ጥር ፳፭
Appearance
ጥር ፳፭፣ በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የዓመቱ ፻፵፭ ኛው ዕለት ሲሆን፤ የበጋ ወቅት ፴ኛው ቀን ነው። ከዚህ ዕለት በኋላ እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ በዘመነ ሉቃስ ፪፻፳፩ ዕለታት ሲቀሩ በዘመነ ዮሐንስ፣ ዘመነ ማቴዎስ እና ዘመነ ማርቆስ ደግሞ ፪፻፳ ቀናት ይቀራሉ።
- ፲፱፻፶፪ ዓ/ም - የብሪታንያው ጠቅላይ ሚኒስትር በደቡብ አፍሪካ ከተማ፣ ኬፕ ታውን ላይ ‘የለውጥ ነፋስ’ (Wind of Change) በመባል የሚታወቀውን ንግግር አደረጉ። ይህ ታሪካዊ ንግግር የብሪታንያን የቅኝ ገዥነት የታሪክ ምዕራፍ መዘጊያነቱን ያበሠረ ንግግር ነበር።
- ፲፱፻፹፪ ዓ/ም የአፓርታይዳዊዋ ደቡብ አፍሪቃ ፕሬዚደንት ደ ክለርክ ለሠላሳ ዓመታት በሕግ ተከልክሎ የነበረውን የአፍሪቃ ብሔራዊ ምክር ቡድን (African National Congress) ሕጋዊ መሆኑንና በወቅቱ በእሥራት ላይ የነበሩትን ኔልሰን ማንዴላ እንደሚፈቱ አስታወቁ።
- ፲፰፻፹፰ ዓ/ም - ወረሂመኑ ተንታ ላይ ልጅ ኢያሱ ከአባታቸው ከራስ ሚካኤል (በኋላ ንጉሥ) እና ከእናታቸው ከወይዘሮ ሸዋረጋ ምኒልክ (የዳግማዊ ምኒልክ ልጅ) ተወለዱ።[1]
የኢትዮጵያ ወራት | |
---|---|
መስከረም - ጥቅምት - ኅዳር - ታኅሣሥ - ጥር - የካቲት - መጋቢት - ሚያዝያ - ግንቦት - ሰኔ - ሐምሌ - ነሐሴ - ጳጉሜ |