ጡት አጥቢ
Appearance
(ከአጥቢ እንስሳ የተዛወረ)
አጥቢ እንስሳት የምንላቸው የጀርባ አጥንት ያላቸው ከሚባሉት የእንስሳት ስፍን ውስጥ የሚገኝ መደብ ነው። በዚህ መደብ ውስጥ የሚገኙት እንደ የሰው ልጅ እና አንበሳ ያሉ እንስሳት ሴቷ አርግዛ በመውለድ እና ጡት ወተት በማጥባቷ ይታወቃሉ። እንዲሁም ባለ ፀጉርና ሙቀት ያለ ደም በመሆናቸውና ተጨማሪ የአዕምሮ ክፍል በመኖራችው ይታወቃሉ።
የመደቡ ዋና ክፍለመደቦች፦
- ዝሆን መጎጥ ወይም «ሰንጊ» (አፍሪካ ብቻ)
- የወርቃማ ፍልፈል ክፍለመደብ - ወርቃማ ፍልፈል፣ አቆስጣ-መጎጥ፣ ተንረክ (አፍሪካና ማዳጋስካር ብቻ)
- የአዋልደጌሳ ክፍለመደብ
- የአሽኮኮ ክፍለመደብ - አሽኮኮ
- ባለ ኩምቢዎች ወይም የዝሆን ክፍለመደብ
- የዱጎንግ ክፍለመደብ ወይም «የባሕር ላሞች»
- የጉንዳን በል ክፍለመደብ - (አሜሪካዎች ብቻ)
- የአርማዲሎ ክፍለመደብ - (አሜሪካዎች ብቻ)
- የዛፍ መጎጥ ክፍለመደብ - (ደቡብ-ምሥራቅ እስያ ብቻ)
- የኮሉጎ ክፍለመደብ ወይም «በራሪ ሌሙሮች»፣ (ደቡብ-ምሥራቅ እስያ ብቻ)
- ሰብአስተኔ - ሌሙሮች፣ ዝንጀሮች፣ ጦጣዎችና የሰው ልጅ
- የጥንቸል ክፍለመደብ - ጥንቸል
- ዘራይጥ - አይጥ፣ ሽኮኮ፣ ጃርት
- የትድግ ክፍለመደብ - ትድግ፣ ፍልፈል፣ መጎጥ
- የሌት ወፍ
- የፓንጎሊን ክፍለመደብ
- ስጋበል - የድመት አስተኔ፣ የውሻ አስተኔ፣ የፋደት አስተኔ፣ ጅብ፣ ጥርኝ፣ ድብ፣ ፋሮ፣ ሞረስ ወዘተ.
- ሙሉ ጣት ሸሆኔ - አሳማ፣ ጉማሬ፣ ቀጭኔ፣ ግመል፣ የቶራ አስተኔ
- የዓሣንበሪ አስተኔ - ከሙሉ ጣት ሸሆኔ ሥር ይዛመዳል
- ጎደሎ ጣት ሸሆኔ - ፈረስ፣ አውራሪስ
- ጠጣይ አጥቢ (ወይም ዕንቁላል ጣይ አጥቢ፤ አውስትራሊያ ብቻ)