ታኅሣሥ ፭
Appearance
(ከታኅሣሥ 5 የተዛወረ)
ታኅሣሥ ፭ ቀን በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የዓመቱ ፺፭ኛው ቀን ነው። ከዚህ ዕለት በኋላ እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ፣ በ ዘመነ ሉቃስ ፪፻፸፩ ቀናት በ ዘመነ ዮሐንስ፤ በ ዘመነ ማቴዎስ፤ እና በ ዘመነ ማርቆስ ደግሞ ፪፻፸ ቀናት ይቀራሉ። እንዲሁም የአቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ የልደት ቀን ነው
- ፲፱፻፴፱ ዓ/ም የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ጽሕፈት ቤቱ በኒው ዮርክ ከተማ እንዲሆን ወሰነ።
- ፲፱፻፶፫ ዓ/ም በወንድማማቾች መንግሥቱ ንዋይ እና ገርማሜ ንዋይ የተሰነጸጸው የታኅሣሥ ግርግር መፈንቅለ መንግሥት ዓላማውን ይፋ አደረገ። አብሮም የለውጥ ፈላጊ ናቸው የሚባሉትን ልዑል ራስ እምሩ ኃይለ ሥላሴን በጠቅላይ ሚኒስትርነት መሾማቸውንና አልጋ ወራሹን መርዕድ አዝማች አስፋ ወሰንን (“አስገድደው”) በማስማማትም መንግሥት በቆረጠላቸው ደመወዝ እየተዳደሩ ለሕገ መንግሥት የሚገዙ ንጉሥ ሆነው እንደሚያገለግሉ እራሳቸው ለሕዝቡ በራዲዮ እንዲያስተላልፉ አደረጉ።
- ፲፱፻፶፬ ዓ/ም ታንዛንያ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት አባል ሆነች።
- ፲፱፻፺፱ ዓ/ም የደቡብ ኮርያው ተወላጅ፣ ባን ኪ ሙን ስምንተኛው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ጸሐፊ ሆኑ።
- ፲፱፻፷፬ ዓ/ም ዲክ ታይገር (ሪቻርድ ኢሄቱ) የሚባለው ናይጄሪያዊ ቦክሰኛ በተወለደ በ ፵፪ ዓመቱ በጉበት ነቀርሳ ምክንያት አረፈ። ዲክ ታይገር የባያፍራን የመገንጠል ሙከራ ደጋፊ ነው በሚል ወደአገሩ እንዳይመለስ ተከልክሎ በስደት አሜሪካ ይኖር ነበር።
- (እንግሊዝኛ) http://en.wikipedia.org/wiki/December_14
- (እንግሊዝኛ) http://news.bbc.co.uk/onthisday/hi/dates/stories/december/14/ Archived ጁን 20, 2006 at the Wayback Machine
- (እንግሊዝኛ) http://www.nytimes.com/learning/general/onthisday/20091214.html
የኢትዮጵያ ወራት | |
---|---|
መስከረም - ጥቅምት - ኅዳር - ታኅሣሥ - ጥር - የካቲት - መጋቢት - ሚያዝያ - ግንቦት - ሰኔ - ሐምሌ - ነሐሴ - ጳጉሜ |