ የተክለ ጻድቅ መኩሪያ ጥናታዊ ስራወች ከ1951ዓም ጀምሮ መታተም ጀመረ። በኢትዮጵያዊዉ ምሁር ተሰማ ሀብተወልደሚካኤል ለመጀመሪያ ጊዜ መሰረታዊ የሆነ የአማረኛ መዝገበ ቃለትም ተጻፈ። በ1950ዓም አዲሱ የኢትዮጰያ ጥናት ምራፍ ተጀመረ ማለት ይቻላል። ብዙ ኢንስቲቲዉቶችና ተቋማትም መቋቋም ጀመሩ። እንደዚሁም ብዙ የጥናት ተቋማት በተከታታይ ዓለማቀፍ የጥናት ኮንፍረንሶች መካሄድ ጀመሩ። ኢትዮጵያን በተመለከተ በሰፊዉ የአንትሮፖሎጅ፣ የአርኪኦሎጅ፣ የኢትኖግራፊ፣ የሰነጽሑፍ፣የሶሽኦሎጅ ጥናቶች በስፊዉ መካሄድ ተጀመረ። እንዲሁም የጥናት መስኮች እየተስፋፉ በዘመናዊ የሶሻልና የኢኮኖሚ፣ የዓለም አቀፍ ግንኙነቶችን የተለያዩ ቋንቋወችንና ጎሳወችን በሚመለከት በሰፊዉ ጥናቶች ይካሄዳሉ። በራሽያ ዉስጥ ስለኢትዮጵያ ጥናት የሚያደርጉ ተቋመትና ምሁራን በጣም በርካታወች ናቸዉ። ከነዚህም ዉስጥ ‘የአፍሪካ ጥናት ኢኒስቲቲዉት፣ ሳንክ ፒተርስቡርግ ዩንበርስቲ ኤትኖግራፊ ፋኮሊቴት፣ የዓለም ስነጽሑፍ ኢኒስቲቲዉት፣ የራሽያ አካዳሚ የምስራቅ ፋኮሊቴትና ሌሎችም። በመካከለኛዉ ክፍለ ዘመን በኢትዮዽያ ታሪክ ላይ ጥናት ያካሄዱ ራሽያዊ ምሁራን ኮቦሻኖብ፣ ቼርንትሶብ፣ ሲሆኑ በዘመናዊ የኢትዮዽያን ታሪክ ላይ ጥናት ያደረጉ ምሁራን፣ ባሲን፣ ራይት፣ተራፊሞብ፣ ትስኪን፣ያግያ፣ ናቸዉ። እንዲሁም ኢትዮጵያ ከራሽያ፣ ከጆርጅያና፣ ከአርሜንያ ጋር የነበሯትን ግንኙነቶች በሚመለከት ጥናት ያደረጉ ምሁራን፣ ማቻራደዜ እና ቶፑዝያን፣ ሲሆኑ ስለኢትዮጵያ ከአረብ የታሪክ ምንጮችን በተመለከተ ጥናት ያደረጉ ምሁራን፣ ቡኒያቶብ ነበሩ። በሌሎች ዘመናዊ የሶሻልና የኢኮኖሚ ጉደዮች ላይ ጥናት ያደረጉ ምሁራንም ጋሊፔሪን፣ ኮኪየብ፣ ሸራዬብ፣ ሼርር ናቸዉ። ቋንቋን በተመለከተ ጥናት ያካሄዱ ምሁራን፣ጋንኪን እና ቲቶብ ናቸዉ። የኢትዮጵያን ስነጽሑፍ በተመለከተ ጥናት ያካሄዱ ምሁራን፣ ቦሊፔ፣ ፓፕሼባ፣ ቱተሩሞባ ሲሆኑ በአጠቃላይ በኢትዮጵያ ጥናት ታላቅ አስተዋጦ ከአደረጉት ኢትዮጵስት ምሁራን መካከል በተለይ የሚከተሉት ጉልህ ቦታ ይይዛሉ። ማንቲሊኒችኮ፣ ባርተንትስኪና እንዲሁም የቼህ ምሁራን የሆኑት ፔትራቾክ፣ ቼርን ናቸዉ። በታላቋ ብርታኒያ የኢትዽያ የጥናት በታላቋ ብርታኒያ የኢትዽያ የጥናት ሴንተር በለንደን ዩንበርስቲ የምስራቅ ፋኮሊቴትና በኦክስፎርድና በማንችስተር ዩንበርስቲ ጥናቶች ይካሄዳሉ። የለንደን ዩንበርስቲ የኦሪንታልና የአፍሪካ ጥናት በሚል ቡሊቴን ያሳትማል። ስለኢትዮዽያ የታወቁት ኢትዮጵስት ሪቻርድ ፓንክረስት ብዙ ስራወቻቸዉን አሳትመዋል። ሌሎች እንግሊዛዊ አትዮጵስቶች ፔሬም፣ ኡሊንዶፍ ናቸዉ።


በአሜሪካ ስለኢትዮጵያ ጥናት[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

በአሜሪካ ስለኢትዮጵያ ጥናት የተጀመረዉ ከሌሎች አካባቢወች ጋር ሲነጣጠር በቅርቡ ቢሆንም በአሁኑ ጊዜ በብዛት ስራወች በመካሄድ ላይ ይገኛሉ። በአሜሪካ ስለኢትዮጵያ ጥናት የሚያደርጉ ሴንተሮች ወይም ተቋማት፡ በሜችጋን የንቨሪስቲና በካሊፎርኒያ የንቨሪስቲ የአፍሪካ ጥናት ማዕከል እና ሌሎችም ስለኢትዮጵያ ጥናቶችን ያካሂዳሉ። ከ1977ዓም ጀምሮ የሜችጋን ዩንቨሪስቲ “የኢትዮጵስቶች ማስታወሻ” በሚል እትሞችን ያወጣ ነበር። /Ethiopianist Notes/ እንዲሁም በኒዉጀርሲ ዩንቨሪስቲ ከ1978ዓም ጀምሮ “የአፍሪካ ቀንድ “በሚል ጆርናል ያሳትሙ ነበር። /Horn of Africa/ በኢትዮጵያ ጥናት እድገት ዉስጥ ዋናዉና ታላቅ ቦታ ሊሰጠዉ የሚገባዉ በኢትዮጵያ የተቋቋሙት የጥናት ተቋማትና የአርኪኦሎጅ ኢኒስቲቲዉት {1961} የአርኪኦሎጆ አናላይዝ በሚል እትመቶችን ያወጣ ነበር። {1963}፣ ሌላዉ ተቋም በአዲስ አበባ ዩንበሪስቲ የተከፈተዉ የኢትዮዽያ ጥናት ኢኒስትቲዉት ሲሆን ይህ ጠቋም የኢትዮዽያ ጥናት ጆርናልን ማሳተም ጀምሯል። ከ1974ዓም አብዮት ፍንዳታ በሁዋላ በኢትዮጵያ ጥናት ተቋማት ላይና እንዲሁም በሕብረተሰቡ ላይ መሰረታዊ ለዉጦች ተካሂደዋል። የኢትዮዽያ ጥናት ኢኒስትቲዉት የአደረጃጅት ለወጥ አካሂዷል። {1976} ተቃሙ ከፍተኛ የሆኑ ታላላቅ ጥናቶችን ስለኢትዮጵያ ማካሄድ ጀምሮ። ለዚህም ተቋም የታወቁት የታሪክ ምሁረና ተመራማሪ ኢትዮጵስት ታደሰ ታምራት በሃላፊነት ተመድበዉ ነበር። የተቋሙ ዋና ሴንተር የነበረዉን የአማረኛ ቋንቋ አካዳሚ የኢትዮጵያ ቋንቋወች አካዳሚ በሚል በመተካት {1976} አያሌ ጥናቶችን በኢትዮጵያ በሚገኙ ብሔርና ብሔረሰቦች ፎልክሮች፣ ቋንቋወችና ባሕሎች ላይ ጥናቶችን አካሂዷል። እንዲሁም መዝገበ ቃላቶችንና የሳይንስና የቴክኖሎጅ ቴርሚኖችን እያሳተመ ያወጣል። አልፋቤት ለሌላቸዉ ቋንቋወች አልፋቤቶች እንዲቀረጡ ያደርጋል፣ለአላቸዉም እንዲሻሻሉ ጥናቶችን ያቀርባል። በዚህ ተቋም ዉስጥ የታወቁት የቋንቋ ምሁራን ፕሮፊሰሮች፣ አምሳሉ አክሊሉ፣ አሰፋ ገ/ማሪያም እና ሌሎችም ምሁራን በተቋሙ ይሰሩ ነበር። ሌላዉ ተቋም ታሪካዊ ሐዉልቶችንና ቅርሶችን ለመንከባከብና ለመጠበቅ የተቋቋመዉ የባሕልና የቅርሶች ጥናት መዕከል /ሴተር/ {1975} ነዉ። የኢትዮጵያ ጥናት በሌሎች የአዉሮፖ አገሮችም በኒዜርላንድና በስዉዘርላንድ ዩንበሪስቲወች ጥናቶችን ያካሂዳሉ። እንዲሁም የስራኤል የቴላቢብ ዩንበሪስቲም ስለኢትዮዽያ ጥናቶችን ያካሂዳል። ዓለም አቀፍ የኢትዮዽያ ጥናት ኢትዮጵስቶች ኮንፍረንስ የተካሄደባቸዉ አመታትና ሀገሮች/ከተማወች።

1ኛዉ ኮንፍረንስ በኢጣሊ ሮም 1959ዓም

2ኛዉ ኮንፍረንስ በኢንግሊዝ ማንችስተር 1963ዓም

3ኛዉ ኮንፍረንስ በኢትዮዽያ አዲስ አበባ 1966ዓም

4ኛዉ ኮንፍረንስ በኢጣሊ ሮም 1972ዓም

5ኛዉ ኮንፍረንስ በኒዘርላንድ ኒትሳ 1977ዓም

6ኛዉ ኮንፍረንስ በእዝራኤል ቴላአቢብ 1980ዓም

7ኛዉ ኮንፍረንስ በሱዲን ሉዋንዳ ዩንበሪስቲ 1982ዓም

8ኛዉ ኮንፍረንስ በኢትዮዽያ አዲስ አበባ 1984ዓም

9ኛዉ ኮንፍረንስ በራሽያ ሞስኮ 1986ዓም