ክንንብ ዘር
Appearance
ክንንብ ዘር (Magnoliophyta ወይም Angiospermae ወይም አባቢ ተክል) ከአትክልት ስፍን ውስጥ አንድ ታላቅ የአትክልት ክፍለስፍን ነው። እነዚህ አበባ እና ፍራፍሬ የሚሰጡት አትክልት ሁሉ ናቸው።
በዘመናዊ ሥነ ሕይወት ጥናት ዘንድ የክፍለስፍኑ ስምንት ዋና መደባት እነዚህ ናቸው፦
- አምቦሬላ ዛፍ - አንድ ዝርያ ብቻ በኑቨል ካሌዶኒ ተገኝቷል።
- የቡሻይ መደብ 80 ዝርዮች
- የኮከብ እንስላል መደብ 100 ዝርዮች
- የማግኖሊያ መደብ - 9000 ዝርዮች፤ ቁንዶ በርበሬ፣ ቀረፋ፣ ሰናመኪ፣ አቡካዶ፣ ግሽጣ፣ አምበሾክ ወዘተ.
- የሁቱ መደብ - በገሞጂዎች ብቻ የሚገኙ 77 ዝርዮች
- አንድክክ - 70,000 ዝርዮች፤ እህል፣ ሣር፣ ሸንኮራ ኣገዳ፣ ዘምባባ፣ ሸምበቆ፣ ሙዝ፣ ዝንጅብል፣ እርድ፣ ኮረሪማ፣ ሰሪቲ፣ ሽንኩርት ወዘተ.
- የውሃ ቀንድ ቅጠል - ጨው አልባ ውሃ የሚኖሩ 6 ዝርዮች
- ሁለት ክክ 170,000 ዝርዮች፤ እንዳሁላ፣ ወይን፣ አኻያ፣ ግራር፣ ጽጌ ረዳ፣ እንጆሬ፣ ፖም፣ ኮክ፣ አልመንድ፣ በለስ፣ እጸ ፋርስ፣ ዱባ፣ ሃብሃብ፣ ኪያር፣ ሮማን፣ ቅርንፉድ፣ ባህር ዛፍ፣ ብርቱካን፣ ማንጎ፣ ጐመን፣ ፓፓያ፣ ሽፈራው፣ ካካዎ፣ ባሚያ፣ ጥጥ፣ ሊሻሊሾ፣ የአውጥ ወገን፣ ቡና፣ ወይራ፣ ጠንበለል፣ ሰሊጥ፣ በሶብላ ወዘተ.
ጅምር! ይህ አጭር ጽሑፍ መሠረት ወይም መዋቅር ነው። አሁን ሊያስፋፉት ይችላሉ! |