ጥቅምት ፳፰
Appearance
(ከጥቅምት 28 የተዛወረ)
ጥቅምት ፳፰ ቀን በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የዓመቱ ፶፰ተኛው እና የመፀው ፴፫ተኛው ዕለት ነው። ከዚህ ዕለት በኋላ እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ በዘመነ ሉቃስ ፫፻፰ ቀናት ሲቀሩ፣ በዘመነ ዮሐንስ፤ ዘመነ ማቴዎስ እና ዘመነ ማርቆስ ደግሞ ፫፻፯ ቀናት ይቀራሉ።
- ፲፮፻፷፩ ዓ/ም - በዕለተ እሑድ ፀሐይ ደም መስላ እንደታየችና ሁለመናዋ በጉም እና ጭለማ እንደተከበበች (በግዕዙ፦”…ወተወለጠ ኵለንታሃ በኅብረ ጢስ ዘጸሊም” ይለዋል) የዘመኑ ‘ዜና-መዋዕል’ አስፍሮታል። ይህ የፀሐይ ግርደት በከፊል እስከ እንግሊዝ አገር ድረስም እንደታየ በፈረንጆቹ ተዘግቧል።
- ፲፱፻፷፮ ዓ/ም - ከዓመት በፊት ወደ ሻንግሃይ፣ ቻይና በመብረር የአየር አገልግሎት መስጠት የጀመረው የኢትዮጵያ አየር መንገድ በዛሬው ዕለት ደግሞ ወደ ቤዪጂንግ፣ መብረር ጀመረ። [1]
- ፲፱፻፷፯ ዓ/ም - የኢትዮጵያ ጊዜያዊ ወታደራዊ መንግሥት (ደርግ) በወቅቱ በብሪታኒያ ሕክምና ላይ የነበሩትን ፀሐፊ-ትዕዛዝ ወልደ ጊዮርጊስ ወልደ ዮሐንስን እና ወንድማቸውን አቶ መኮንን ወልደ ዮሐንስን በሦስት ቀናት እጃቸውን እንዲሰጡ አዘዘ።
- ፲፱፻፹ ዓ.ም. - የቱኒዚያው ፕሬዚደንት ሀቢብ ቡርጊባ ከሥልጣናቸው ተፈንቅለው በጠቅላይ ሚኒስቴሩ በዚኔ ኤል አቢዲን ቤን አሊ ተተኩ።
- ፲፱፻፺፫ ዓ.ም. - የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዚደንት ዊሊያም ጄፈርሰን ክሊንተን ባለቤት፣ ሂላሪ ሮዳም ክሊንተን ለአሜሪካ ሴኔት አባልነት በኒው ዮርክ ግዛት ተመረጡ።
- ^ መኮንን (ካፕቴን)፤ "አቪዬሽን በኢትዮጵያ -ዕውቀት፣ ጥበብ፣ ጥረትና እድገት" (፲፱፻፺፭) ገጽ ፪፻፹፭
- (እንግሊዝኛ) P.R.O., FCO 371/1829 - ANNUAL REVIEW FOR ETHIOPIA FOR 1974
- (እንግሊዝኛ) http://www.nytimes.com/learning/general/onthisday/20081105.html
የኢትዮጵያ ወራት | |
---|---|
መስከረም - ጥቅምት - ኅዳር - ታኅሣሥ - ጥር - የካቲት - መጋቢት - ሚያዝያ - ግንቦት - ሰኔ - ሐምሌ - ነሐሴ - ጳጉሜ |