Jump to content

ውክፔዲያ:ታሪካዊ ማስታወሻዎች/ታኅሣሥ 1

ከውክፔዲያ

ታኅሣሥ ፩

  • ፲፰፻፷፩ ዓ/ም - በዓለም የመጀመሪያው የመንገድ ተሽከርካሪዎች መቆጣጠሪያ መብራት በእንግሊዝ ዋና ከተማ በለንደን ላይ የፓርላማ ሕንጻ (የዌስትሚንስተር ቤተ መንግሥት) ‘Palace of Westminster’ ፊት ለፊት ተተክሎ አገልግሎት ላይ ዋለ።
  • ፲፱፻፸፬ ዓ/ም - የብሪታንያቢ.ቢ.ሲ.አሜሪካ አሥራ አምሥት ግዛቶች ውስጥ ‘ሰዶማውያን’ን የሚያጠቃ ያልታወቀ አዲስ በሽታ እንደገባ እና በእነኚሁ ግዛቶች ውስጥ ሰባ አምሥት ሰዎች፥ በእንግሊዝ አገር ደግሞ አንድ ሰው በዚሁ በሽታ መሞታቸውን ዘገበ። ይሄ በሽታ በኋላ ኤይድስ የተባለው በሽታ ሲሆን ሠላሣ ዓመታት እንኳን ባልሞላ ጊዜ ውስት በዓለም ላይ ወደ ሃያ አራት ሚሊዮን የሚጠጉ ሰዎችን ሕይወት ወስዷል።
  • ፲፱፻፹፩ ዓ/ም -በቀድሞው የሶቪዬት ሕብረት ግዛት ውስጥ በአርሜኒያ ክልል ውስጥ በተከሰተው የምድር እንቅጥቅጥ አርባ አምሥት ሺህ ሰዎች ሲሞቱ ወደ ግማሽ ሚሊዮን የሚጠጉ ሰዎች ደግሞ መኖሪያ ቤታቸውን አጥተዋል። ስፒታክ የምትባል የሃያ አምሥት ሺህ ነዋሪዎች ከተማ በዚሁ እንቅጥቅጥ ፈጽማ ወድማለች።