ውክፔዲያ:ታሪካዊ ማስታወሻዎች/ጥቅምት 30
Appearance
- ፲፰፻፵፰ ዓ/ም - የሸዋ ንጉሥ ኃይለ መለኮት ሣህለ ሥላሴ በድንገተኛ ኅመም አርፈው በደብረ በግዕ ተቀበሩ።
- ፲፱፻፲፩ ዓ.ም. - የጀርመን ቄሳር ዳግማዊ ዊልሄልም ከዙፋናቸው እንደሚወርዱ በይፋ አሰታወቁ።
- ፲፱፻፴፩ ዓ.ም. - በጀርመን እና በአውስትሪያ አገሮች ናዚዎች የይሁዳውያን መቅደሳትና መደብሮችን በዝብዘው በእሳት አጋዩ። ይሄም ታሪካዊ ምዕራፍ “Kristallnacht” የመስተዋት መስበሪያ ምሽት በመባል ይታወቃል።
- ፲፱፻፶፰ ዓ.ም. - በሰሜን ምሥራቅ አሜሪካ ግዛቶችና በካናዳ ለአሥራ ሦስት ሰዐት ተኩል ያህል ጊዜ የኤሌክትሪክ ኃይል ተቋርጦ ስምንት መቶ ሺህ ሰዎች በኒው ዮርክ ውስጠ መሬት ባቡር ላይ ተደንቅረው አመሹ። ችግሩ በግምት የሃያ አምስት ሚሊዮን ሕዝቦችን ኑሮ አዛብቷል።
- ፲፱፻፷፫ ዓ.ም. - በሁለተኛው የዓለም ጦርነት የአገራቸውን አርበኞች የመሩ እና ታዋቂው የፖለቲካ ሰው፣ የፈረንሳይ ፕሬዚደንት ሻርል ደጎል በተወለዱ በ ሰባ ዘጠኝ ዓመታቸው አረፉ።
- ፲፱፻፹፪ ዓ.ም. - በኮሙኒስታዊ የምሥራቅ ጀርመን ሪፑብሊክ የበርሊን ግንብ ፈረሰ። አገሪቷም ዙሪያ ድንበሮቿን በመክፈት ሕዝቦቿ ወደምዕራብ በነፃ እንዲጓዙ አመቻቸች።