ታኅሣሥ ፲፯
Appearance
ታኅሣሥ ፲፯ ቀን በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የዓመቱ ፻፯ተኛው እና የመፀው ወቅት ፹፪ተኛው ቀን ነው። ከዚህ ዕለት በኋላ እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ፣ በ ዘመነ ሉቃስ ፪፻፶፱ ቀናት በ ዘመነ ዮሐንስ፤ በ ዘመነ ማቴዎስ፤ እና በ ዘመነ ማርቆስ ደግሞ ፪፻፶፰ ቀናት ይቀራሉ።
- ፲፰፻፺፮ ዓ/ም - ዳግማዊ ዓፄ ምኒልክ ሊጎበኛቸው ከመጣው የአሜሪካ ኅብረት መንግሥት ወኪል 'ሮበርት ፒ ስኪነር' (Robert P. Skinner) ጋር የንግድ ውል ተፈራረሙ። ይኼም ድርጊት በኢትዮጵያ እና በአሜሪካ ኅብረት የመጀመሪያው የ'ዲፕሎማሲ' መክፈቻ ግንኙነት ነው።
- ፲፱፻፹ ዓ/ም - ኢትዮጵያ ባዘጋጀችው የምሥራቅና መካከለኛው አፍሪቃ የእግር ኳስ ዋንጫ (ሴካፋ) ዚምባብዌን በፍጹም ቅጣት ምት በማሸነፍ፣ ለመጀመሪያ ጊዜ ዋንጫውን ከፍ ያደረገችበት ነበር፡፡ ዋንጫውን ለብሔራዊ ቡድኑ አምበል ገብረ መድኅን ኃይሌ የሰጡት የኢትዮጵያ ሕዝባዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ (ኢሕዲሪ) ፕሬዚዳንት፣ መንግሥቱ ኃይለ ማርያም ሲሆኑ፣ የተሰማቸውን ደስታ የገለጹት ፻ ሺሕ ተመልካች የሚይዝ ስታዲየም ለመሥራት ቃል በመግባት ነበር፡፡
- ፲፱፻፺፯ ዓ/ም - በሕንድ ውቅያኖስ ሥር የተነሳው የመሬት እንቅጥቅጥ ያስከተለው ኃይለኛ የባሕር ሞገድ በስሪ ላንካ፣ ሕንድ፣ ኢንዶኔዚያ፣ ታይላንድ እና ማሌዚያ አገራት ከ፪መቶ ፴ሺ በላይ የሚቆጠሩ ሰዎችን ሕይወት አጥፍቷል።
- ፳፻ ዓ/ም - በኬንያ የፕሬዚደንታዊ ምርጫ ምዋይ ኪባኪ አሸናፊ ናቸው ተብሎ ሲታወጅ በመላ አገሪቱ የተከተለው የተቃውሞ ረብሻ በአገሪቱ ለተከሰቱት ፖለቲካዊ፤ ምጣኔ-ኃብት እና ሰብዓዊ ነውጦች ዋና መንስዔ ሆኗል።
- ሪፖርተር
የኢትዮጵያ ወራት | |
---|---|
መስከረም - ጥቅምት - ኅዳር - ታኅሣሥ - ጥር - የካቲት - መጋቢት - ሚያዝያ - ግንቦት - ሰኔ - ሐምሌ - ነሐሴ - ጳጉሜ |