አባል:Abdissa Aga/ዋናው ገጽ

ከውክፔዲያ
Jump to navigation Jump to search

Problem with displaying Amharic characters?

You might want to start from the font section.

Hide (link)

በኮምፒውተርዎ ላይ በአማርኛ በቀላሉ ለማቀነባበር...

እባክዎ የመረዳጃ ገጹን ይመለከቱ።

3colors.jpg

ወደ ዊኪፔድያ እንኳን ደኅና መጡ!

ዊኪፔድያ የተሟላ፣ ትክክለኛ እና፡ ነጻ መዝገበ ዕውቀትን በብዙ ቋንቋዎች ለማቅረብ የሚጥር የትብብር ሥራ ውጤት ነው። ይህ የአማርኛው ዊኪፔዲያ ጥር 18 ቀን 1996 ዓመተ ምኅረት (27 January 2004 እ.ኤ.አ.) የተጀመረ ሲሆን 14,851ጽሑፎች አካቶ ይዟል።

ይህን መዝገበ እውቀት የተሟላ ለማድረግ አሁን ካሉት መጣጥፎች በብዙ ዕጥፍ የሚበልጡ ጽሑፎች ያስፈልጉናል። የፕሮጀክቱ ጀማሪዎች እና አንቀሳቃሾች ፕሮጀክቱን በመምራት ብቻ ሳይሆን በተለያዩ ርእሶች መጣጥፍ በማዘጋጀትም ጭምር እየተሳተፉ ነው። እባክዎን እርስዎም በአማርኛ መጻፍ ከቻሉ፣ በሚፈልጉት ርዕሰ-ጉዳይ ዙሪያ ጽሑፎችን በማቅረብ ለዚህ ፕሮጀክት መሳካት አስተዋጽኦ ያድርጉ። ይህ ሥራ ወደፊት በጣም ትልቅና ጠቃሚ የዕውቀት ምንጭ እንደሚሆን ተስፋ አለን።

ዊኪፔድያ የጋራ ነው። ማንኛውም ሰው ለዚህ መዝገበ ዕውቀት ተዋጽዖ ሊያደርግ ይችላል። ጽሑፍ ለማቅረብ ወይም በአርትዖት ሥራ ለመሳተፍ ዘዴው በጣም ቀላል ነው። ጽሑፍ ለማቅረብም ሆነ የጽሑፍን ስሕተት፣ የፊደል ግድፈት (ታይፖ)፣ ወዘተ. ለማስተካከል፤ ወይም የጽሑፍ ማከያ ለማቅረብ ማድረግ ያለብዎት በዚያው ገጽ የኅዳግ ጥግ ያለውን "ይህን ገጽ ለማዘጋጀት" የሚለውን መጫን ብቻ ነው።

በቀይ ቀለም የሚታዩ ቃላት ገና ያልተጻፉ አርእስትን ይጠቍማሉ። በእነዚህም ሆነ በሌሎች ርእሶች ላይ መጣጥፍ ለማቅረብ ይችላሉ። ሥራዎ ያልተጠናቀቀ መስሎ ቢሰማዎ እምብዛም አይጨነቁ፤ አንዳችን የሌላችንን ስራ(ጽሑፍ) በማረም በጋራ በጣም ጠቃሚ መጣጥፎችን ማበርከት እንችላለን።

በተጨማሪ የእርዳታ ገጽ ላይ የቀረበውን ማስታወሻ አንብበው ማንኛዉንም ጽሑፍ ለማቅረብ ከአሁን ጀምሮ ይሞክሩ። ሙከራ ለማድረግ ቢፈልጉ፣ በማንኛውም ጊዜ ወደ መፈተኛው ቦታ መሻገር ይችላሉ።

የተሳትፎዎትን መጀመርያ መጣጥፍ ከከእንግሊዝኛው ዊኪፔድያ በመተርጐም ማቅረብ ይቀልዎት ይሆናል። እጅግ ብዙ ትርጕም መጣጥፎች ቢኖሩን ለአማርኛው ዊኪፒዲያ ማደግ መልካም መንገድ ይጠርጋሉ።

ዛሬ ሰኞ፣ [[ውክፔዲያ:የቀን መለወጫ/21 ኦክቶበር]] ቀን 1998 ዓመተ ምኅረት ነው።
የዛሬ ቀን (እንደ አውሮጳውያን አቆጣጠር) 21 ኦክቶበር, 2019 ነዉ።
ስለ ምን ለማወቅ ይፈልጉ ነበር? አሣብዎን በዚህ ያቅርቡ።
ቀልዶችን ያውቃሉ? እዚህ ላይ ይጨምሩ!


ምርጥ ፅሑፎች
page=1


የሾላ ዛፍ

በለስ (ሮማይስጥFicus) ቅጠሉ ሰፋፊ፣ ነጭ ፈሳሽ ያለው፣ ፍሬው የሚበላ የእፅዋት አስተኔ ነው። ፍሬውም ደግሞ በለስ ወይም ዕጸ በለስ ይባላል። በበለሱ ቤተሠብ ውስጥ ብዙ ልዩ ልዩ የዛፍ አይነቶች አሉ፤ ከነዚህም ውስጥ፦

  • ተራ በለስ F. carica ከጥንት ጀምሮ ስለ ፍሬው በእርሻ ወይም በጓሮ ተተክሏል። ፍሬውም ለጤንነት እጅግ መልካም ነው።
  • የቆላ በለስ F. palmata
  • ሾላ F sycomorus -
  • ዋርካ (ወይም ወርካ) F. vasta - በብዙ ቅርንጫፎች በጣም ትልቅ የሆነ የበለስ አይነት ነው። ፍሬው ከሾላ ፍሬ ያንሳል። ይህ ፍሬ ከበሰለና ከደረቀ በኋላ ይበላል።
  • የጎማ ዛፍ F. elastica
  • የቊልቋል በለስ (Opuntia) እውነተኛ በለስ ሳይሆን እንዲያውም ቊልቋል ነው። ሆኖም ፍሬውን ስለሚመስል ብዙ ጊዜ ይህም ተክል 'በለስ' ይባላል።

የበለስ 'ፍሬ' በዕውኑ ወደ ውስጥ ያበበ አበባ ነው። ይህ ክስተት ለሥነ ሕይወት ጥናት በጣም የሚያስገርም ድንቅ ነው። እነኚህ አበቦች የወንዴ ዘር የሚያገኙበት ዘዴ በልዩ ብናኝ አርካቢ ጥቃቅን ተርብ አማካኝነት ነው። ይህች የበለስ ተርብ ወደ ፍሬው ውስጥ ገብታ በመኖር እንቁላሏን በዚያ ትጥላለች። አለበለዚያ አብዛኞቹ በለስ አይነቶች ብናኝ ዘርን ሊያገኙ አይችሉም። ተርቢቱ ዕንቁላሏን ጥላ በበለሱ ውስጥ ከሞተች በኋላ፣ በፍሬው ያለው ኤንዛይም በድኑን ፈጽሞ ይበላል። የዛፉ ጾታ አንስት ከሆነ፣ የተርቢቱ እንቁላል አይፈለፈለም፣ ፍሬውም በሰው ይበላል። የዛፉ ጾታ ግን ፍናፍንት ሲሆን፣ ዕንቁላሎቿ ይፈለፈላሉ፤ ፍሬው ለፍየል ሊሰጥ ይችላል እንጂ በሰዎች አይበላም። ተርቦች ከፍናፍንት ዛፍ ተወልደው ሴት ተርቦቹ የሴት ዛፍ እንዲያገኙ ገበሬው የፍናፍንት ዛፍ ቅጠል ከአንስት ዛፍ ቅርንጫፍ ይሰቅላል። አንዳንድ የበለስ አይነት ያለ ተርብ ያፈራል፤ ነገር ግን የነዚህ ፍሬዎች መካን ይሆናሉ። ዳሩ ግን በለሶች በእፃዊ ተዋልዶ ለማብዛት በተለይ ስለሚመቹ፣ ይህ ዘዴ የተለመደና ፈጣን የመራቦ ዘዴ ነው።

እስልምና፣ በሕንዱ፣ በቡድሂስትና በጃይን እምነቶች፣ በለሶች የተቀደሱ ዛፎች ሆነው ይቆጠራሉ። በክርስትናም በአይሁድም በኩል በለስ ወይም ሾላ በብሉይ ኪዳን ብዙ ጊዜ ይጠቀሳል። ለምሳሌ በአንዳንድ ሥፍራ በትንቢት፣ በእግዚአብሔር መንግሥት ሰው ሁሉ በራሱ ወይንና በለስ ሥር እንደሚቀመጥ ይላል። በተጨማሪ በኦሪት ዘፍጥረት 3፡7 ዘንድ አዳምሕይዋን ከበለስ ቅጠል ልብስ ሠሩላቸው። ከዚህ የተነሣ በተለይ በተዋሕዶ ቤ.ክ. የበለስ ፍሬ ወይም እፀ-በለስ እግዚአብሔር እንዳትበሉት ብሎ ያዘዛቸው ፍሬ መሆኑን በመገመት ይታመናል። ሆኖም በሌላ አስተሳስብ የተከለከለው ፍሬ መታወቂያ ወይን ወይም ቱፋህ ነበር። መታወቂያው በመጽሐፉ እርግጠኛ ስላልሆነ፣ በእርግጥ በለስ ማለቱ ነበር ልንል አንችልም። በአዲስ ኪዳን ውስጥ ደግሞ በለስ በክርስቶስ ምሳሌዎች ብዙ ጊዜ ይጠቀሳል፤ በማርቆስ ወንጌል ምዕራፍ 11 መሠረት ኢየሱስም አንዲቱን በለስ ረግሞ ነበር።


ታሪክ በዛሬው ዕለት (ኦክቶበር 21, 2019 እ.ኤ.አ.)

ጥቅምት ፲፩

Hernando de Magallanes del museo Madrid.jpg
Bikila in Tokyo 1964.jpg
  • ፲፱፻፶፯ ዓ/ም - የሮማ ኦሊምፒክ የማራቶን ድል አድራጊው አበበ ቢቂላቶክዮ ውድድር የራሱን የኦሊምፒክ ክብረ ወሰን በመስበር በ2 ሰዓት 12 ደቂቃ 11.2 ሰከንድ አዲስ የዓለም ክብረ ወሰን ድልን ተቀዳጀ። ከዚህ ድል ከሰላሳ ስድስት ቀናት በፊት ትርፍ አንጀቱን በቀዶ ሕክምና አስወግዶ ስለነበረ፣ ድሉን ለሁለተኛ ጊዜ ብቻ ሳይሆን ሳያገግም በአዲስ ክብረ ወሰን ማሸነፉ በማራቶን ውድድር እስካሁን ድረስ አቻ የለሽ ጀግና አድርጎ አስመስክሮለታል።


መዝገበ ዕውቀት
Socrates blue version2.png
ፍልስፍና
P physics.svg
ሳይንስ
ኢትዮጵያ
ኢትዮጵያ
ሒሳብ
ሒሳብ
P Society.png
ኅብረተ -ሰብ
P windturbine.png
ምህንድስና
P history clock.png
ታሪክ
P countries.png
መልክዐ ምድር
P vip.svg
ቋንቋ
P Food.png
ኑሮዘዴና ዕደጥበብ
P culture.svg
ባሕልና ኪነት
P lion of judah blank.svg
ባሕልዊ ዕውቀቶች
P Economy.png
ንግድና ኢኮኖሚ
የዊኪ ኅብረተሰብ

መጣጥፎችን፡ ስለ መጻፍ
ሰላምታ ለአዲስ ገቢዎች! / Welcome newcomers - መመሪያዎችና ልምዶች - የማብዛት ፈቃድ - የማዘጋጀት ዘዴ - ቀላል መማርያ - አጻጻፍ መምሪያ - የምርምር ምንጮች - የተፈለጉ ፅሑፎች - አንጸባራቂ ንባቦች - ምክር ይጠይቁ - ዕቅዶች

ስለ ውክፔዲያ ዕቅድ በጠቅላላው
ስለ ውክፔዲያ ሶፍትዌር - ሜታ Wikimedia Meta - ዐዋጆች - ተራ ጥያቄዎች - የዝርዝር ቁጥሮች - ደብዳቤ ይጻፉልን - ምንጭጌ (ስለዚሁ ሥራ አገባብ ለማወራት) - ውክፔዲያን በየቋንቋው - ጭውውት - ጠቃሚ ዕርዳታዎች - የውክፔዲያ ወዳጆች - የጋዜጦች መጠቃለያ


ጎን ለጎን

ዊኪፔድያ በየቋንቋው "የሥራ እኅቶች"

(1 - የሌላ ቋንቋ ቀበሌኛ፣ 2 - ሰው ሠራሽ ቋንቋ፣)

ውክፔዲያ በአፍሪካ ልሣናት (ከ10 መጣጥፍ በላይ ያላቸው)፦

Bamanankan (ባምባርኛ) · Fulfulde (ፉላኒ) · هَوُسَ (ሃውሳ) · Igbo (ኢግቦ) · kiKongo (ኮንጎኛ) · Malagasy (መለጋሲ) · linNgála (ሊንጋላ) · kiNyarwanda (ኪንያርዋንዳ) · kiRundi (ኪሩንዲ) · chiShona (ሾና) · Soomaaliga (ሶማልኛ) · seSotho (ሶጦ) · kiSwahili (ስዋሂልኛ) · seTswana (ጽዋና) · chiTumbuka (ቱምቡክኛ) · Twi (ትዊ) · Wolof (ዎሎፍኛ) · isiXhosa (ቆሣ) · Yorùbá (ዮሩብኛ) · isiZulu (ዙሉኛ)


የሙሉ ቋንቋዎች ዝርዝር---የብዙ ቋንቋ መተባበር---አዲስ ውክፔዲያን ለመጀመር

ነጻ መጽሐፈ ዕውቀት የሆነው የዊኪፔድያ አስተናጋጅ Wikimedia Foundation ነው። ይህ ለማትረፍ ያልሆነ ድርጅት አያሌ ልዩ ልዩ ባለ ብዙ ቋንቋ እና ሥራ እቅዶች ያካሂዳል፦
Wiktionary

መዝገበ ቃላት

Wikibooks

ነፃ መጻሕፍት

Wikiquote

ጥቅሶች ስብስብ

Wikisource

ነፃ የደራሲ ስራዎች

Wikispecies

የፍጡሮች ማውጫ

Wikinews Wikinews

ወቅታዊ ዜናዎች

Commons
የጋራ ሚዲያ ማስቀመጫ
Meta-Wiki

ውኪሜድያ ጠቅላላ ዕቅዱ የጋራ መተባበር