ኅዳር ፪
Appearance
ኅዳር ፪ ቀን በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የዓመቱ ፷፪ኛው እና የመፀው ወቅት ፴፯ተኛ ቀን ነው። ከዚህ ዕለት በኋላ እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ፣ በ ዘመነ ሉቃስ ፫፻፬ ቀናት በ ዘመነ ዮሐንስ፤ በ ዘመነ ማቴዎስ፤ እና በ ዘመነ ማርቆስ ደግሞ ፫፻፫ ቀናት ይቀራሉ።
- ፲፱፻፲፩ ዓ.ም. - ከአራት ዓመት ጦርነት በኋላ የአንደኛው የዓለም ጦርነት በአንድ በኩል ንምሳ በሌላ በኩል ተቃዋሚዎቿ አባር አገሮች በስምምነትና በፊርማ ውጊያው ከጧቱ አምስት ሰዐት ላይ እንዲያቆም ተስማሙ። ይሄ ድርጊት በየዓመቱ ከጧቱ አምስት ሰዐት ላይ በሁለት ደቂቃ ሕሊናዊ ጸሎት ይከበራል።
- ፲፱፻፶፰ ዓ.ም. - በቀድሞዋ ሰሜን ሮዴዚያ፤ በዛሬይቷ ዚምባብዌ በነጩ ጠቅላይ ሚኒስቴር ኢያን ስሚዝ የሚመራው መንግሥት ከህግ ውጭ አገሪቱን ከብሪታንያ ነጻነት አወጀ።
- ፲፱፻፺፯ ዓ.ም - የፍልስጥኤም ነጻነት ግንባርን እና የፍልስጥኤምን ሕዝብ ከአርባ ዓመት በላይ የመሩት ያሲር አራፋት በተወለዱ በሰባ አምሥት ዓመታቸው በፓሪስ ሆስፒታል አረፉ፡ ወዲያው ማህሙድ አባስ በእሳቸው ምትክ የድርጅቱ መሪ ሆነው ተመረጡ።
- ፲፰፻፷፪ ዓ.ም.- ፋሺስት ኢጣልያ አገራችንን ኢትዮጵያን በወረረበት ዘመን፤ የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥትነትን ሥልጣን ይዘው የነበሩት የኢጣልያ ንጉሥ ቪክቶር ኢማኑኤል ሣልሳዊ በዚህ ዕለት ተወለዱ።
- ፲፱፻፺፯ ዓ.ም.- የፍልስጥኤም ነጻነት ግንባር መሪ እና የኖቤል ሰላማዊ ሽልማት ተቀባይ ያሲር አራፋት
- (እንግሊዝኛ) http://news.bbc.co.uk/onthisday/hi/dates/stories/november/11/newsid_4292000/4292998.stm
- (እንግሊዝኛ) http://www.nytimes.com/learning/general/onthisday/20081111.html
የኢትዮጵያ ወራት | |
---|---|
መስከረም - ጥቅምት - ኅዳር - ታኅሣሥ - ጥር - የካቲት - መጋቢት - ሚያዝያ - ግንቦት - ሰኔ - ሐምሌ - ነሐሴ - ጳጉሜ |