በር:ኅብረተሰብ

ከውክፔዲያ
Jump to navigation Jump to search

ሥነ ሕብረተሰብ

ሥነ ሕብረተሰብ የሰው ልጆች በቡድንና በተናጥል ያላቸውን ጠባይና አደረጃጀት የሚያጠና ክፍል ነው።

Mozilla.svg
የዕለቱ ምርጥ ጽሑፍ

የሕገ መንግሥት ታሪክ


ሱመር ከተማ ላጋሽ አለቃ ኡሩካጊና በ2093 ዓክልበ. ያሕል ዓመታት ያዋጀ ሕገ ፍትሕ በታሪካዊ መዝገብ እስከምናውቀው ድረስ መጀመርያ የሕገ መንግሥት ሰነድ ነው። ሰነዱ እራሱ ገና አልተገኘም፤ ነገር ግን ለዜጎቹ አንዳንድ መብት እንደ ፈቀደላቸው ይታወቃል። ለምሳሌ ለመበለትና ለደሀ አደጎች ቀረጥ እንዳስቀረላቸው ድሆችንም ከሃብታሞች አራጣ እንደጠበቃቸው ይታወቃል።

ከዚህ በኋላ ብዙ መንግሥታት በተጻፈ ሕግ እንዲገዙ ልዩ ስርዓት ነበራቸው። ከተገኙት ሕግጋት ሁሉ ጥንታዊ የሆነው በ1983 ዓክልበ. የገዙ የኡር ንጉሥ የኡር-ናሙ ሕግጋት ነው። በተለይ ዕውቅ የሆኑ የጥንት መንግሥት ሕጎች የኢሲን ንጉሥ ሊፒት-እሽታር ሕግጋት (1832 ዓክልበ.) ፤ የባቢሎን ንጉሥ ሃሙራቢ ሕግጋት (1704 ዓክልበ.)፤ የኬጢያውያን ሕግጋት፤ የአሦር ሕግጋትና፤ ሕገ ሙሴእስራኤል (ምናልባት 1655 ዓክልበ.) ናቸው። ....

Gnome-fs-blockdev.svg
የዕለቱ ምርጥ ምስል
ኒው ዮርክ ከተማ፣ አሜሪካ በምሽት
Icon-Rechtshinweis-blau2-Asio.svg
የዕለቱ ምርጥ የሕግ ጽሑፍ

ህግ ተርጓሚ


ህግ ተርጓሚ ወይም ፍርድ ቤት፡ ፍርድ የመስጠት ስልጣን ያለው የመንግስት አካል ነው። ከሶስቱ ከፍተኛ የመንግስት አካላት ማለትም ህግ አውጭህግ ተርጓሚ እና ህግ አስፈጻሚ አንዱ ነው። ይህ አካል ህግ ተርጓሚ የሚባለው ነው። የወንጀለኛ መቅጫ ህግ፣ ሲቪል ህግአስተዳደራዊ ህግ እና ሌሎች ህጎችን በ የህግ የበላይነት ላይ መሰረት በማድረግ ይተረጉማል።

ታሪክ[ኮድ አርም]

ፍርድ በኢትዮጵያ የረጅም ጊዜ ታሪክ ያለው ክንውን ነው። ኢትዮጵያ ውስጥ በተለምዶ ወይም ባህልበላ ልበልሃ እየታገዘ በመንደር ሽማግሌዎች ወይም በሀገረ ገዥዎች ፊት ይቀርብ ነበር። ከቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ አገዛዝ ወዲህ በዘመናዊው የመንግስት መዋቅር የህግ ተርጓሚነትን የመንግስት ሰልጣን ተሰጥቶት መንግስት በሾማቸው ዳኞች ይመራል።

ገለልተኝነት[ኮድ አርም]

ይህ አካል በዘመናዊዉ የዴሞክራሲ መርህ ከየትኞቹም የመንግስት አካላት በገለልተኝነት ይንቀሳቀሳል። ሶስቱም የመንግስት አካላት ጣልቃ መግባት አይችሉም። በሃገሪቱ የሚገን ማንኛውም ዜጋ፣ አካል፣ ወይንም ተቋም ይዳኝበታል።

A coloured voting box.svg
የዕለቱ ምርጥ የፖለቲካ ጽሑፍ

የኅሊና ነፃነት


የኅሊና ነፃነት ማለት ማንኛውም ግለሠብ ምንምን ሀሣብ፣ እምነት ወይም አስተያየት በጽናት ለመያዝ የሚረጋገጥበት ነጻነት ነው። የሌላ ሰዎች እምነት ምንም ቢሆንም፣ ይህ ነጻነት ለየግለሠቡ ጽኑእ ሆኖ ይቆጠራል።

መግለጫ[ኮድ አርም]

ኅሊና ነጻነት ለሰዎች ለመከልከል ቢሞከር ኖሮ ይህ የሰው ልጆች መሠረታዊ መብት (ሰው ለራሱ ለማሰብ) እንደ መከልከል ይቆጠራል።

የኅሊና ነጻነት ፍሬ ነገር እያንዳንዱ ግለሠብ ለራሱ የቱን እምነት ለመምረጥ ስለሚሰጥ፣ 'የሃይማኖት ነጻነት' ጽንሰ ሐሳብ ከዚህ ጋር ተያይዟል። በአንዳንድ ህብረተሠብ ወይም መንግሥት በተግባር የሃይማኖት ነጻነት ወይም የእምነት ነጻነት ባይከበርም፣ በሌሎች ህብረተሠብ ወይም ሕገ መንግሥታት ግን በተለይ በምእራቡ አለም ይህ ነጻነት በታሪክ እጅግ ተከብሯል። ለምሳሌ በአሜሪካ ሕገ መንግሥት 1ኛ ማሻሻያ አንቀጽ መሠረት ሃይማኖት ወይም ንግግር የሚከለክል ሕግ እንደማይጸና ይረጋገጣል። ዛሬ በአለም ዙሪያ ደግሞ አብዛኛው ሕገ መንግሥታት የእምነት ነጻነት የሚያረጋግጡ ናቸው። በ1948 ዓ.ም. በኢትዮጵያ የወጣ ሕገ መንግሥት አንቀጽ 40 አባባል እንዲህ ነው፦

«የሕዝቡን መልካም ጠባይ ወይም ፀጥታን ወይም በፖለቲካ ረገድ የሚያውክ ካልሆነ በቀር በንጉሠ ነገሥቱ መንግሥት ግዛት የሚኖሩ ሰዎች በሕግ መሠረት የሃይማኖታቸውን ሥርዓት አክብረው በነፃ ከመፈጸም አይከለከሉም።»

«የሰብዓዊ መብት አቀፋዊ መግለጽ» አንቀጽ ፲፰ ደግሞ እንደሚለው፣

«እያንዳንዱ ሰው፡ የሃሳብ የሕሊናና የሃይማኖት ነጻነት መብት አለው። ይህም መብት ሃይማኖቱን ወይም እምነቱን የመለወጥ ነጻነትንና ብቻውን ወይም ከሌሎች ጋር በኀብረት በይፋ ወይም በግል ሆኖ ሃይማኖቱን ወይም እምነቱን የማስተማር፣ በተግባር የመግለጽ የማምለክና የማክበር ነጻነትን ይጨምራል።»

እንዲሁም በአንቀጽ ፲፱ ዘንድ፣

«እያንዳንዱ ሰው የሐሳብና ሐሳቡን የመግለጽ መብት አለው። ይህም መብት ያለጣልቃ ገብነት በሐሳብ የመጽናትንና ዜናን ወይም ሐሳቦችን ያላንዳች የድንበር ገደብ የማግኘትን የመቀበልን ወይም የማካፈልን ነጻነትም ይጨምራል።» .....
Business-commerce.svg
የዕለቱ የኢኮኖሚ ምርጥ ጽሑፍ

ገንዘብ

ሳንቲም እና ብር – በብዛት በስራ ላይ በተጨባጩ አለም ውስጥ የተሰማሩ የገንዘብ አይነቶች ናቸው። ገንዘብ ከነዚህ ውጭ ሊሆን ይቻላል።

በአንድ አገር ወይም ማህበረሰብ ውስጥ ለሸቀጥ (አሰፈላጊ እቃ) ና አገልግሎት መግዢያ እንዲሁም እዳ መክፈያ የሚያገለግ ማንኛውም ነገር ሁሉ ገንዘብ ይባላል።

የጥንቱ ገንዘብ ዋጋ ይመነጭ የነበረው ከራሱ ከተሰራበት እቃ ዋጋ ነበር (ለምሳሌ፡ ከወርቅ የተሰራ ሳንቲም) ። በዚህ ምክንያት እንዲህ አይነቱ ገንዘብ የኮሞዲቲ ገንዘብ ይባላል። በአሁኑ በአለማችን የሚሰራባቸው ገንዘቦች በራሳቸው የራሳቸው የሆነ ዋጋ የላቸውም (ለምሳሌ ከተልባ እግር የተሰራው ዶላር በራሱ ዋጋ የለውም) ። ይህ አይነት ገንዘብ ፊያት ገንዘብ ሲባል ዋጋው የሚመነጨው የአንድ አገር መንግስት ህጋዊ መገበባያ ብሎ ስላወጀው ብቻ ነው። ህጋዊ መገበባያ ሲባል ለማንኛውም በዚያ አገር ውስጥ ላለ እዳ ይህ የታወጀው ገንዘብ እንደ ክፍያ ሲቀርብ "አይ! አልቀበልም" ማለት ክልክል ነው። በዚህ ምክንይት የፊያት ገንዘብ ዋጋ ከመንግስት ሃይል ጋር ከፍተኛ ግንኙነት አለው።

ያንድ ዘመናዊ ሃገር የገንዘብ አቅርቦት በሁለት ይከፈላል፣ ይኸውም ተጨባጭ የሆነው የታተመው ብርና በማይጨበጥ መልኩ በባንክ ቤት ተጠራቅሞ ያለው በቼኪንግ እና ሴቪንግ የሚከፈለው የባንክ ሒሳብ ነው። ባብዛኛው ጊዜ እኒህ የ ባንክ ሒሳቦች ታትሞ ከቀረበው ብር በላይ ናቸው። በምናባዊ አለም ውስጥ የተቀመጡት እነዚህ የቁጥር ሰነዶች ምንም እንኳ የማይታዩና የማይዳሰሱ ቢሆንም ልክ እንደ ጥሬ ብር እኩል ለመሸጥና ለመለወጥ ያገለግላሉ። ...

Le-Temps-p1030243.jpgCopenhagen Metro escalators.jpgChicago 2007-5.jpgMarx Engels Lenin.svgMystethoscope.jpgEP Strasbourg hemicycle l-gal.jpgQWERTY keyboard.jpgParis 75005 Quai de Montebello Bouquinistes 20071014.jpgHK Starbucks Coffee in Caine Road.jpg1,5 und 10 Dollarnoten.jpgKonkretismus (DSC04014).jpgChess bishop 1000.jpgSan Francisco International Airport at night.jpgNYCSub 7 car exterior.jpgMontinari Milano.jpgKings Cross Station Platforms, London - Sept 2007.jpg
  መደቦች
A coloured voting box.svg
ፓለቲካ


  ተጨማሪ

ሕዝባዊ ጉዳዮች

ሕግ ሥነ ንዋይ (ኢኮኖሚክስ) የሰው ልጅ ጥናት

የባሕል ጥናት (ሶሲዮሎጂ) ትምህርት ሃይማኖት የመጻሕፍት ቤትና የመረጃ ጥናት