ግንቦት ፯
Appearance
(ከግንቦት 7 (ፓርቲ) የተዛወረ)
- ለኢትዮጵያዊው ፖለቲካዊ ፓርቲ፣ የግንቦት 7 ፖለቲካዊ ፓርቲ ይዩ።
ግንቦት ፯ ቀን፣ በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የዓመቱ ፪፻፵፯ኛው ዕለት ሲሆን፤ የፀደይ (በልግ) ወቅት ፵፪ኛው ቀን ነው። ከዚህ ዕለት በኋላ እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ በዘመነ ሉቃስ ፻፲፱ ዕለታት ሲቀሩ በዘመነ ዮሐንስ፣ ዘመነ ማቴዎስ እና ዘመነ ማርቆስ ደግሞ ፻፲፰ ቀናት ይቀራሉ።
- ፲፱፻፵ ዓ/ም - ታላቋ ብሪታኒያ በፍልስጥኤም ላይ የነበራት የአስተዳደር ሥልጣን ሲያከትም፤ ግብጽ፣ ዮርዳኖስ፣ ሊባኖስ፣ ሶርያ፣ ኢራቅ እና ሳውዲ አረቢያ ተባብረው አዲስ የተመሠረተችውን እስራኤልን ወረሩ። ይኼም ድርጊት የመጀመሪያውን የአረብ እና እስራኤል ጦርነት ለኮሰ።
- ፲፱፻፷፪ ዓ/ም - የአሜሪካው ፕሬዚደንት ሪቻርድ ኒክሰን በሀገራቸው ጦር ሠራዊት ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ አና ሄይስ (Anna Mae Hays) እና ኤልሣበጥ ሆይሲንግቶን(Elizabeth P. Hoisington) የተባሉ ሁለት ሴት መኮንኖችን ወደጄነራልነት ማዕርግ አሳደጉ።
- ፲፱፻፹፫ ዓ/ም - ፈረንሳዊቷ ኢዲዝ ክሬሶን (Édith Cresson) የሀገራቸው የመጀመሪያዋ ሴት ጠቅላይ ሚኒስትር ሆኑ።
የኢትዮጵያ ወራት | |
---|---|
መስከረም - ጥቅምት - ኅዳር - ታኅሣሥ - ጥር - የካቲት - መጋቢት - ሚያዝያ - ግንቦት - ሰኔ - ሐምሌ - ነሐሴ - ጳጉሜ |
ጅምር! ይህ አጭር ጽሑፍ መሠረት ወይም መዋቅር ነው። አሁን ሊያስፋፉት ይችላሉ! |