ጥር ፳፰፣ በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የዓመቱ ፻፵፰ ኛው ዕለት ሲሆን፤ የበጋ ወቅት ፴፫ኛው ቀን ነው። ከዚህ ዕለት በኋላ እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ በዘመነ ሉቃስ ፪፻፲፰ ዕለታት ሲቀሩ በዘመነ ዮሐንስ፣ ዘመነ ማቴዎስ እና ዘመነ ማርቆስ ደግሞ ፪፻፲፯ ቀናት ይቀራሉ።
- ፲፱፻፶ ዓ/ም - በግብጽ፣ ጋማል አብደል ናስር የአገሪቱ የመጀመሪያው ፕሬዚደንት ሆነው ታጩ።
- ፲፱፻፶ ዓ/ም - የአሜሪካ ኅብረት አየር ኃይል በሳቫና (ጂዮርጂያ) ጠረፍ አካባቢ አንድ የሃይድሮጅን ቦምብ ጠፍቶበት እስካሁን አልተገኘም።