ሚያዝያ ፳፫
Appearance
(ከሚያዝያ 23 የተዛወረ)
ሚያዝያ ፳፫
በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የዓመቱ ፪፻፴፫ኛው ዕለት ሲሆን የፀደይ (በልግ)ወቅት ፳፰ተኛው ቀን ነው። ከዚህ ዕለት በኋላ እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ፣ በዘመነ ዮሐንስ ፻፴፫ ዕለታት ሲቀሩ፤ በዘመነ ማቴዎስ፤ ማርቆስ እና ሉቃስ ደግሞ ፻፴፪ ዕለታት ይቀራሉ።
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ይሄንን ዕለት ሰማዕቱ ቅዱስ ጊዮርጊስ የሞተበትን ዕለት ማስታወሻ አድርጋ ትዘክረዋለች፡
“በዘአዕረፈ እግዚእየ ማር ጊዮርጊስ ገብሩ ለኢየሱስ ክርስቶስ በዘተከለለ ወርኁ በጽርዕ ጵንፍልዮ ስሙ ዘበትርጓሜሁ ሚያዝያ አመ ፳ወ፫ ለሠርቅ ወዕለቱሂ ዓርብ በጊዜ ፱ቱ ሰዓት አሜን።”
“የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አገልጋይ ጌታዬ ቅዱስ ጊዮርጊስ ያረፈበት ሰማዕትነቱን የፈጸመበት ወሩ በጽርዕ ጵንፍልዮ ይባላል። ይኸውም ሚያዝያ ነው ወሩ በባተ በሃያ ሦስት ቀን ዕለቱም ዓርብ በዘጠኝ ሰዓት ነው አሜን።” [1]
- ፲፱፻፷፰ ዓ/ም ፥ የኅብረተ ሰብአዊት ኢትዮጵያ ጊዜያዊ ወታደራዊ አስተዳደር፣ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ዴሞክራሲያዊ አብዮት ፕሮግራምን አወጣ።
- http://www.ethiopianreporter.com Archived ጃንዩዌሪ 24, 2005 at the Wayback Machine ኪንና ባህል፡ ሳምንቱ በታሪክ
- (እንግሊዝኛ) http://en.wikipedia.org/wiki/April_30
የኢትዮጵያ ወራት | |
---|---|
መስከረም - ጥቅምት - ኅዳር - ታኅሣሥ - ጥር - የካቲት - መጋቢት - ሚያዝያ - ግንቦት - ሰኔ - ሐምሌ - ነሐሴ - ጳጉሜ |