ሐምሌ ፳፪
Appearance
(ከሐምሌ 22 የተዛወረ)
ሐምሌ ፳፪ ቀን
በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የዓመቱ ፫፻፳፪ ኛው ቀን ነው። ከዚህ ዕለት በኋላ እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ፣ በ ዘመነ ሉቃስ ፵፬ ቀናት፣ በዘመነ ዮሐንስ፤ በ ዘመነ ማቴዎስ፤ እና በ ዘመነ ማርቆስ ደግሞ ፵፫ ቀናት ይቀራሉ።
- ፲፰፻፳፰ ዓ/ም በፓሪስ ከተማ በፈረንሳይ አብዮት እና በ’ናፖሌዎናዊ ጦርነቶች’ ሕይወታቸውን ላጡ ፈረንሳውያን ወታደሮች መታሰቢያ የቆመው ‘የድል ቅስት’ (Arc de Triomphe) ተመረቀ።
- ፲፱፻፲፫ ዓ/ም አዶልፍ ሂትለር የጀርመን ሰብአዊ የሠራተኞች ማኅበር (Nationalsozialistische Deutsche Arbeiterpartei ) መሪ ሆኖ ተመረጠ።
- ፲፱፻፳፰ ዓ/ም በወሎ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ጳጳስ የነበሩት አቡነ ጴጥሮስ በፋሺስት ኢጣልያኖች እጅ ተረሽነው ለኢትዮጵያ አገራቸው ነጻነት ሰማዕትነት ተቀበሉ።
- ፲፱፻፵ ዓ/ም በሁለተኛው ዓለም ጦርነት ምክንያት ለ አሥራ ሁለት ዓመታት ተቋርጦ የነብረው የኦሊምፒክ ፲፬ኛው ውድድር በሎንዶን ተጀመረ።
- (እንግሊዝኛ) http://en.wikipedia.org/wiki/July_29
የኢትዮጵያ ወራት | |
---|---|
መስከረም - ጥቅምት - ኅዳር - ታኅሣሥ - ጥር - የካቲት - መጋቢት - ሚያዝያ - ግንቦት - ሰኔ - ሐምሌ - ነሐሴ - ጳጉሜ |