መስከረም ፴
Appearance
(ከመስከረም 30 የተዛወረ)
በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የመጀመሪያ ወር መደምደሚያ እና የዓመቱ ፴ኛው ዕለት ሲሆን፣ የመፀው ወቅት ፭ኛው ቀን ነው። ከዚህ ዕለት በኋላ እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ፣ በዘመነ ሉቃስ ፫፻፴፮ ዕለታት ሲቀሩ፤ በዘመነ ዮሐንስ ፣ ዘመነ ማቴዎስ እና ዘመነ ማርቆስ ደግሞ ፫፻፴፭ ዕለታት ይቀራሉ።
- ፮፻፸፫ ዓ/ም የቀሊፋ ቀዳማዊ ያዚድ ወታደሮች በካርባላ ጦርነት ላይ የነቢዩ ሞሐመድን የልጅ ልጅ የአሊ ልጅ ሁሴንን አንገቱን በመቁረጥ ሰውት። ሺአቶች ዕለቱን በሐዘን ያስቡታል፡፡
- ፲፰፻፷ ዓ/ም - ዓፄ ቴዎድሮስ ርዕሰ ከተማቸው ያደረጓትን ደብረ ታቦር ካቃጠሉ በኋላ አውሮፓውያን ሠራተኞቻቸውን እና ሠራዊታቸውን አስከትለው ጉዟቸውን ወደ መቅደላ ምሽግ ጀመሩ።
- ፲፱፻፶ ዓ/ም የጋናው የገንዘብ ሚኒስትር ኮምላ አግቤሊ ግብዴማ፣ በዘረኛነት ጥላቻ ምክንያት በዴላዌር ምግብ ቤት መስተንግዶ በመነፈጋቸው፣ የአሜሪካው ፕሬዚደንት ድዋይት አይዘንሃወር ይቅርታ ጠየቋቸው።
- ፲፱፻፸፫ ዓ/ም ሁለት ትላልቅ የመሬት እንቅጥቅጥ ነውጦች ኤል አስናም በምትባለዋ የሰሜናዊ አልጄሪያ ከተማ ላይ የ፳ ሺህ ሰዎችን ነፍስ ጥፋትና የብዙ ሺህ ሰዎችን የአካል ጉዳት አስከተሉ።
- ፲፱፻፺፰ አገራቸውን ዩጋንዳ፣ መጀመሪያ ወደነጻነትና በጄኔራል ኢዲ አሚን መፈንቅለ መንግሥት እስከወደቁ ጊዜ ድረስ በቀዳማዊ ሚንስትርነት፤ ከአሚን ውድቀት በኋላ ለሁለተኛ ጊዜ በመፈንቅለ መንግሥት እስከተሰደዱ ድረስ ያገለገሉት አፖሎ ሚልተን ኦቦቴ ጆሃንስበርግ ላይ አረፉ::
- (እንግሊዝኛ) http://news.bbc.co.uk/onthisday/hi/dates/stories/october/10/ Archived ሜይ 1, 2023 at the Wayback Machine
- (እንግሊዝኛ)Markham, Clements R., A History of the Abyssinian Expedition, London Macmillan and Co. (1869)
- (እንግሊዝኛ) http://www.answers.com/topic/milton-obote
የኢትዮጵያ ወራት | |
---|---|
መስከረም - ጥቅምት - ኅዳር - ታኅሣሥ - ጥር - የካቲት - መጋቢት - ሚያዝያ - ግንቦት - ሰኔ - ሐምሌ - ነሐሴ - ጳጉሜ |