ሚያዝያ ፩
Appearance
ሚያዝያ ፩፣ በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የዓመቱ ፪፻፲፩ኛው ዕለት ሲሆን፤ የፀደይ (በልግ)ወቅት ፮ኛው ቀን ነው። ከዚህ ዕለት በኋላ እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ በዘመነ ሉቃስ ፻፶፭ ዕለታት ሲቀሩ በዘመነ ዮሐንስ፣ ዘመነ ማቴዎስ እና ዘመነ ማርቆስ ደግሞ ፻፶፬ ቀናት ይቀራሉ።
- ፲፱፻፶፩ ዓ/ም - የአሜሪካ የጠፈር በረራና ምርመራ ባለሥልጣን (NASA the National Aeronautics and Space Administration) ’መርኩሪ’ በሚባለው የአገሪቱ የመጀመሪያ የሰው አሳፋሪ መንኮራኩር መርሐ-ግብር የሚሳተፉትን ጠፈርተኞች ለዓለም አስተዋወቀ። እነርሱም፦ ስኮት ካርፔንተር፣ ጎርደን ኩፐር፣ ጆን ግሌን፣ ቨርጅል ግሪሰም፣ ዎልተር ስኪራ፣ አላን ሼፈርድ እና ዶናልድ ስሌይተን ነበሩ።
- ፲፱፻፶፪ ዓ/ም - ሁለት የብሪታንያ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት፤ ብራያን ሃሪሶን (Brian Harrison) እና ጄምስ ስሌተር (James Slater) ለጉብኝት አዲስ አበባ ገቡ። ከንጉሠ ነገሥቱም ጋር ተገናኝተው ተወያይተዋል።
- ፲፱፻፷ ዓ/ም - የጥቁር አሜሪካዊው የሰብዓዊ መብት መሪ የዶክቶር ማርቲን ሉተር ኪንግ የቀብር ሥነ-ሥርዓት በተወለዱበት ከተማ በአትላንታ ተከናወነ። የጆርጂያ ክፍለ-ሀገር ገዥ ሌስተር ማደክስ ዶክቶር ኪንግ የ’ሀገር ጠላት’ ነበሩ በሚል አቋም እቀብሩ ላይ አልሳተፍም ብለው መቅረታቸው ሳይበቃ ለሟቹም ክብር የክፍለ ሀገሩን መንግሥታዊ ቢሮዎች እንደማይዘጉ አስታወቁ።
- ፲፱፻፷፭ ዓ/ም - የቡልጋሪያ ባለ ሥልጣናት ከኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት መንግሥት ጋር በሁለቱ አገሮች መኻል የባህላዊ ግንኙነት እና ልውውጥ ለመወያየት አዲስ አበባ ገቡ።
- ፲፱፻፷፮ ዓ/ም - በጠቅላይ ሚኒስትር እንዳልካቸው መኮንን የሚመራው የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት መንግሥት ሕገ መንግሥታዊ የዘውድ ሥርዓትን ለመመሥረት የታዘዘውን አጥኒ ሸንጎ በማንኛውም ጉዳይ እንደሚተባበረውና እንደሚረዳው አረጋገጠ። አያይዞም መሬትን በተመለከተ በአገሪቱ ውስጥ ማንም ሰው ለማልማት ከሚችለው በላይ መሬት መያዝ እንዳይችልና ለወደፊት ከአርሶ አደሮች በስተቀር የእርሻ መሬት ለማንም እንደማይሰጥ ለማድረግ የሚያስችል ሕግ እንደሚወጣ አስታወቀ።
- (እንግሊዝኛ)http://news.bbc.co.uk/onthisday/hi/dates/stories/april/9/newsid_2463000/2463927.stm
- (እንግሊዝኛ) http://ourgeorgiahistory.com/ogh/Martin_Luther_King Archived ጁን 12, 2011 at the Wayback Machine
- (እንግሊዝኛ) http://www.thepeoplehistory.com/april9th.html Archived ኦገስት 13, 2011 at the Wayback Machine
- (እንግሊዝኛ) P.R.O., FO 371/154836 - Annual Report from Ethiopia for 1960
- (እንግሊዝኛ) P.R.O., FCO 371/1660 - ANNUAL REVIEW FOR ETHIOPIA FOR 1973
- (እንግሊዝኛ) P.R.O., FCO 371/1829 - ANNUAL REVIEW FOR ETHIOPIA FOR 1974
የኢትዮጵያ ወራት | |
---|---|
መስከረም - ጥቅምት - ኅዳር - ታኅሣሥ - ጥር - የካቲት - መጋቢት - ሚያዝያ - ግንቦት - ሰኔ - ሐምሌ - ነሐሴ - ጳጉሜ |