Jump to content

ኩክ ደሴቶች

ከውክፔዲያ

ኩክ ደሴቶች
Kūki 'Āirani
Cook Islands

የኩክ ደሴቶች ሰንደቅ ዓላማ የኩክ ደሴቶች አርማ
ሰንደቅ ዓላማ አርማ
ብሔራዊ መዝሙር Te Atua Mou E
የኩክ ደሴቶችመገኛ
የኩክ ደሴቶችመገኛ
ዋና ከተማ ኣቫሩኣ
ብሔራዊ ቋንቋዎች እንግሊዝኛ
ኩክ ደሴቶች ማዖሪኛ
መንግሥት
{{{
ንግሥት

ጠቅላይ ሚኒስትር
 
ግርማዊት ንግሥት ኤልሳቤጥ ፪ኛ
ሄንሪ ፐና
የመሬት ስፋት
አጠቃላይ (ካሬ ኪ.ሜ.)
 
240
የሕዝብ ብዛት
የ2016 እ.ኤ.አ. ግምት
የ2011 እ.ኤ.አ. ቆጠራ
 
21,000
14,974
ገንዘብ የኒው ዚላንድ ዶላር
ኩክ ደሴቶች ዶላር
ሰዓት ክልል UTC –10
የስልክ መግቢያ +682
ከፍተኛ ደረጃ ዶሜን .ck

ኩክ ደሴቶች Cook Islands በፓሲፊክ ውቅያኖስ የሚገኝ የኒው ዚላንድ ራስ-ገዥ ደሴቶች አገር ነው።

ደሴቶቹ መጀመርያ በእስፓንያ መርከበኞች በ1587 ዓም ተዘገቡ። የክርስትና ሰባኪዎች ከ1813 ዓም ጀምሮ ደርሰው የኗሪዎቹ ብዛት የክርስትና ምዕመናን ሆነዋል። በ1880 ዓም የፈረንሳይ ቅኝ አገር እንዳይሆኑ ፈርተው በራሳቸው ልመና በዩናይትድ ኪንግደም ጥብቅና ሥር ገቡ፤ በ1893 ዓም ጥብቅናው ወደ ኒው ዚላንድ ተዛውሮ እስካሁን ድረስ ከኒው ዚላንድ ጋር ተባባሪነት አላቸው። ሕዝቡ ግን ምንጊዜም በተግባር ራስ ገዥ ሆነዋል።

ይፋዊ ቋንቋዎች እንግሊዝኛ እና የኩክ ደሴቶች ማዖሪኛ ናቸው፤ ፑካፑካኛ ደግሞ ይነገራል።

ትንሽ ኮኮነትፓፓያሎሚቡና፣ ወዘተ. ለአለም ገበያ ይመረታሉ። በባህላዊ ሥነ ጥበብ፣ የእንጨት እጅ ሥራዎች፣ የሽመና ዕቃዎች፣ የሽመና ባርኔጣ፣ ትርዒት የሚያሳይ ድሪቶ፣ ወዘተ. ይሠራሉ። ራግቢ ከሁሉ የሚወድ እስፖርት ጨዋታ ነው። ባህላዊ ጭፈራዎች አሉ።

በኩክ ደሴቶች አበሳሰል ስምንት-እግርዛጎል ለበስ፣ የአሳማ ግልገል፣ የፖሊኔዥያ አሮውሩትጎደሬ ይበላሉ። ለቅመሞች ዝንጅብል፣ ሎሚ፣ በሶብላነጭ ሽንኩርት፣ ኮኮነት ይጨመራሉ። በምግብ አሠራሮቹ መካከል፦

  • ሩካው - የገደሬ ቅጠል በኮኮነት ወጥና ሽንኩርት
  • ኢካ ማታ - ጥሬ አሣ በሎሚ ተዘፍዝፎ በኮኮነት ቅባት
  • ፖኬ - በሙዝና በኮኮነት ወተት ወይም በፓፓያ የሚሠራ ጣፋጭ

አሉ። የአምበሾክ፣ የብርቱካንና የማንጎ ጭማቂዎች ይጠጣሉ፣ እንዲሁም የኮኮነት ውሃቢራቡና የሚወደዱ መጠጦች ናቸው።