ኅዳር ፲፯
Appearance
ኅዳር ፲፯ ቀን በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የዓመቱ ፸፯ኛ ቀን ነው። ከዚህ ዕለት በኋላ እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ፣ በ ዘመነ ሉቃስ ፪፻፹፱ ቀናት በ ዘመነ ዮሐንስ፤ በ ዘመነ ማቴዎስ፤ እና በ ዘመነ ማርቆስ ደግሞ ፪፻፹፰ ቀናት ይቀራሉ።
- ፲፯፻፹፪ ዓ.ም. - የአሜሪካን ሕገ መንግሥት መቋቋም በማስታወስ እግዚአብሔርን ማመስገኛ ብሔራዊ በዓል በፕሬዚደንቱ ጆርጅ ዋሽንግተን አሳሳቢነት በኮንግረስ የጸደቀ ህግ ተደነገገ።
- ፲፰፻፸፱ ዓ.ም - የአዲስ አበባ ከተማ በዳግማዊ ምኒልክና እቴጌ ጣይቱ በፍል-ውሐ፣ ንጉሥ ሣህለ ሥላሴ አጥር አሳጠረውበት በነበረው ሥፍራ አካቢብ ላይ ተመሥርታ በዚሁ ዕለት አዲስ አበባ ተብላ ተሠየመች።
- ፲፱፻፴፬ ዓ.ም. - የአሜሪካ ፕሬዚደንት ፍራንክሊን ዲ ሩዝቬልት በአውሮፓውያን አቆጣጠር የኅዳር ወር አራተኛው ሐሙስ እግዚአብሔርን ማመስገኛ ብሔራዊ በዓል እንዲሆን የሚያስገድደውን ህግ ፈርሙ።
የኢትዮጵያ ወራት | |
---|---|
መስከረም - ጥቅምት - ኅዳር - ታኅሣሥ - ጥር - የካቲት - መጋቢት - ሚያዝያ - ግንቦት - ሰኔ - ሐምሌ - ነሐሴ - ጳጉሜ |