Jump to content

የካቲት ፳፫

ከውክፔዲያ
(ከየካቲት 23 የተዛወረ)

የካቲት ፳፫፣ በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የዓመቱ ፻፸፫ ኛው ዕለት ሲሆን፤ የበጋ ወቅት ፶፰ ኛው ቀን ነው። ከዚህ ዕለት በኋላ እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ በዘመነ ሉቃስ ፻፺፫ ዕለታት ሲቀሩ በዘመነ ዮሐንስ፣ ዘመነ ማቴዎስ እና ዘመነ ማርቆስ ደግሞ ፻፺፪ ቀናት ይቀራሉ።

ይሄ ዕለት በኢትዮጵያ የአድዋ ጦርነት የድል በዓል መታሰቢያ ነው።

ዓቢይ ታሪካዊ ማስታወሻዎች

[ለማስተካከል | ኮድ አርም]
  • ፲፰፻፶፱ ዓ/ም – ነብራስካአሜሪካ ኅብረት ፴፯ ኛዋ አባል ሆነች። ላንካስተር የሚባለው ከተማዋ በአዲስ ስም ሊንከን ተብሎ ዋና ከተማዋ ሆነ።
  • ፲፱፻፷፩ ዓ/ም - በብሪታኒያ እና በፈረንሳይ ትብብር የተሰራው ‘ኮንኮርድ’ አየር ዠበብ ለመጀመሪያ ጊዜ ከፈረንሳይ ከተማ ቱሉዝ ተነስቶ ለ ሃያ ሰባት ደቂቃ የበረራ ሙከራ አደረገ።
  • ፲፱፻፷፪ ዓ/ም - አሁን ዚምባብዌ የምትባለው የቀድሞዋ ሮዴዢያ ነጭ ዜጎች በመሪያቸው ኢያን ስሚዝ ሥልጣን አገሪቱን ከብሪታኒያ ዘውድ ጋር የነበራትን ሰንሰለት በጥሰው በሸፍጥ ሪፑብሊክ አደረጓት።
  • (እንግሊዝኛ) P.R.O., FO 371/183838
  • (እንግሊዝኛ) P.R.O., FCO 371/784
  • (እንግሊዝኛ) P.R.O., FCO 371/1118
  • (እንግሊዝኛ) P.R.O., FCO 371/1660


የኢትዮጵያ ወራት
መስከረም - ጥቅምት - ኅዳር - ታኅሣሥ - ጥር - የካቲት - መጋቢት - ሚያዝያ - ግንቦት - ሰኔ - ሐምሌ - ነሐሴ - ጳጉሜ