ነሐሴ ፲፫
ነሐሴ ፲፫ ቀን በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የዓመቱ ፫፻፵፫ኛው ቀን ነው። ከዚህ ዕለት በኋላ እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ፣ በ ዘመነ ሉቃስ ፳፫ ቀናት በ ዘመነ ዮሐንስ፤ በ ዘመነ ማቴዎስ፤ እና በ ዘመነ ማርቆስ ደግሞ ፳፪ ቀናት ይቀራሉ።
ከኢትዮጵያን ሪፖርተር ፦ "ሆያ ሆዬ" በሚል አርስት ነሐሴ ፲፫ ቀን ፳፻፩ ዓ.ም የወጣ አንቀጽ
"መጣና ባመቱ አረ እንደምን ሰነበቱ ክፈትልኝ በሩን የጌታዬን ሆያ-ሆዬ-ሆ"
እያሉ ልጆች በዜማ እያወረዱ፣ በየመንደሩ እየተሽከረከሩ የሚጫወቱት ለቡሄ በዓላቸው ነው፡፡ ከትውልድ ወደ ትውልድ ሲተላለፍ የኖረ፣ አሁንም እየቀጠለ ያለ ትውፊት ነው፡፡
ዛሬ ነሐሴ ፲፫ ቀን የበዓሉ ክብር ነው፡፡ በተለይ ነባሩን ትውፊት ይዞ የሚገኘው በገጠር አካባቢ ነው፡፡ ቡሄኞቹ ልጆች ለበዓሉ አስቀድመው ይዘጋጃሉ፡፡ ጅራፍ ሲገምዱና ሲያጮሁ ይሰነብታሉ፡፡ እናቶችም ለበዓሉ የሚሆን ሙልሙል ዳቦ ያዘጋጃሉ፡፡ እየጨፈሩ ለሚመጡ ልጆችም ያበረክታሉ፡፡
በአዲስ አበባ ባሁን ጊዜ እየዞሩ ከሚጨፍሩት ሕፃናት ሌላ በከተማዋ ዳርቻ የሚኖሩ ጎረምሶችም በኦሮምኛ የቡሄ ጭፈራቸውን፣ ቄጠማ እያበረከቱ የሚያስኬዱበት ሥርዓት አላቸው፡፡
ቡሄ ጎላጣ፣ መላጣ ማለት እንደሆነ መጻሕፍት ይገልጻሉ፡፡ የክረምቱ ጨለማነት አልፎ ወደ ብርሃን፣ ወደ ጥቢ የሚያመራበት፣ ወደ መፀው የሚዘለቅበት ወገግታ የሚታይበት እንደሆነ ይታመንበታል፡፡
ከቡሄ በኋላ የጠነከረ ክረምት ስለማይኖርም "ቡሄ ከዋለ የለም ክረምት፣ ዶሮ ከጮኸ የለም ሌሊት" እየተባለም ይነገራል፡፡
ለባህላዊው በዓል መሠረት የሆነው፣ ኢየሱስ ክርስቶስ በሚያስተምርበት ጊዜ በታቦር ተራራ ላይ (ደብረ ታቦር) ብርሃነ መለኮቱን፣ ክብረ መንግሥቱን የገለጠበት ዕለት እንደሆነ ይጠቀሳል፡፡
- ፲፱፻፸፱ ዓ.ም. ረቡዕ ዕለት፣ ታላቁ የስፖርት ሰው፣ የኦሊምፒኩ አውራ ይድነቃቸው ተሰማ ያረፉበት ቀን ነው፡፡
- ፲፱፻፹፱ ዓ/ም በደብረ ዳሞ ገዳም ብዙ ታሪካዊ ፤ ሃይማኖታዊ እና ምሥጢራዊ የመጽሐፍ ቅርሶችን ያካተተው ቤተ መጻሕፍትና ሃይማኖታዊ 'ንዋየ ቅድሳት' የተከተቱበት ግምጃ ቤት ባልታወቀ ምክንያት በእሳት አደጋ ቃጠሎ ወደሙ።[1]
- ^ ለይኩን ብርሃኑ ፥ "ለምንት አንገለጉ አሕዛብ" (ጥቅምት 1997)፥ ገጽ 15
- http://ethiopianorthodox.org/amharic/abeyetbealat/yebealatenaatsewamat.pdf
- http://www.ethiopianreporter.com/content/view/6227/54/ Archived ኦገስት 20, 2009 at the Wayback Machine
- ዶክቶር እኖ ሊትመን። የቴዎድሮስ ታሪክ፤ በብርሊን እንደሚገኝ አብነት አሳታሚው (በ፲፱፻፪ ዓ/ም)
- መርስዔ ኀዘን ወልደ ቂርቆስ፤ ዕለታዊ የታሪክ ድርጊት - የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን የመጀመሪያው ፓትረያርክ (፲፱፻፶፩ ዓ/ም)
የኢትዮጵያ ወራት | |
---|---|
መስከረም - ጥቅምት - ኅዳር - ታኅሣሥ - ጥር - የካቲት - መጋቢት - ሚያዝያ - ግንቦት - ሰኔ - ሐምሌ - ነሐሴ - ጳጉሜ |