Jump to content

ሆይ

ከውክፔዲያ
የ21:39, 24 ዲሴምበር 2022 ዕትም (ከΕὐθυμένης (ውይይት | አስተዋጽኦ) ተዘጋጅቶ)
(ለውጡ) ← የፊተኛው እትም | «የአሁኑን እትም ለመመልከት» (ለውጡ) | የሚከተለው እትም → (ለውጡ)

ሀ ሁ ሂ ሃ ሄ ህ ሆ



አቡጊዳ ታሪክ

ሆይ (ወይም ሀውይ) በአቡጊዳ ተራ አምስተኛው ፊደል ነው። እንዲሁም በከነዓን፣ በአራማያ፣ በዕብራይስጥ እና በሶርያም ፊደሎች አምስተኛው ፊደል «ሄ» ይባላል።

ዓረብኛ ደግሞ ተመሳሳይ ፊደል «ሃእ» ተብሎ በ«አብጃድ» ተራ 5ኛ ነው። በግሪክ አምስተኛው ፊደል «ኧፕሲሎን» ይባላል። በነዚህ ቋንቋዎች አጠራሩ «ህ» (ተናባቢ) ሲሆን በግሪክ ግን አናባቢ («ኧ») ሆኗል።

በመጀመርያው (ግዕዝ) ቅርጽ (ሀ) በልሳነ ግዕዝ እንደ ሌሎቹ ፊደላት የ«ኸ» አናባቢ ድምጽ ሆነው ነበር፤ በአማርኛ ግን ድምጹ እንደ አራተኛው (ራብዕ) ቅርጽ (ሃ) አንድላይ ነው። ይህ ስህተት እየታረመ ነው።

በአማርኛ አጻጻፍ ብዙ ጊዜ ከሐውት (ሐ) ከኀርም (ኀ) እና ከኻፍ (ኸ) ጋራ ሊለዋውጥ ይችላል። ቀድሞ ግን ድምጾቻቸው የተለያዩ ነበሩ።

ተመሳሳይ ግብፃዊ ስዕል ቅድመ-ሴማዊ ሣባ ግዕዝ
A28


የሆይ መነሻ ከቅድመ-ሴማዊ ጽሕፈት እንደ ሆነ ይታስባል። በዚህ ጽሕፈት ፊደሉ የሚደሰት ሰው ስዕል መስለ። ለዚህም ተመሳሳይ የግብጽ ሀይሮግሊፍ ነበር፤ አጠራሩ ግን «ቀእ» ነበር። በግብፅ የሠሩት ሴማውያን ግን በቋንቋቸው «ሄ» ስላሉት፣ ይህ ስዕል «ህ» ሆኖ እንዲሰማ መጣ።

ከነዓን አራማያ ዕብራይስጥ ሶርያ ዓረብኛ
ሆይ ሆይ ה ሆይ هـ


የከነዓን «ሄ» እንዲሁም ከዚህ ምልክት ተወስዶ በዚያ መንገድ የዕብራይስጥና የአራማያ «ሄ» የአረብኛም «ሃእ» ወለደ። ከዚህ በላይ የግሪክ አልፋቤት «ኧፕሲሎን» (Ε ε) አባት ሆነ፤ እሱም የላቲን አልፋቤት (E e) እና የቂርሎስ አልፋቤት (Е е) ወላጅ ሆነ። ስለዚህ እነዚህ ሁሉ የ«ሆይ» ሩቅ ዘመዶች ሊባሉ ይቻላል። በተጨማሪ የግዕዝ ቁጥር (አምስት) ከግሪኩ ε በመወሰዱ እሱም የ«ሀ» ዘመድ ነው። የነዚህ ቁጥሮች ቅርጽ ከግሪክ ፊደላት ቢወስዱም እስከሚቻል ድረስ ቅርሶቻቸው እንደ ግዕዝ ፊደሎች እንዲመሳስሉ ተደረገ። ስለዚህ ቅርጹ ε የወሰደው መልክ በጥንታዊ ፊደል ጽሕፈት ለ«ሩ» የጠቀመ ቅርጽ ነበር።