Jump to content

ሚያዝያ ፳፯

ከውክፔዲያ

ሚያዝያ ፳፯

ኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የዓመቱ ፪፻፴፯ ኛው ዕለት ነው። ከዚህ ዕለት በኋላ እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ፣ በዘመነ ዮሐንስ ፻፳፱ ዕለታት ሲቀሩ፤ በዘመነ ማቴዎስማርቆስ እና ሉቃስ ደግሞ ፻፳፰ ዕለታት ይቀራሉ።

ይህች ቀን በአገራችን ታሪክ ሁለት የሐዘንና የደስታ ቀኖችን ትዘክራለች። ሚያዝያ ፳፯ ቀን ፲፱፻፳፰ ዓ/ም የፋሽሽት ኢጣልያ ጄነራል ባዶሊዮ በጊዚያዊ ድል አድራጊነት አዲስ አበባን ከቁጥጥሩ ሥር ያደረገበትና ነጻነታችንን ያጣንበት ዕለት ሲሆን ልክ በአምስት ዓመቱ በ ፲፱፻፴፫ ዓ/ም ደግሞ ንጉሠ ነገሥቱ በአርበኞች አባት እናቶቻችን ትግል፣ በእንግሊዝ እና ግብረአበሮቿ ዕርዳታ በድል አድራጊነት አዲስ አበባ የገቡበት ዕለት ነው።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንም ይሄንን ዕለት ከነጻነት ቀን በተጨማሪ በመድሃኔ ዓለም ኢየሱስ ክርስቶስ ስም ትዘክረዋለች።


  • ፲፱፻፶፮ ዓ/ም የአውሮፓ ሸንጎ (The Council of Europe) ይሄንን ዕለት “የአውሮፓ ቀን” ብሎ ሰይሞታል
  • ፲፱፻፷፮ ዓ/ም - ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ በብሔራዊ የድል በዐል ላይ ባደረጉት ንግግር፣ በአገሪቱ የተለኮሰውን የአብዮት እሳት በተመለከተ ከውጭ የሚራገብ ነቀርሳ እንደሆነና ኢትዮጵያውያን በሙሉ በሕብረት እንዲቃወሙት ጥሪያቸውን አሰሙ።


የኢትዮጵያ ወራት
መስከረም - ጥቅምት - ኅዳር - ታኅሣሥ - ጥር - የካቲት - መጋቢት - ሚያዝያ - ግንቦት - ሰኔ - ሐምሌ - ነሐሴ - ጳጉሜ