የካቲት ፬
Appearance
(ከየካቲት 4 የተዛወረ)
የካቲት ፬፣ በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የዓመቱ ፻፶፬ ኛው ዕለት ሲሆን፤ የበጋ ወቅት ፴፱ ኛው ቀን ነው። ከዚህ ዕለት በኋላ እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ በዘመነ ሉቃስ ፪፻፲፪ ዕለታት ሲቀሩ በዘመነ ዮሐንስ፣ ዘመነ ማቴዎስ እና ዘመነ ማርቆስ ደግሞ ፪፻፲፩ ቀናት ይቀራሉ።
- ፲፱፻፱ ዓ/ም - ንግሥት ዘውዲቱ፣ "ግርማዊት ዘውዲቱ፣ ንግሥተ ነገሥት ዘኢትዮጵያ" ተብለው በመናገሻ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን በሊቀ ጳጳሱ በአቡነ ማቴዎስ እጅ ቅብዐ መንግስት ተቀብተው የንጉሠ ነገሥቱን ዘውድ ጫኑ።
- ፲፱፻፶፭ ዓ/ም - የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት መንግሥት በኢራቅ ወታደራዊ መፈንቅለ መንግሥት ለተተካው የኮሎኔል አብዱል ሳላም አሪፍ መንግሥት ሕጋዊ ዕውቀት መስጠቱን አስታወቀ።
- ፲፱፻፲ ዓ/ም - «ብርሃን ዘ ኢትዮጵያ » በሚል ቅፅል ስም የሚታወቁት የዳግማዊ ምኒልክ ባለቤት፣ እቴጌ ጣይቱ ብጡል አረፉ። ሥርዓተ ቀብራቸውም በእንጦጦ መንበረ ፀሓይ ማርያም ቤተ ክርስቲያን ተፈጸመ። በኋላ ግን አጽማቸው ተነስቶ ንግሥት ነገሥታት ዘውዲቱ ለአባታቸው ዳግማዊ ምኒልክ አጽም ማሣረፊያ በተሠራው የታዕካ ነገሥት በዓታ ቤተ ክርስቲያን ተቀብሯል።
- መርስዔ ኀዘን ወልድ ቂርቆስ፤ “የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን የመጀመሪያው ፓትረያርክ” (፲፱፻፶፩ ዓ/ም)፣ ዕለታዊ የታሪክ ድርጊት
- (እንግሊዝኛ) P.R.O.፣ FO 371/178551 Annual Review of 1963
- (እንግሊዝኛ) Ibid. ፤ FCO 371/1829 Annual Review of 1974
የኢትዮጵያ ወራት | |
---|---|
መስከረም - ጥቅምት - ኅዳር - ታኅሣሥ - ጥር - የካቲት - መጋቢት - ሚያዝያ - ግንቦት - ሰኔ - ሐምሌ - ነሐሴ - ጳጉሜ |