ጋኔን

ከውክፔዲያ

ጋኔን (ነጠላ) ወይንም አጋንንት (ብዙ ቁጥር) የእርኩስ መንፈስ አይነት ሲሆን ከመጽሐፍ ቅዱስ ተመዘው በተስፋፉ ጽሑፎች ላይ የዚህ መንፈስ ታሪክ/አፈ-ታሪክ ተጽፎ ይገኛል። ለምሳሌ ቀኖናዊ ባልሆኑት ስነ ፍጥረት እና ሰይፈ ስላሴ በተባሉ የግዕዝ መጻሕፍት።

አሁንም ብዙው ህብረተሰብ እንዲህ ያስባል። በመጽሐፍ ቅዱስ ስለሚጠቀሱ፣ እስካሁን ድረስ በዓለም ዙሪያ ያሉ አብያተ ክርስቲያናት ትምህርት እንዲህ ይመስላል። አጋንንት የሳይንስ እውቀት ባላቸውም ሆነ በሌላቸው ኢትዮጵያውን ዘንድ እጅግ ከፍተኛ ፍርሃቻን የሚፈጥር አስተሳሰብ ነው። ነገር ግን የአጋንንት ታሪክ የሚመነጨው የሳይንስ አስተሳሰብ ባልተስፋፋበትና ስለቫይረስም ሆነ ጀርም በማይታወቅበት ዘመን ሲሆን ዘመናዊው የሳይንስ አስተሳሰብ ከዚህ ይለያል፣ እንደሚከተለው ይላል፦ ዋና ዓላማውም የበሽታዎችን አመጣጥ በሚያሳምን መልኩ ለመረዳት እና ለመተንበይ ነበር። ይሄ በኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን በአብዛኛው ያልተማረ ህብረተሰብ የሚሰራበት የነበር ነው። ስለሆነም ሆድ ቁርጠትጉስምትብድብድ ወዘተ በአጋንንት ምክንያት የሚመጡ ተደርገው ይታሰቡ ነበር።

የተለምዶ የአጋንንት አመጣጥ ታሪክ[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

እንደ ሰይፈ ስላሴ ታሪክ፣ በሰማይ ቤት 100 የመላዕክት ነገዶች ነበሩ። ከለታት አንድ ቀን እግዚአብሔር በሌለበት፣ ሰባልስዮስ ወይንም ሰይፈ ስላሴ የተሰኘ የመላዕክት አለቃ እኔ ሁሉን ፈጠርኩ አለ። ከ100ዎቹ ነግዶች አንደኛው ወገን ይህን የሰባልስዮስን ቃል አመነ። ይሄው ቡድን ወደ እሳት ተጣለ። ከሳት ከወጣም በኋላ የሰይጣን አገልጋይ ሆነ፡፡ የነገዱ አባላቶችም መጠሪያ ስማቸውም አጋንንት ሆነ።

እንደዚሁ አፈ ታሪክ 99 የመላዕክት ነገዶች ስለቀሩ እግዚአብሔር 100ውን ለመሙላት አዳምን ፈጠረ፡፡ ሆኖም አዳም ከጭቃ ስለተሰራ እና ሰይጣን ደግሞ ከአየር እና ብርሃን ስለተሰራ፣ ሰይጣን ለሰው ልጅ ክብር መስጠት እምቢ አለ፣ ስለዚህም በሁለቱ መካከል የማያቋርጥ ጠብ አለ።

የጋኔን በሽታና ባህላዊውን መድሃኒቱ[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

ከላይ እንደተጠቀሰው አብዛኛው በሽታ በአጋንንት ምክንያት የሚመጡ እንደንበር በብዙዎች ይታመን ነበር። ስለሆነም አንድ ግለሰብ በሽታ ሲይዘው እርሱን ለማዳን አንዱ አማራጭ አጋንንት የያዘውን ሰው በዛር መንፈስ በማስያዝ አጋንንቱን ከውስጡ ማስለቀቅ ነበር። የዛር መንፈስ ከአጋንንት ይሻላል ተብሎ ስለሚታመን። ፀበልቁርባን እና እንዲሁም የእርግፍጋፎ እንጨት (Protea Abyssinica) ለፈውስ ይረዳሉ ተብለው ተጠቃሚነትን ያገኛሉ[1]። ለኤድስ እና ሌሎች የቫይረስ እና ጀርም በሽታዎች በፀበል ፈውስ መፈለግ መሰረቱ ከዚህ የተዛባ ግንዛቤ ይፈልቃል።

በመጽሐፍ ቅዱስ[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

በብሉይ ኪዳን[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

  • ኦሪት ዘዳግም 32፡15 ፣17 መሠረት በሙሴ መዝሙር፣ ይሹሩን (የእስራኤል ሕዝብ መጠሪያ) እግዚአብሔርን ተወ፣ እግዚአብሔር ላልሆኑ አጋንንት እንደ ሠዉ ይጠቅሳል።
  • መጽሐፈ ዜና መዋዕል ካልዕ 11፡14-15 ኢዮርብዓምይሁዳ ተለይቶ የእስራኤል ንጉሥ በሆነበት ጊዜ የይሖዋ ካህናት ትቶ ለራሱ አጋንንት ካህናት እንዳቆመ ይላል።
  • መዝሙረ ዳዊት 91፡6 በእግዚአብሔር መጠጊያ የሚኖር ሰው ልጅ «ከቀትር ጋኔን» እንደማይፈራ ያረጋግጣል። የጥንታዊ ግሪክ («ሳባ ሊቃውንት») ትርጉም እንዲህ ይላል፤ አሁን ግን በይፋዊው ዕብራይስጥ ትርጉም «በቀትር ከሚያጥፋው ጥፋት» እንደማይፈራ ይላል።
  • መዝሙረ ዳዊት 95፡5 የአረመኔ ጣኦታት ሁሉ ለአጋንንት እንደ ሆኑ ይገልጻል።
  • መዝሙረ ዳዊት 105፡35-7 እስራኤላውያን የአሕዛብ እምነቶች ሲከተሉ እንኳን ልጆቻቸውን ለአጋንንት እንደ ሠዉ ይነግራል።
  • ትንቢተ ኢሳይያስ 13፡21 የባቢሎን ውድቀት ሲነበይ አጋንንት በዚያ ይዘፍናሉ ይላል። (በአንዳንድ ትርጉም ግን «አጋንንት» የሚለው የዕብራይስጥ ቃል ደግሞ ፍየል ማለት ሊሆን ይችላል።)
  • እንዲሁም ትንቢተ ኢሳይያስ 34፡14 የኤዶምያስ ጥፋት ሲነበይ፣ አጋንንት (ወይም ፍየሎች?) እርስ በርስ በዚያ ይጠራራሉ ይነግራል።

አዋልድ መጻሕፍት[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

በአዲስ ኪዳን[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

ወንጌሎች በተለይም በማርቆስ ወንጌል ዘንድ፣ ኢየሱስ በልዩ ልዩ ደዌ ወይም በሽታ የተሰቃዩትን ሰዎች እየፈወሰ፣ ጋኔን ወይም ርኩስ መንፈስ ካደረበት ሰው ጋኔኑን በቃሉ ያወጣል። (ማቴ. 4፡24፣ 8፡16፣ ማርቆስ 1፡32-34፣ 39፤ ወዘተ.)

  • የማቴዎስ ወንጌል 8፡28-33 - በጌርጌሴኖን አገር መቃብር ውስጥ ከኖሩ አጋንንት ካደሩባቸው ከ2 ግፈኛ ሰዎች አጋንንቱን አወጣና ወደ እሪያ መንጋ እንዲገቡ ፈቀደ። በማርቆስ 5 እና ሉቃስ 8 መሠረት የአንዱ ጋኔን ስም ሌጌዎን («ጭፍራ» ወይም «ሠራዊት» በሮማይስጥ) ይባል ነበር።
  • ማቴዎስ 9፡32 - ኢየሱስ ጋኔን ካደረበት ዲዳ ሰው ጋኔኑን አወጣና ዲዳው ተናገረ፤ የፈሪሳውያን አይሁድ ወገን ግን «በአጋንንት አለቃ አጋንንትን ያወጣል አሉ»።
  • ማቴዎስ 10፡8፣ የማርቆስ ወንጌል 3፡15፣ 16፡17፤ የሉቃስ ወንጌል 9፡1 - ኢየሱስ 12 ሐዋርያቱን አጋንንት እንዲያውጡ አዘዛቸው።
  • ማቴዎስ 11፡18፣ የሉቃስ 7፡33 - ኢየሱስ ስለ ዮሐንስ መጥምቁ ሲያስተምር አንዳንድ ሰዎች ጋኔን እንደ ነበረበት ይሉ እንደ ነበር ይገልጻል።
  • ማቴዎስ 12፡22 - ኢየሱስ ጋኔን ካደረበት ዕውር ዲዳ ጋኔኑን አወጣና ሰውዬው ተፈወሰ። ሕዝቡ ተገርሞ ኢየሱስ የዳዊት ልጅ (መሢሕ) እንደ ነበር ገመተ። የፈሪሳውያን ወገን ግን ይህ በብዔል ዜቡል በአጋንንት አለቃ ነው አሉ።
  • ማቴዎስ 15፡22-28 - አንዲት ከነዓናዊ ሴት ኢየሱስን «የዳዊት ልጅ ሆይ» ስትለው ጋኔን ከሴት ልጅዋ እንዲያውጣ ለመነችው።
  • የማርቆስ ወንጌል 7፡25-30 - ከነዓናዊት ሴት «ግሪክ፣ ትውልድዋም ሲሮፊኒቃዊት» ይባላል።
  • ማርቆስ 16፡9፣ ሉቃስ 8፡2 - ኢየሱስ ከመግደላዊት ማርያም 7 አጋንንት እንዳወጣ ይጻፋል።
  • ሉቃስ 4፡33 - ኢየሱስ በምኲራብ ሲያስተምር፣ አንድ ርኲስ ጋኔን መንፈስ ያደረበት ሰው ጮኸበት። ኢየሱስ ጋኔኑ ከዚህ ሰው እንዲወጣ አዘዘና ጋኔኑ ሰውዬውን በመካከላቸው ጥሎት ከእርሱ ወጣ።
  • ሉቃስ 4፡41 - ብዙ ጊዜ አጋንንትን ሲያውጣ፣ እንዲህ ይጮሁ ነበር፤ የኢየሱስ መታወቂያ ክርስቶስ (መሢሕ) መሆኑን ስላወቁ ነበር።
  • ሉቃስ 9፡37-42 - አንድ ሰው ኢየሱስ ጋኔን ከወንድ ልጁ እንዲያወጣ ለመነው። ይህ ጋኔን ልጁን ሲይዘው ይጮህና አረፋም እያስደፈቀው ያንፈራግጠው ነበር።
  • ሉቃስ 11፡14-26፤ ማርቆስ 3፡22-30፣ - ኢየሱስ ጋኔን ከዲዳ ሰው አወጣና አንዳንድ በብኤል ዜቡል ነው ሲሉ ገሰጻችው፤ እርስ በርስዋ የምትለያይ መንግሥት ትጠፋለች ሲላቸው። ከዚያ ርኩስ መንፈስ ከሰው በወጣ ጊዜ ዕረፍት እየፈለገ ውኃ በሌለበት ቦታ ማለፉን ያስተምራል።

ሌሎች ምንጮች[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

ማጣቀሻ[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

  1. ^ Reidulf Knut Molvaer: Socialization and social control in Ethiopia (1995) Page 47