የካቲት ፮
Appearance
የካቲት ፮፣ በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የዓመቱ ፻፶፮ ኛው ዕለት ሲሆን፤ የበጋ ወቅት ፵፩ ኛው ቀን ነው። ከዚህ ዕለት በኋላ እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ በዘመነ ሉቃስ ፪፻፲ ዕለታት ሲቀሩ በዘመነ ዮሐንስ፣ ዘመነ ማቴዎስ እና ዘመነ ማርቆስ ደግሞ ፪፻፱ ቀናት ይቀራሉ።
- ፲፭፻፶፭ ዓ/ም - የ ፲፪ ዓመቱ ልጅ ማር (ጌታ) ሠርፀ ድንግል፣ አባታቸው አጼ ሚናስ ሲሞቱ በስመ መንግሥት መለክ ሰገድ ተብለው ነገሡ። አጼ ሠርፀ ድንግል የመንግሥት ሥራቸውን የሚሠሩት በእናታቸው በእቴጌ አድማስ ሰገድ ሥሉስ ኃይላ አማካይነት ነበር።
- ፲፭፻፶፭ ዓ/ም ኢትዮጵያን ከአራት ዓመታት በንጉሥነት የመሯት አፄ ሚናስ (ስመ መንግሥት፣ ቀዳማዊ አድማስ ሰገድ) በዕለተ እሑድ አረፉ፡፡ አጼ ሚናስ የአጼ ገላውዴዎስ ወንድምና የአጼ ልብነ ድንግል ልጅ ነበሩ።
- መርስዔ ኀዘን ወልድ ቂርቆስ፤ ዕለታዊ የታሪክ ድርጊት “የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን የመጀመሪያው ፓትረያርክ” (፲፱፻፶፩ ዓ/ም)፣
የኢትዮጵያ ወራት | |
---|---|
መስከረም - ጥቅምት - ኅዳር - ታኅሣሥ - ጥር - የካቲት - መጋቢት - ሚያዝያ - ግንቦት - ሰኔ - ሐምሌ - ነሐሴ - ጳጉሜ |