ነሐሴ ፱
Appearance
ነሐሴ ፱ ቀን በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የዓመቱ ፫፻፴፱ ኛው ቀን ሲሆን የክረምት ወቅት ፵፬ኛው ቀን ነው። ከዚህ ዕለት በኋላ እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ፣ በ ዘመነ ሉቃስ ፳፯ ቀናት ሲቀሩ፣ በዘመነ ዮሐንስ፤ በ ዘመነ ማቴዎስ፤ እና በ ዘመነ ማርቆስ ደግሞ ፳፮ ቀናት ይቀራሉ።
- ፲፱፻፮ ዓ/ም - የአትላንቲክ ውቅያኖስንና ሰላማዊ ውቅያኖስ ለማገናኘት የተቆፈረው የፓናማ ቦይ ሥራው ተጠናቆ አገልግሎት መስጠት ጀመረ።
- ፲፱፻፴፯ ዓ/ም - ጃፓን በቃል ኪዳን አገሮች ተሸንፋ እጇን ስትሰጥ የሁለተኛው የዓለም ጦርነት ፍጻሜ ሆነ። በዚህ ዕለት ኮሪያም ነጻ ወጣች።
- ፲፱፻፴፱ ዓ/ም - ለ፫ መቶ ፴፬ ዓመታት በብሪታኒያንጉዛት ሥር በቅኝ ግዛትነት የኖረችው ሕንድ በዚህ ዕለት ነጻነቷን ተቀዳጀች። እስላማዊው የሰሜን-ምዕራብ አካልም በዚሁ ዕለት ተገንጥሎ ፓኪስታን በሚል ስም አዲስ አገር ተፈጠረ።
- ፲፱፻፶፪ ዓ/ም - ለሰማንያ ዓመታት በፈረንሳይ ሥር በቅኝ ግዛትነት ይተዳደር የነበረው ኮንጎ ሪፑብሊክ በዚህ ዕለት ነጻነቱን ተቀዳጀ። ፊልበርት ዩሉ የአገሪቱ የመጀመሪያው ፕሬዚደንት ሆኑ።
- {{en]] P.R.O., FCO 371/1829 - ANNUAL REVIEW FOR ETHIOPIA FOR 1974
- {{en]] http://en.wikipedia.org/wiki/August_15
የኢትዮጵያ ወራት | |
---|---|
መስከረም - ጥቅምት - ኅዳር - ታኅሣሥ - ጥር - የካቲት - መጋቢት - ሚያዝያ - ግንቦት - ሰኔ - ሐምሌ - ነሐሴ - ጳጉሜ |