ሚያዝያ ፳፱
Appearance
(ከሚያዝያ 29 የተዛወረ)
ሚያዝያ ፳፱ በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የዓመቱ ፪፻፴፱ኛው ዕለት ሲሆን፤ የፀደይ (በልግ)ወቅት ፴፬ኛው ቀን ነው። ከዚህ ዕለት በኋላ እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ በዘመነ ሉቃስ ፻፳፯ ዕለታት ሲቀሩ በዘመነ ዮሐንስ፣ ዘመነ ማቴዎስ እና ዘመነ ማርቆስ ደግሞ ፻፳፮ ቀናት ይቀራሉ።
- ፲፰፻፹፩ ዓ/ም - በፓሪስ ከተማ ለስድስት ወራት የተካሄደው ዓለም አቀፋዊ አውደ ርዕይ በዚህ ዕለት ተመርቆ ሲከፈት ግንባታው ገና ያላለቀውን የ’አፌል ቅስት’ (La Tour Eiffel) ሕዝብ እስከ ሁለተኛው ፎቅ ድረስ እየወጣ መጎብኘት ጀመረ።
- ፲፱፻፯ ዓ.ም. - በመጀመሪያው የዓለም ጦርነት የንምሣ ባሕር-ሰመጥ የጦር መርከብ፣ ሉሲታኒያ የተባለችውን የእንግሊዝ መርከብ በአየርላንድ አጠገብ አጥቅታ ስታሰምጥ ፩ሺ፩መቶ፺፰ ተሣፋሪዎች ሞቱ።
- ፲፱፻፴፯ ዓ/ም - ንምሣ በአውሮፓ ለስድስት ዓመታት በተካሄደው ሁለተኛው የዓለም ጦርነት ተሸናፊነቷን አምና የምርኮኛ ውል ፈረመች።
የኢትዮጵያ ወራት | |
---|---|
መስከረም - ጥቅምት - ኅዳር - ታኅሣሥ - ጥር - የካቲት - መጋቢት - ሚያዝያ - ግንቦት - ሰኔ - ሐምሌ - ነሐሴ - ጳጉሜ |
ጅምር! ይህ አጭር ጽሑፍ መሠረት ወይም መዋቅር ነው። አሁን ሊያስፋፉት ይችላሉ! |