ጥቅምት ፳፬
ጥቅምት ፳፬ ቀን በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የዓመቱ ፶፬ኛ ቀን ነው። ከዚህ ቀን በኋላ እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ፣ በ ዘመነ ሉቃስ ፫፻፲፪ ቀናት በ ዘመነ ዮሐንስ፤ በ ዘመነ ማቴዎስ፤ እና በ ዘመነ ማርቆስ ደግሞ ፫፻፲፩ ቀናት ይቀራሉ።
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በዚህ ዕለት በየወሩ በ እቲሳ ቡልጋ የተወለዱት የኢትዮጵያዊው የቅዱስ አቡነ ተክለ ኃይማኖት መታሰቢያ ቀን አድርጋ ታከብረዋለች።
፲፬፻፹፮ ዓ.ም የጄኖአው ተወላጅ ክሪስቶፎሮ ኮሎምቦ (Christopher Colombus) የአትላንቲክ ውቅያኖስን ከአውሮፓ ወደምዕራብ የማቋረጥ ሁለተኛው ጉዞው፤ ለመጀመሪያ ጊዜ የዶሚኒካ ደሴትን አገኘ።
፲፰፻፹፮ ዓ.ም. ፓናማ በአሜሪካ ማበረታታት ተነስታ ከኮሎምቢያ ቅኝ ግዛትነት ነጻነቷን አወጀች። የአሜሪካው ፕሬዚደንት ቴዎድሮስ ሩዝቬልት የፓናማ ቦይን ለመቅደድ ፈልገው ኮሎምቢያ ለዚሁ ሥራ መከፈል የፈለገችውን ዋጋ ስላልተስማሙበት ፓናማ ነጻ አገር እንድትሆን ጥረታቸው ተሳካ።
፲፱፻፶ የሶቪዬት ሕብረት በጠፈር የመጀመሪያውን እንስሳ፤ ላይካ የተባለውን ውሻ፤ በስፑትኒክ ሁለተኛ መንኲራኩር ወደጠፈር ተኮሰች።
፲፱፻፷፫ ዓ/ም ሰባ ከመቶውን የአዲስ አበባ ውሐ የሚያስተናግደው የለገዳዲ የውሐ ግድብ ተመርቆ አገልግሎቱን ጀመረ።
፲፱፻፺፯ ዓ.ም. የአሜሪካው ፕሬዚደንት ጆርጅ ወከር ቡሽ ለሁለተኛና ለመጨረሻ ጊዜ ተመረጡ።
፲፱፻፹፱ ዓ.ም የመካከለኛው አፍሪካ ሪፑብሊክ አገርን በወታደራዊ መፈንቅለ መንግሥት ከያዙ በኋላ ራሳቸውን በዘውድ ያነገሡት ዣን ቢዴል ቦካሳ በተወለዱ በሰባ አምስት ዓመታቸው አረፉ።
የኢትዮጵያ ወራት | |
---|---|
መስከረም - ጥቅምት - ኅዳር - ታኅሣሥ - ጥር - የካቲት - መጋቢት - ሚያዝያ - ግንቦት - ሰኔ - ሐምሌ - ነሐሴ - ጳጉሜ |