መስከረም ፬
Appearance
(ከመስከረም 4 የተዛወረ)
መስከረም ፬ ቀን
በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የዓመቱ ፬ኛው እና የክረምት ፸፬ኛው ዕለት ነው። ከዚህ ዕለት በኋላ እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ፣ በዘመነ ሉቃስ ፫፻፷፪ ዕለታት ሲቀሩ፤ በዘመነ ዮሐንስ ፣ ዘመነ ማቴዎስ እና ዘመነ ማርቆስ ደግሞ ፫፻፷፩ ዕለታት ይቀራሉ።
- ፲፭፻፴፬ ዓ/ም - ሳንቲያጎ ቺሌ በኗሪ አርበኞች ጠፋ።
- ፲፮፻፪ ዓ/ም - የስፓንያ ከተማ ቫሌንሲያ ሞሪስቾዎችን (አረብ ክርስቲያን) ሁሉ አባረራቸው።
- ፲፮፻፸፮ ዓ/ም - የአውሮፓ ሠራዊት በቪዬና ውግያ ቱርኮችን አሸነፉ።
- ፲፰፻፺፬ ዓ/ም - የአሜሪካ ፕሬዚደንት መኪንሊ በነፍሰ ገዳይ ጥይት ሲሞቱ ቴዮዶር ሩዝቬልት ፕሬዚዳንት ሆኑ።
- ፲፱፻፵ ዓ/ም- የደጃዝማች ባልቻ መታሰቢያ ሆስፒታል በዚህ ዕለት ተመርቆ ተከፈተ።
- ፲፱፻፶፫ ዓ/ም - "ኦፔክ" -" የነዳጅ አስወጪ አገራት ድርጅት" - ተመሰረተ።
- ፲፱፻፶፫ ዓ/ም - በኮንጎ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ በተካሄደ ወታደራዊ መፈንቅለ መንግሥት አምባ ገነኑ ዮሴፍ ሞቡቱ የሥልጣኑን በትር ጨበጠ።
የኢትዮጵያ ወራት | |
---|---|
መስከረም - ጥቅምት - ኅዳር - ታኅሣሥ - ጥር - የካቲት - መጋቢት - ሚያዝያ - ግንቦት - ሰኔ - ሐምሌ - ነሐሴ - ጳጉሜ |