Jump to content

ድንት

ከውክፔዲያ
የ12:42, 22 ማርች 2020 ዕትም (ከMinorax (ውይይት | አስተዋጽኦ) ተዘጋጅቶ)
(ለውጡ) ← የፊተኛው እትም | «የአሁኑን እትም ለመመልከት» (ለውጡ) | የሚከተለው እትም → (ለውጡ)

ደ ዱ ዲ ዳ ዴ ድ ዶ ዷ



አቡጊዳ ታሪክ

ድንት (ወይም ድልት) በአቡጊዳ ተራ አራተኛው ፊደል ነው። እንዲሁም በከነዓንአራማያና በዕብራይስጥሶርያም ፊደሎች አራተኛው ፊደል «ዳሌት» ይባላል። በዓረብኛ ደግሞ ተመሳሳይ ፊደል «ዳል» ተብሎ በ«አብጃድ» ተራ 4ኛ ነው። (በዘመናዊ ተራ ግን 8ኛው ነው።) በግሪክም 4ኛው ፊደል «ዴልታ» ይባላል። በነዚህ ቋንቋዎች ሁሉ አጠራሩ «ድ» ነው።

አማርኛ ደግሞ «ጀ ጁ ጂ ጃ ጄ ጅ ጆ» ከ«ደ...» ትንሽ ተቀይሯል።

ተመሳሳይ ግብፃዊ ስዕል ቅድመ-ሴማዊ ሣባ ግዕዝ
O31


የድንት መነሻ ከቅድመ-ሴማዊ ጽሕፈት እንደ ሆነ ይታስባል። በዚህ ጽሕፈት ፊደሉ ወይም የደጅ ወይም የዓሣ ስዕል መስለ። ለደጅ ተመሳሳይ የግብጽ ሀይሮግሊፍ «ዐእ» ነበር።

ከነዓን አራማያ ዕብራይስጥ ሶርያ ዓረብኛ
ድንት ድንት ד ድንት


የከነዓን «ዳሌት» እንዲሁም ከዚህ ምልክት ተወስዶ በዚያ መንገድ የዕብራይስጥና የአራማያ «ዳሌት» የአረብኛም «ዳል» ወለደ። ከዚህ በላይ የግሪክ አልፋቤት «ደልታ» (Δ δ) አባት ሆነ፤ እሱም የላቲን አልፋቤት (D d) እና የቂርሎስ አልፋቤት (Д, д) ወላጅ ሆነ። ስለዚህ እነዚህ ሁሉ የ«ድንት» ሩቅ ዘመዶች ሊባሉ ይቻላል። በተጨማሪ የግዕዝ ቁጥር (አራት) ከግሪኩ Δ በመወሰዱ እሱም የ«ደ» ዘመድ ነው።