Jump to content

የኡጋሪት አልፋቤት

ከውክፔዲያ
የኡጋሪት ፊደላት

የኡጋሪት አልፋቤትኡጋሪት ከተማ፣ ሶርያ በጥንት ከ1400-1200 ዓክልበ. ገደማ የተጻፈ አልፋቤት (አብጃድ) ነበረ።

በወቅቱ የመላው ከነዓንጥንታዊ ግብጽመስጴጦምያአናቶሊያ ለኢንተርናሽናል ፖለቲካ ለመደበኛ ቋንቋ የተጠቀመው አካድኛ ነበረ። ይህን የፈርዖኖች 3 አመንሆተፕና የአኸናተን ደብዳቤዎች ወይም የአማርና ደብዳቤዎች (1369-1339 ዓክልበ. ግድም) ያሳየናል። አካድኛ የተጻፈበት ጽሕፈት በልዩ ውሻል ምሣሪያ ወይም ኩኔይፎርም በተባለ ጽሕፈት ይጻፍ ነበር። ነገር ግን ኩኔይፎርም የቻይና ጽሕፈትን በመምሰል ቃላት በብዙ ሺህ ቅርጾች ይጻፉ ነበር እንጂ እንደ አልፋቤት፣ አብጃድ ወይም አቡጊዳ አልነበረም።

ኡጋሪት ጽላቶች ላይ ኡጋሪትኛ የተባለውን ሴማዊ ቀበሌኛ ለመጻፍ የኡጋሪት ኩኔፎርም አልፋቤት በ1400 ዓክልበ. ያህል ፈጠሩ። የፊደላት ቅርጾች በውሻል ተሠርተው ሲሆን እንደ አካድኛ ኩኔፎርም ቢመስሉም፣ ቅርጾቹ ግን ከኩኔይፎርም ቃላት እንደ ደረሱ አይመስልም። ይልቁንም ምናልባት ቅርጾቹ እንደ ቅድመ-ሴማዊ ጽሕፈትቅድመ ከነዓናዊ ጽሕፈት ወይም ጌባል ጽሕፈት ፊደላት ለመምሰል ታሠቡ።

የጽሑፉ አቅጣጫ ከግራ ወደ ቀኝ ሄደ። 30 ፊደላት አሉ። አንዳንድ አናባቢዎች ከ«እ» በኋላ ብቻ (ወይም አ፣ ኢ፣ ኡ) ይጻፉ ነበር።

ለኡጋሪት ፊደላት ቅደም-ተከተል ሁለት አይነቶች በሰነዶቹ ተገኝተዋል። አንዱ እንደ ፊንቄ አልፋቤት ወይም እንደ ግዕዝ «አ ቡ ጊ ዳ» ተራ «ስሜን ሴማዊ ቅደም ተከተል» ተብሏል። ሌላው ቅደም-ተከተል ግን እንደ «ደቡብ ሴማዊ ቅደም-ተከተል» ወይም እንደ «ሀ ለ ሐ መ» ያህል ይመስላል።

«ስሜን ሴማዊ ቅደም ተከተል»

ʾa b g d h w z y k š l m n s ʿ p q r ġ t ʾi ʾu s2
א ב ג ד ה ו ז ח ט י כ ל מ נ ס ע פ צ ק ר ש ת

«ደቡብ ሴማዊ ቅደም ተከተል»

h l m q w š r t s k n b ś p ʾ ʿ g d ġ z y
ה ל ח מ ק ו ר ת ס כ נ ב פ א ע ג ד ט ז י ש צ
የኡጋሪት ፊደላት[1]
ፊደል በላቲን ጽሕፈት አማርኛ ዕብራይስጥ አረብኛ
𐎀 ʾa א أ
𐎁 b ב ب
𐎂 g ג ج
𐎃 خ
𐎄 d ד د
𐎅 h ה ه
𐎆 w ו و
𐎇 z ז ز
𐎈 ח ح
𐎉 ט ط
𐎊 y י ي
𐎋 k כ ك
𐎌 š ש ش
𐎍 l ל ل
𐎎 m מ م
𐎏 ذ
𐎐 n נ ن
𐎑 ظ
𐎒 s ס س
𐎓 ʿ  ע ع
𐎔 p פ ف
𐎕 צ ص
𐎖 q ק ق
𐎗 r ר ر
𐎘 ث
𐎙 ġ غ
𐎚 t ת ت
𐎛 ʾi ئ
𐎜 ʾu ؤ
𐎝 s2
𐎟 ቃል መለያ (፡)
  1. ^ Daniels, Peter T.; Bright, William, eds (1996). "Epigraphic Semitic Scripts". The World's Writing Systems. Oxford University Press, Inc. p. 92. ISBN 978-0-19-507993-7.