የካቲት ፴
Appearance
የካቲት ፴፣ በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የዓመቱ ፻፹ ኛው ዕለት ሲሆን፤ የበጋ ወቅት ፷፭ኛው ቀን ነው። ከዚህ ዕለት በኋላ እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ በዘመነ ሉቃስ ፻፹፮ ዕለታት ሲቀሩ በዘመነ ዮሐንስ፣ ዘመነ ማቴዎስ እና ዘመነ ማርቆስ ደግሞ ፻፹፭ ቀናት ይቀራሉ።
- ፲፰፻፹፩ ዓ/ም - በሱዳን ግዛት ውስጥ ባለችው ገላባት ላይ በዓፄ ዮሐንስ ፬ኛ የሚመራው የኢትዮጵያ ሠራዊት እና የሱዳን 'ማህዲ' ሠራዊቶች በዚህ ዕለትጦርነት ገጥመው፣ ኢትዮጵያውያኖቹ በማሸነፍ ላይ ሳሉ ንጉሠ ነገሥቱ፣ መጀመሪያ እጃቸው ላይ፤ ቀጥሎም ደረታቸውን በጥይት ስለተመቱ የኢትዮጵያው ሠራዊት ከሥፍራው በማፈግፈግ ሲለቅ ድሉ የ'ማህዲዎቹ' ኾነ። ንጉሠ ነገሥቱም ማታውኑ አረፉ።
- ፲፱፻፶፪ ዓ/ም - የሶቪዬት ሕብረት ፩ ሺህ ተማሪዎችን የሚያስተናገድ የቴክኒክ ትምህርት ቤት (የአሁኑ ባህር ዳር ዩኒቨርስቲ) ባህር ዳር ላይ እንደምትሠራ የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት መንግሥት አስታወቀ።
- (እንግሊዝኛ) http://en.wikipedia.org/wiki/March_9
- (እንግሊዝኛ) P.R.O., FO 371/154836
የኢትዮጵያ ወራት | |
---|---|
መስከረም - ጥቅምት - ኅዳር - ታኅሣሥ - ጥር - የካቲት - መጋቢት - ሚያዝያ - ግንቦት - ሰኔ - ሐምሌ - ነሐሴ - ጳጉሜ |
ጅምር! ይህ አጭር ጽሑፍ መሠረት ወይም መዋቅር ነው። አሁን ሊያስፋፉት ይችላሉ! |