Jump to content

ኅዳር ፳፭

ከውክፔዲያ
የ23:43, 26 ኦገስት 2013 ዕትም (ከMedebBot (ውይይት | አስተዋጽኦ) ተዘጋጅቶ)
(ለውጡ) ← የፊተኛው እትም | «የአሁኑን እትም ለመመልከት» (ለውጡ) | የሚከተለው እትም → (ለውጡ)

ኅዳር ፳፭ ቀን በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የዓመቱ ፹፭ኛው ቀን ነው። ከዚህ ዕለት በኋላ እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ፣ በ ዘመነ ሉቃስ ፪፻፹፩ ቀናት በ ዘመነ ዮሐንስ፤ በ ዘመነ ማቴዎስ፤ እና በ ዘመነ ማርቆስ ደግሞ ፪፻፹ ቀናት ይቀራሉ።

ዓቢይ ታሪካዊ ማስታወሻዎች

[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

፲፮፻፲፪ ዓ.ም. ሠላሣ ስምንት ከብሪታንያ የመጡ አቅኝዎች ቨርጂኒያ ላይ አርፈው ለ እግዚአብሔር ምስጋናቸውን አቀረቡ። ይሄም ድርጊት በአሜሪካ የመጀመሪያው የምሥጋና ሰርዐት ዕለት ነበር ይባላል።

፲፯፻፹፬ ዓ.ም. በዓለም የመጀመሪያው የ’ዕሑድ ጋዜጣ’ የብሪታንያው ‘ኦብዘርቨር’ ‘The Observer’ የተባለው ጋዜጣ የመጀመሪያው ዕትም ወጣ።

፲፱፻፴፰ ዓ.ም. በአሜሪካ የሕዝብ እንደራሴዎች ‘United States Senate’ አባላት በስድሳ አምሥት ለ ሰባት ድምጽ አሜሪካ ጥቅምት ፲፬ ቀን ፲፱፻፴፰ ዓ.ም. የተመሠረተው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዓባል እንድትሆን አጸደቁ።

፲፱፻፶፩ ዓ.ም. የቀድሞዋ ዳሆሚ የዛሬዪቷ ቤኒንፈረንሳይ ቁጥጥር ውጭ ዕራሷን በራሷ የመግዛት ስርዐት ጀመረች።

፲፱፻፶፬ ዓ.ም. የብሪታንያ መንግሥት ለሴቶች ዜጋዎቹ የ’ጽንሰት መከላከያ’ መድሐኒት በብሔራዊ የጤና ጥበቃ አገልግሎት በነጻ መቀበል እንዲችሉ አደርገ።

፲፱፻፸ ዓ.ም. የመካከለኛው አፍሪካ ሪፑብሊክ ፕሬዚደንት ጃን ቤደል ቦካሳ ዕራሳቸውን በራሳቸው ቀዳማዊ ቦካሳ በሚል ስም በማንገሥ የአገሪቱም ስም ተቀይሮ ‘የመካከለኛው አፍሪካ ንጉሠ ነገሥት መንግሥት’ በሚል ስም ተሰየመች።

፲፱፻፹፬ ዓ.ም. የፓን አሜሪካ አየር መንገድ ከ ስድሳ አራት ዓመታት አገልግሎት በኋላ አከተመ።

፲፱፻፹፭ ዓ.ም. በሶማሊያ አገር ውስጥ በተከሰተው የ’ዕርስ በርስ ጦርነት’ የአሜሪካው ፕሬዚደንት ጆርጅ ኸርበርት ዎከር ቡሽ የ’ሰብዓዊ ርሕራሔ’ ምክንያት በሚል መነሻ ሃያ ስምንት ሺህ የአሜሪካ ወታደሮችን ወደ ሶማሊያ ላኩ።

፲፰፻፸፭ ዓ.ም. እስፓኝን ለሠላሣ ስድስት ዓመታት በአምባገነንነት የመሩት ፍራንሲስኮ ፍራንኮ ተወለዱ።

፲፭፻፷ ዓ/ም - የዓፄ ልብነድንግል ሚስት እቴጌ ሰብለ ወንጌል በዚህ ዕለት አመድ በር በምትባል ሥፍራ አረፉ።



የኢትዮጵያ ወራት
መስከረም - ጥቅምት - ኅዳር - ታኅሣሥ - ጥር - የካቲት - መጋቢት - ሚያዝያ - ግንቦት - ሰኔ - ሐምሌ - ነሐሴ - ጳጉሜ