የካቲት ፲፫
Appearance
(ከየካቲት 13 የተዛወረ)
የካቲት ፲፫፣ በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የዓመቱ ፻፷፫ ኛው ዕለት ሲሆን፤ የበጋ ወቅት ፵፰ ኛው ቀን ነው። ከዚህ ዕለት በኋላ እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ በዘመነ ሉቃስ ፪፻፫ ዕለታት ሲቀሩ በዘመነ ዮሐንስ፣ ዘመነ ማቴዎስ እና ዘመነ ማርቆስ ደግሞ ፪፻፪ ቀናት ይቀራሉ።
- ፲፭፻፴፭ ዓ/ም - በዕለተ ረቡዕ አህመድ ግራኝ ወገራ ላይ የንጉሥ ገላውዴዎስን ሠራዊት ገጥሞ በቡርቱጋል ነፍጥ ተመትቶ አህመድ ግራኝ ሲሞት የተረፈው ሠራዊቱ ተሸንፎ ኮበለለ።
- ፲፱፻፷፮ ዓ/ም - በኢትዮጵያ በፈነዳው አብዮት፣ የወጥቶ-እብስ ሠራተኞት የሦስት ቀን አድማቸውን ጀመሩ። በአዲስ አበባ በየቀበሌው እና በየመንገዱ የሚካሄደው ሽብር ቀጥሎ ዋለ።
- ፲፱፻፷፮ ዓ/ም - የአፍሪቃ፤ የካሪቢያን እና የሰላማዊ ውቅያኖስ አገሮች የንግድ ሚኒስቴሮች ከአውሮፓ የ ኤኮኖሚክ ኅብረት ጋር የንግድ ግንኙነትን ለማጠንከር አዲስ አበባ ላይ ስብሰባቸውን ጀመሩ።
- ፲፯፻፰ ዓ/ም - ንጉሥ ዓፄ ዮስጦስ አርፈው እራሳቸው ባሠሩት በጎንደርልደታ ማርያም ቤተ ክርስቲያን ተቀበሩ። በህመም ምክንያት ሞቱ ቢባልም፣ በነፍሰ ገዳይ እጅ ታንቀው እንደሞቱ በሰፊው ይታመናል።
- መርስዔ ኀዘን ወልድ ቂርቆስ፤ ዕለታዊ የታሪክ ድርጊት “የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን የመጀመሪያው ፓትረያርክ” (፲፱፻፶፩ ዓ/ም)፣
- (እንግሊዝኛ) P.R.O., FCO 371/1660
- (እንግሊዝኛ) P.R.O., FCO 371/1829
የኢትዮጵያ ወራት | |
---|---|
መስከረም - ጥቅምት - ኅዳር - ታኅሣሥ - ጥር - የካቲት - መጋቢት - ሚያዝያ - ግንቦት - ሰኔ - ሐምሌ - ነሐሴ - ጳጉሜ |