ውክፔዲያ:ታሪካዊ ማስታወሻዎች/ነሐሴ 30
Appearance
ነሐሴ 30 ቀን: አስተማሮች ቀን በሕንደኬ (የራዳክሪሽናን ልደት)...
- ፬፻፪ ዓ/ም - ሮማ በንጉሥ አላሪክ በሚመሩት ቪዚጎቶች ተዘረፈች።
- ፲፮፻፵፩ ዓ/ም - በኢጣልያ ካስትሮ የሚባል ከተማ በሮማ ፓፓ ላይ አመጽ አድርጎ፡ የፓፓው ሠራዊት አጠፉት።
- ፲፮፻፶፰ ዓ/ም - ለሦስት ቀን እና ሦስት ሌሊት የጋየውና በሎንዶን ከተማ ፲ ሺህ ሕንጻዎችን ያወደመው “ታላቁ ቃጠሎ” በዚህ ዕለት ተነሣ።
- ፲፯፻፸፭ ዓ/ም - የአሜሪካ ነጻነት አብዮት ከእንግሊዝ ጋር በፓሪስ ውል ተጨረሰ።
- ፲፯፻፺ ዓ/ም - የአንድ ሳምንት የፈጀ የባሕር ውጊያ በእንግሊዝ አና በእስፓንያ መካከል ከቤሊዝ አጠገብ ጀመረ።
- ፲፯፻፺፪ ዓ/ም - የፈረንሳይ ንጉሠ ነገሥት ናፖሌዎን የማልታን ደሴት በጦር ኃይል ግዴታ ለታላቋ ብሪታንያ ለቀቀ።
- ፲፰፻፸፰ ዓ/ም - ከ፴ ዓመት ትግል በኋላ፣ የአፓቺ አለቃ ጀሮኒሞ በአሪዞና ግዛት እጁን ሰጠ።
- ፲፱፻፶፪ ዓ/ም - የኮንጎ ፕሬዚደንት ዮሴፍ ካዛቩቡ የአገሪቱን ጠቅላይ ሚኒስትር ፓትሪስ ሉሙምባ ከሥልጣናቸው ሽረው በቁም እሥራት ላይ አዋሏቸው።
- ፲፱፻፶፪ ዓ/ም - የግጥም ጠቢቡ ሌዎፖልድ ሴዳር ሴንግሆር በሴኔጋል የመጀመሪያ ፕሬዚደንት ሆእው ተመረጡ።
- ፲፱፻፶፪ ዓ/ም - ቦክሰኛው ሞሀመድ አሊ (የቀድሞው ካሲየስ ክሌይ) በሮማው የበጋ ኦሊምፒክ ውድድር በመለስተኛ ክብደት ወርቅ ተሸለመ።
- ፲፱፻፷፬ ዓ/ም - ሙኒክ ላይ በተካሄደው የበጋ ኦሊምፒክ ውድድር ላይ “ጥቁር መስከረም” ("Black September") የተባለ የፍልስጥኤም ሽብርተኛ ቡድን የእስራኤልን ተወዳዳሪዎችና አሰልጣኞች በአፈና ከያዘ በኋላ አሥራ አንዱን ገደላቸው።