ጥቅምት ፳፱
Appearance
ጥቅምት ፳፱ ቀን በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የዓመቱ ፶፱ነኛው እና የመፀው ፴፬ተኛው ዕለት ነው። ከዚህ ዕለት በኋላ እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ በዘመነ ሉቃስ ፫፻፯ ቀናት ሲቀሩ፣ በዘመነ ዮሐንስ፤ ዘመነ ማቴዎስ እና ዘመነ ማርቆስ ደግሞ ፫፻፮ ቀናት ይቀራሉ።
- ፲፰፻፹፪ ዓ.ም. - በአሜሪካ ሰሜን ምዕራብ የሚገኘውና ስሙ ከስፓኝኛ ቋንቋ ሞንታኛ (ተራራ) የመጣው ሞንታና የተባለው ክልል የአሜሪካ ሕብረትን በመቀላቀል አርባ አንደኛው ክፍለ ግዛት ሆነ።
- ፲፱፻፲፮ ዓ.ም. - በጀርመን ከተማ በሚዩኒክ የቢራ አዳራሽ ውስጥ የወደፊቱ መሪና የናዚ ቡድን ሊቀ መንበር አዶልፍ ሂትለር ውጤቱ ያልተሳካ የመፈንቅለ መንግሥት ሙከራውን አንቀሳቀሰ።
- ፲፱፻፶፫ ዓ.ም. - በአሜሪካ የፕሬዚደንታዊ ውድድር በጊዜው ምክትል ፕሬዚደንት የነበሩትን ሪቻርድ ኒክሰንን በማሸነፍ ጆን ፊትዝጄራልድ ኬኔዲ የአገሪቱ ሠላሳ አምስተኛው ፕሬዚደንት ሆነው ተመረጡ።
- ፲፱፻፷፬ ዓ/ም - የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት መንግሥት የአድአን አካባቢ በዘመናዊ ግብርና ለማልማት የሚያስችል፣ በ፵ ዓመት የሚከፈል የሦስት ተሩብ ሚሊዮን ብር (E$3.25 million) ብድር ውል ከአሜሪካ መንግሥት ጋር ተፈራረመ።
- (እንግሊዝኛ) P.R.O., FCO 31/1118 - ETHIOPIA: ANNUAL REVIEW FOR 1971
- (እንግሊዝኛ) http://www.nytimes.com/learning/general/onthisday/20081105.html
የኢትዮጵያ ወራት | |
---|---|
መስከረም - ጥቅምት - ኅዳር - ታኅሣሥ - ጥር - የካቲት - መጋቢት - ሚያዝያ - ግንቦት - ሰኔ - ሐምሌ - ነሐሴ - ጳጉሜ |