የ2014 እ.ኤ.አ. ፊፋ የዓለም ዋንጫ
የ2014 እ.ኤ.አ. ፊፋ የዓለም ዋንጫ |
|
---|---|
ይፋዊ ምልክት
|
|
የውድድሩ ዝርዝር | |
አስተናጋጅ | ![]() |
ቀናት | ከሰኔ ፭ እስከ ሐምሌ ፮ ቀን |
ቡድኖች | ፴፪ (ከ፭ ኮንፌዴሬሽኖች) |
ቦታ(ዎች) | ፲፪ ስታዲየሞች (በ፲፪ ከተማዎች) |
← ![]() ![]() |
የ2014 እ.ኤ.አ. ፊፋ የዓለም ዋንጫ ፳ኛው የፊፋ የዓለም ዋንጫ ሲሆን ከሰኔ ፭ እስከ ሐምሌ ፮ ቀን ፳፻፪ ዓ.ም. በብራዚል ይካሄዳል።[1] ብራዚል ይህን ውድድር ስታዘጋጅ ይሄ ሁለተኛ ጊዜዋ ነው። ፊፋ የ2014 እ.ኤ.አ. ውድድር በደቡብ አሜሪካ እንደሚካሄድ በ2007 እ.ኤ.አ. ካወጀ በኋላ ብራዚል ያለማንም ተቀናቃኝ አዘጋጅ አገር ሆና ተመርጣለች።
የ፴፩ አገራት ብሔራዊ ቡድኖች ከጁን 2011 እ.ኤ.አ. ጀምሮ የተካሄዱ የማጣሪያ ውድድሮችን በማለፍ ከብራዚል ጋር በመጨረሻው ውድድር ላይ ለመሳተፍ በቅተዋል። በጠቅላላው ፷፬ ጨዋታዎች በ፲፪ ከተማዎች ውስጥ በሚገኙ አዲስ የተገነቡ ወይም የተሻሻሉ ስታዲየሞች ይከናወናሉ። በዓለም ዋንጫ ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ የጎል ላይን ቴክኖሎጂ በጥቅም ላይ ውሏል።[2]
በ1930 እ.ኤ.አ. ከተካሄደው የመጀመሪያው የዓለም ዋንጫ ጀምሮ ሁሉም የዓለም ዋንጫ ሻምፕዮን አገራት (ብራዚል፣ አርጀንቲና፣ እንግሊዝ፣ ፈረንሣይ፣ ጀርመን[ማስታወሻ 1]፣ ኢጣልያ፣ እስፓንያ እና ኡራጓይ) በዚህ ውድድር ውስጥ ተሳታፊ ናቸው። ከዚህ በፊት በደቡብ አሜሪካ የተዘጋጁትን ዋንጫዎች እንዳለ የወሰዱት የደቡብ አሜሪካ ቡድኖች ናቸው።[3]
ተሳታፊ አገራት እና ዳኛዎች[ለማስተካከል | ኮድ አርም]
ማጣሪያ[ለማስተካከል | ኮድ አርም]
ከጁን 2011 እስከ ኖቬምበር 2013 እ.ኤ.አ. የተካሄዱትን የማጣሪያ ጨዋታዎች ያለፉት አገራት ከውድድሩ በፊት ከያዙት ደረጃ ጋር ተዘርዝረዋል። ከነዚህ ውስጥ ቦስኒያና ሄርጸጎቪና ብቻ ከዚህ በፊት በዓለም ዋንጫ አልተሳተፈችም።[4][ማስታወሻ 2]
ኤ.ኤፍ.ሲ. ካፍ ኦ.ኤፍ.ሲ.
|
ኮንካካፍ ኮንሜቦል |
ዩኤፋ |
የምድብ ድልድል ዕጣ አወጣጥ[ለማስተካከል | ኮድ አርም]
፴፪ቱ ተሳታፊ አገራት በአራት በ፬ ቋቶች ተደራጅተዋል። በፊፋ የብቃት ደረጃ ላይ የሚገኙት ምርጥ ፯ ቡድኖች ብራዚል ጨምረው በዘር ቋት (seeded pot) ውስጥ ተመድበዋል።[5] ቀሪዎቹ ቡድኖች በተቻለ መጠን ከተለያዩ ኮንፌዴሬሽኖች እንዲወጣጡ (ማለትም በአንድ ምድብ ውስጥ የሚገኙ አገራት በመልከዓምድር የተራራቁ እንዲሆን) በማድረግ በሌሎቹ ፫ ቋቶች ተመድበዋል።[6][7] የመደብ ድልድል ሥነ ስርዓቱ ኅዳር ፳፯ ቀን ፳፻፮ ዓ.ም. ብራዚል በሚገኘው ኮስታ ዶ ሳዊፒ ሪዞርት ተካሄዷል።[8]
ቡድኖች[ለማስተካከል | ኮድ አርም]
ዋና መጣጥፍ፦ የ2014 እ.ኤ.አ. ፊፋ የዓለም ዋንጫ ቡድኖች
እንድ 2010 እ.ኤ.አ. ውድድር እያንዳንዱ ቡድን ፳፫ ተጫዋቾች ሲኖሩት ከነዚህም ውስጥ ፫ቱ ግብ ጠባቂ መሆን አለባቸው። እያንዳንዱ ብሔራዊ የእግር ኳስ ማህበር የሚያሰልፋቸውን ፳፫ ተጫዋቾች ውድድሩ ከመጀመሩ ፲ ቀናት በፊት ማሳወቅ ነበረበት።[9]
ቡድኖቹ ከፍተኛ ጉዳት የደረሰበት ተጫዋች ካጋጠማቸው ከመጀመሪያ ግጥሚያቸው 24 ሰዓት በፊት ድረስ መለወጥ ይችላሉ።[9]
ዳኛዎች[ለማስተካከል | ኮድ አርም]
የፊፋ ዳኛዎች ኮሚቴ በጥር ፮ ቀን ፳፻፮ ዓ.ም. ከ፵፫ አገራት የተውጣጡ ፳፭ የዳኛ ሦስትዮሾችን እና ፰ ረዳት ጥንዶችን (አራተኛና አምስተኛ ዳኛዎች) ለውድድሩ ሾሟል።[10][11]
የሽልማት ገንዘብ[ለማስተካከል | ኮድ አርም]
ፊፋ ለውድድሩ ያቀረበው ጠቅላላ የሽልማት ገንዘብ $576 ሚሊዮን ነው። ይህም ከ2010 እ.ኤ.አ. ውድድር ሽልማት ገንዘብ የ፴፯ ከመቶ ዕድገት አለው።[12] ከዚህ ውስጥ $70 ሚሊዮን የሚሆነው ተጫዋቾቹ ለሚጫወቱበት ክለቦች ተጫዋቾቹ ለሚደርስባቸው ጉዳት መካካሻ እንዲሆን ተሰጥቷል። ከውድድሩ በፊት እያንዳንዱ ቡድን ለዝግጅት ወጪው $1.5 ሚሊዮን የተረከበ ሲሆን ቀሪው ገንዘብ እንደሚመለከተው ተከፋፍሏል፦
- $8 ሚሊዮን - ለያንዳንዱ በምድብ ደረጃ የወደቀ ቡድን (፲፮ ቡድኖች)
- $9 ሚሊዮን - ለያንዳንዱ በየ፲፮ ዙር የወደቀ ቡድን (፰ ቡድኖች)
- $14 ሚሊዮን - ለያንዳንዱ በሩብ ፍፃሜ የወደቀ ቡድን (፬ ቡድኖች)
- $20 ሚሊዮን - በአራተኛ ደረጃ ለጨረሰው ቡድን
- $22 ሚሊዮን - በሶስተኛ ደረጃ ለጨረሰው ቡድን
- $25 ሚሊዮን - በሁለተኛ ደረጃ ለጨረሰው ቡድን
- $35 ሚሊዮን - ለአሸናፊው ቡድን
ከተማዎችና ስታዲየሞች[ለማስተካከል | ኮድ አርም]
በአስራ ሁለት ከተማዎች የሚገኙ አስራ ሁለት ስታዲየሞች ለውድድሩ ተዘጋጅተዋል። ሰባቱ አዲስ የተገነቡ ሲሆን አምስቱ ደግሞ የተሻሻሉ ስታዲየሞች ናቸው።
መሰልጠኛ ሰፈሮች[ለማስተካከል | ኮድ አርም]
እያንዳንዱ ቡድን የራሱ የሆነ የመሰልጠኛና መቆያ ሰፈር አለው። ፊፋ ፹፬ ዕጩ ከተማዎችን ካስታወቀ በኋላ[13] በጥር ፳፫ ቀን ፳፻፮ ዓ.ም. እያንዳንዱ የተሳታፊ ቡድኖች የመረጡትን ከተማ ይፋ አርጓል።[14]
የምድብ ደረጃ[ለማስተካከል | ኮድ አርም]
ምድብ ኤ[ለማስተካከል | ኮድ አርም]
ዋና መጣጥፍ፦ የ2014 እ.ኤ.አ. ፊፋ የዓለም ዋንጫ ምድብ ኤ መለጠፊያ:የ2014 እ.ኤ.አ. ፊፋ የዓለም ዋንጫ ምድብ ኤ
ምድብ ቢ[ለማስተካከል | ኮድ አርም]
ዋና መጣጥፍ፦ የ2014 እ.ኤ.አ. ፊፋ የዓለም ዋንጫ ምድብ ቢ መለጠፊያ:የ2014 እ.ኤ.አ. ፊፋ የዓለም ዋንጫ ምድብ ቢ
ምድብ ሲ[ለማስተካከል | ኮድ አርም]
ዋና መጣጥፍ፦ የ2014 እ.ኤ.አ. ፊፋ የዓለም ዋንጫ ምድብ ሲ መለጠፊያ:የ2014 እ.ኤ.አ. ፊፋ የዓለም ዋንጫ ምድብ ሲ
ምድብ ዲ[ለማስተካከል | ኮድ አርም]
ዋና መጣጥፍ፦ የ2014 እ.ኤ.አ. ፊፋ የዓለም ዋንጫ ምድብ ዲ መለጠፊያ:የ2014 እ.ኤ.አ. ፊፋ የዓለም ዋንጫ ምድብ ዲ
ምድብ ኢ[ለማስተካከል | ኮድ አርም]
ዋና መጣጥፍ፦ የ2014 እ.ኤ.አ. ፊፋ የዓለም ዋንጫ ምድብ ኢ መለጠፊያ:የ2014 እ.ኤ.አ. ፊፋ የዓለም ዋንጫ ምድብ ኢ
ምድብ ኤፍ[ለማስተካከል | ኮድ አርም]
ዋና መጣጥፍ፦ የ2014 እ.ኤ.አ. ፊፋ የዓለም ዋንጫ ምድብ ኤፍ መለጠፊያ:የ2014 እ.ኤ.አ. ፊፋ የዓለም ዋንጫ ምድብ ኤፍ
ምድብ ጂ[ለማስተካከል | ኮድ አርም]
ዋና መጣጥፍ፦ የ2014 እ.ኤ.አ. ፊፋ የዓለም ዋንጫ ምድብ ጂ መለጠፊያ:የ2014 እ.ኤ.አ. ፊፋ የዓለም ዋንጫ ምድብ ጂ
ምድብ ኤች[ለማስተካከል | ኮድ አርም]
ዋና መጣጥፍ፦ የ2014 እ.ኤ.አ. ፊፋ የዓለም ዋንጫ ምድብ ኤች መለጠፊያ:የ2014 እ.ኤ.አ. ፊፋ የዓለም ዋንጫ ምድብ ኤች
ማስታወሻ[ለማስተካከል | ኮድ አርም]
- ^ የጀርመን ሬኮርድ ሶስት ጊዜ የዓለም ዋንጫ አሸናፊ የነበረችውን የምዕራብ ጀርመን ሬኮርድ ይጨምራል
- ^ ከ1992 እ.ኤ.አ. በፊት ቦስኒያና ሄርጸጎቪና የዩጎዝላቪያ አካል ነበረች። ዩጎዝላቪያ በ፰ የዓለም ዋንጫዎች ተሳትፋለች።
ማመዛገቢያ[ለማስተካከል | ኮድ አርም]
- ^ (እንግሊዝኛ) "Pot allocations for the Preliminary Draw". FIFA.com (Fédération Internationale de Football Association) (27 July 2011). በ27 July 2011 የተወሰደ.
- ^ (እንግሊዝኛ) "FIFA launch GLT tender for Brazil 2013/14". FIFA.com (Fédération Internationale de Football Association) (19 February 2013).
- ^ (እንግሊዝኛ) "If the World Cup started tomorrow". ESPN (12 June 2013).
- ^ (እንግሊዝኛ) "1 day to go". FIFA.com (Fédération Internationale de Football Association) (11 June 2014).
- ^ (እንግሊዝኛ) "Pot 1 seeds set for Brazil 2014 draws". FIFA.com (Fédération Internationale de Football Association). 17 October 2013. http://www.fifa.com/worldranking/news/newsid=2197884/index.html በ23 November 2013 የተቃኘ.
- ^ (እንግሊዝኛ) "Draw procedures approved". FIFA.com (Fédération Internationale de Football Association). 3 December 2013. http://www.fifa.com/worldcup/final-draw/news/newsid=2238498/index.html በ3 December 2013 የተቃኘ.
- ^ (እንግሊዝኛ) "Final draw procedures". FIFA.com (Fédération Internationale de Football Association) (3 December 2013). በ3 December 2013 የተወሰደ.
- ^ (እንግሊዝኛ) "Final Draw reveals intriguing groups". FIFA.com (Fédération Internationale de Football Association). 6 December 2013. http://www.fifa.com/worldcup/news/y=2013/m=12/news=final-draw-reveals-intriguing-groups-2240026.html.
- ^ ሀ ለ (እንግሊዝኛ) "Regulations – FIFA World Cup Brazil 2014". FIFA.com (Fédération Internationale de Football Association).
- ^ (እንግሊዝኛ) "Referee trios and support duos appointed for 2014 FIFA World Cup". FIFA.com (Fédération Internationale de Football Association) (15 January 2014).
- ^ (እንግሊዝኛ) "Referees & assistant referees for the 2014 FIFA World Cup". FIFA.com (Fédération Internationale de Football Association).
- ^ (እንግሊዝኛ) "World Cup money pot increased to $576m". reuters.com. በ25 April 2014 የተወሰደ.
- ^ (እንግሊዝኛ) "Team Base Camps Brochure". FIFA.com (Fédération Internationale de Football Association) (7 November 2013).
- ^ (እንግሊዝኛ) "Team Base Camps for Brazil 2014 announced". FIFA.com (Fédération Internationale de Football Association) (21 January 2014).