ወደ
ውክፔዲያ እንኳን ደህና መጡ! ውክፔዲያ ማለት የተለያዩ አገር ሰዎች ተሰባስበው በ
ብዙ ቋንቋዎች የዓለምን ዕውቀት እየመዘገቡ እና እያነበቡ ያሉበት በጣም ታዋቂ ድረ-ገጽ ነው። ውክፔዲያ የጋራ ነው። ማንም ሰው በዚህ መዝገበ ዕውቀት ሊጽፍ ይችላል። እርስዎ ለውክፔዲያ አዲስ ከሆኑ እላይ
ለጀማሪዎች የሚለውን አፅቅ ይጫኑና እንዴት እንደሚሳተፉ ይማሩ።
እዚህ ውክፔዲያ ላይ ጽሑፍ ለማቅረብ፡
- ድፈሪ-- አዲስ ጽሑፍ ለመጀመር ወይንም ያለውን ጽሑፍ ለማስተካከል ምንጊዜም አትፍሪ። ጽሑፍሽ ያልተሟላ፣ ወይንም ያልተጠናቀቀ ቢመስልሽ አትጨነቂ። ጅምር ጽሑፍሽ በተፈለገው ጊዜ ሊስተካክል፣ ሊሻሻል እና ሊጠናቀቅ ይችላል።
- ተማሪ አስተምሪ-- በማንኛውም የዕውቀት ዘርፍ ለመሳተፍ ይቻላል። ተማሪዎች በጥናታቸው ጊዜ እሚያጠኑትን ትምህርት ተርጉመው በጥቂቱ ቢጽፉ ለጥናታቸው ይረዳቸዋል።
- ተርጉም-- ጽሑፍ ለማቅረብ የግዴታ ከባዶ መነሳት አያስፈልግም። ከእንግሊዝኛው ውክፔዲያ ወይም ከሌላ ቋንቋ ውክፔዲያም እየተረጎምክ ጽሑፍ ማቅረብ ትችላለህ።