የአሜሪካ ፕሬዚዳንት
Appearance
የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ከአሜሪካ መንግሥት 3ቱ ቅርንጫፎች (ሕግ አውጪው፣ አስፈጻሚው፣ ችሎታዊው) መሀል የ2ኛው ወይም የአስፈጻሚው ቅርንጫፍ ዋና ባለሥልጣን ናቸው።
የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ዝርዝር ከ1929 እ.ኤ.አ. እስከ 2001 እ.ኤ.አ.፦
[ለማስተካከል | ኮድ አርም]ዋና መጣጥፍ፦ የአሜሪካ ፕሬዝዳንቶች ዝርዝር
- ሄርበርት ሁቨር - 1929-1933 እ.ኤ.አ.
- ፍራንክሊን ሮዘቨልት - 1933-1945 እ.ኤ.አ.
- (ፍራንክሊን ሮዘቨልት 4 ጊዜ ተመርጠው ከሁሉ የረዘመ ዘመን ነበራቸው። ከዚህ ቀጥሎ በሕዝቡ ድምጽ ብዛት፣ ማንም ፕሬዚዳንት ከ2 ጊዜ በላይ እንዳይመረጥ የአሜሪካ ሕገ መንግሥት 22ኛ ማሻሻያ አንቀጽ ጸና።)
- ሃሪ ትሩመን (1945-1953 እ.ኤ.አ.)
- ድዋይት አይዘንሃወር (1953-1961 እ.ኤ.አ.)
- ጆን ኤፍ ኬኔዲ (1961-1963 እ.ኤ.አ.)
- (ኬኔዲ አንድ ሙሉ ዘመን ሳይጨርስ ተገደለና ሊንደን ጆንሶን ዘመኑን የጨረሰው ነበር።)
- ሊንደን ጆንሰን (1963-1969 እ.ኤ.አ.)
- ሪቻርድ ኒክሰን (1969-1974 እ.ኤ.አ.)
- ጄራልድ ፎርድ (1974-1977 እ.ኤ.አ.)
- (ጄራልድ ፎርድ መቸም አልተመረጠም። ፕሬዚዳንት የሆነ በምርጫ ሳይሆን፣ ኒክሰን ማዕረጉን ስለ ተወ ነበር።)
- ጂሚ ካርተር (1977-1981 እ.ኤ.አ.)
- ሮናልድ ሬገን (1981-1989 እ.ኤ.አ.)
- ጆርጅ ኤች ቡሽ (1989-1993 እ.ኤ.አ.)
- ቢል ክሊንተን (1993-2001 እ.ኤ.አ.)
- ጆርጅ ደብሊዩ ቡሽ (2001 እ.ኤ.አ.-2009 እ.ኤ.አ.)
- ባራክ ኦባማ (2009 እ.ኤ.አ.- 2017 እ.ኤ.አ.)
- ዶናልድ ጆን ትራምፕ (2017 እ.ኤ.አ.- 2021 እ.ኤ.አ.)
- ጆ ባይድን (2021 እ.ኤ.አ. -)