በር:ቋንቋ

ከውክፔዲያ
ባቢሎን ግንብ
እንኳን ወደ ቋንቋ
ክፍል መጡ!!!

መግቢያ ሐተታ

አለም ቋንቋ ቤተሰቦች

ቋንቋ የድምጽ፣ የምልክት ወይም የምስል ቅንብር ሆኖ ለማሰብ ወይም የታሰበን ሃሳብ ለሌላ ለማስተላለፍ የሚረዳ መሳሪያ ነው። በአጭሩ ቋንቋ የምልክቶች ስርዓትና እኒህን ምልክቶች ለማቀናበር የሚያስፈልጉ ህጎች ጥንቅር ነው። ቋንቋወችን ለመፈረጅ እንዲሁም ለምክፈል የሚያስችሉ መስፈርቶችን ለማስቀመጥ ባለው ችግር ምክንያት በአሁኑ ሰዓት በርግጠኝነት ስንት ቋንቋ በዓለም ላይ እንዳለ ማወቅ አስቸጋሪ ነው። እንደ ተለያየ መስፈርት ግምት ከ3000 እስክ 7000 ቋንቋወች በአለም ላይ እንዳሉ ስምምነት አለ።

የሰው ልጅ ቋንቋ በተፈጥሮ የሚገኝ ሲሆን ህጻናት ቋንቋን በደመ ነፍስ ይማራሉ። በተፈጥሮ የሚገኙ የሰው ልጅ ቋንቋዎች ከድምጽና ከየሰውነት ክፍሎች ምልክት ይፈጠራሉ። በሺሆች የሚቆጠሩ የሰው ልጆች ቋንቋዎች ቢኖሩም የሁሉም የጋራ የሆኑ ቋሚ ጸባዮች አሏቸው። እኒህ ቋሚ ጸባዮች በሁሉም የተፈጥሮ ቋንቋውች ሠርጸው የሚገኙ እንጂ ላንዱ ሰርተው ላንዱ የማይሰሩ አይደሉም።

የአለም ቋንቋወች

ኢቲሞሎጂ

ልዩ ቋንቋወች - የቋንቋዎች ዝርዝር - የቋንቋ ቤተሰቦች

አፍሮ ኤዥያዊ

በርበር ቋንቋ - ግብጻዊ ቋንቋ - ሃማዊ ቋንቋ - ኦሞቲክ ቋንቋ - ሴማዊ ቋንቋ - ቻዳዊ ቋንቋ

ህንዶ አውሮጳዊ

ባልቲክ ቋንቋ - ጀርመናዊ ቋንቋ - ኢራናዊ ቋንቋ - ጣልያናዊ ቋንቋ - ሴልቲክ ቋንቋ - ሮማንስ ቋንቋ - ስላቭ ቋንቋ

ኒጀር ኮንጎ

አትላንቲክ ቋንቋ - ባንቱ ቋንቋ - ማንዴ ቋንቋ - ኮርዶፋን ቋንቋ

ሲኖ ቲቤታዊ

ቻይና ቋንቋ - ትቤቶ በርማዊ ቋንቋ

አውስትራሎ ኤዣያዊ

ድራድቪዲያን ቋንቋ - ፊኖ ኡግሪካዊ ቋንቋ - አሜርካዊህንዶች ቋንቋ - ኮዚያኒዛዊ ቋንቋ


የኢትዮጵያ ቋንቋዎች

ሴማዊ ቋንቋዎች ኩሻዊ ቋንቋዎች ኦሟዊ ቋንቋዎች ናይሎ ሰሀራዊ ቋንቋዎች ያልተመደቡ


የዕለቱ ምርጥ የኢትዮጵያ ቋንቋ ጽሑፍ

የአማርኛ ቋንቋ ጥናት


የእለቱ ምርጥ ስለ-አማርኛ ጽሑፍ

አማርኛ ፦ ሥርዓተ ነጥቦች


በወረቀት ላይ የሰፈረ ሐሳብ (ቋንቋ) መልእክቱ ግልጽ ሆኖ እንዲተላለፍ ሥርዓተ - ነጥቦች የጎላ ድርሻ አላቸው። በጽሑፍ ላይ ነጥቦችን አስተካክሎ ካለመጠቀም የተነሳ ዐረፍተ ነገሮችን ያሻማሉ፤ መልእክቶች ይዛባሉ፤ ሐሳቦች ይድበሰበሳሉ። ስለዚህ ሐሳቦችን ግልጽ በሆነ መልኩ በጽሑፍ ለማስተላለፍም ሆነ የተጻፈውን መልእክት በትክክል አንብቦ ለመረዳት ሥርዓተ - ነጥቦችን እና አገልግሎታቸውን በሚገባ ማወቅ ተገቢ ይሆናል።

ብዙዎቻችን ከሁለት ነጥብና ከአራት ነጥብ በስተቀር ሌሎቹን ሥርዓተ - ነጥቦች በሚገባ አንጠቀምም። ለምሣሌ አንዱ ድርብ ሠረዝ (፤) የሚጠቀምበትን ቦታ ሌላው ነጠላ ሠረዝ (፣)/(፥) ይጠቀማል፤ እንዲሁም አንዱ ትእምርተ - ጥያቄ (?) የሚጠቀምበትን ቦታ ሌላው ትእምርተ - አንቅሮን ይጠቀማል። ወጥ የሆነ የአጠቃቀም ስርዓት አይታይም። በርግጥ አንዳንዴ ድርብ ሠረዝን መጠቀም አለመጠቀም የምርጫ ጉዳይ ሊሆን ይችላል። ሐሳቦች ተደራርበው ወይም ተጣምረው እንዲቀርቡ የፈለገ ሰው ድርብ ሠረዝን ተጠቅሞ ሐሳቦቹን በአንድ ዐረፍተ ነገር ሊያጠቃልል ይችላል። በአንጻሩ ደግሞ ሐሳቦቹን ቆራርጦ የተለያዩ ዐረፍተ ነገሮች በማድረግ ለየብቻቸው ሊያቀርብ የፈለገ ሰው አራት ነጥብን መጠቀም ይችላል። ዞሮ ዞሮ የሥርዓተ - ነጥቦችን አጠቃቀም ማወቅ ተገቢ ነው።

በአሁኑ ጊዜ በአማርኛ ቋንቋ ውስጥ በማገልገል ላይ የሚገኙት ሥርዓተ - ነጥቦች የሚከተሉት ናቸው።

አንድ ነጥብ (.)

አንድ ነጥብ (.) በግእዝ ነቁጥ ይባላላል። በአማርኛ ደግሞ <<ይዘት>> ተብሎ የሚጠራ ሲሆን በሦስት የተለየ መልክ ያገለግላል።

  • ቃላትን በምህፃረ - ቃል አሳጥሮ ለመጻፍ የሚያገለግል ሲሆን ሁለት የተለያዩ ሥርዓቶችን ይከተላል።

ሀ. የቃላትን መነሻ ፊደል ብቻ በመውሰድ ምሳሌ፡ ተ. መ. ድ. = የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት

ለ. የአንድን ቃል መነሻና መድረሻ ሆሄ ብቻ በመውሰድ ምሳሌ፡ ወር. = ወታደር


ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ


የዕለቱ ምርጥ የቋንቋ ጽሑፍ



Purge server cache