Jump to content

ሰይንት ቪንሰንትና ዘ ግረነዲንዝ

ከውክፔዲያ

ሰይንት ቪንሰንትና ዘ ግረነዲንዝ
Saint Vincent and the Grenadines

የሰይንት ቪንሰንትና ዘ ግረነዲንዝ ሰንደቅ ዓላማ የሰይንት ቪንሰንትና ዘ ግረነዲንዝ አርማ
ሰንደቅ ዓላማ አርማ
ብሔራዊ መዝሙር "Saint Vincent, Land so beautiful"
የሰይንት ቪንሰንትና ዘ ግረነዲንዝመገኛ
የሰይንት ቪንሰንትና ዘ ግረነዲንዝመገኛ
ዋና ከተማ ኪንግስታውን
ብሔራዊ ቋንቋዎች እንግሊዝኛ
መንግሥት
{{{
ንግሥት
አገረ ገዥ
ጠቅላይ ሚኒስትር
 
ንግሥት ኤልሣቤጥ
ፍሬድሪክ ባለንታይን
ራልፍ ጎንሳልቨስ
የመሬት ስፋት
አጠቃላይ (ካሬ ኪ.ሜ.)
 
389 (184ኛ)
የሕዝብ ብዛት
የ2012 እ.ኤ.አ. ግምት
 
109,991 (181ኛ)
ገንዘብ የምሥራቅ ካሪቢያን ዶላር
ሰዓት ክልል UTC −4
የስልክ መግቢያ +1 784
ከፍተኛ ደረጃ ዶሜን .vc

ሰይንት ቪንሰንትና ዘ ግረነዲንዝካሪቢያን ባህር ደሴት አገር ሲሆን ዋና ከተማው ኪንግስታውን ነው። ሰይንት ቪንሰንት ዋናው ትልቁ ደሴት ነው።

ብሪቲሽ ኮመንዌልዝ አባል ሲሆን ከንግሥት ኤልሣቤጥ ግዛቶች አንዱ ነው። የሀገሩ ዋና ምርት ሙዝ ነው፣ እንዲሁም የቱሪዝም መድረሻ ነው። የአገር ሥራ ቋንቋ እንግሊዝኛ ቢሆንም የሕዝብ መነጋገሪያ የቪንሰንት ክሬዮል ነው።

በአገሩ ታሪክ፣ እስከ 1711 ዓም ድረስ የደሴቶች ኗሪዎች የካሪቦች ብሔር አውሮጳውያን እንዳይሠፍሩባቸው ከለከሉ። በቋንቋቸው ሰይንት ቪንሰንትን «ዮውሎውማይን» ይሉት ነበር። በመርከብ አደጋ ምክንያት ግን ከባርነት ያመለጡ አፍሪካውያን በደሴቶቹ ደርሰው ከካሪቦቹ ጋር ተቀላቀሉ። እነርሱም የጋሪፉና ብሔር ተብለው በኋላ (1789 ዓም) ወደ ሆንዱራስቤሊዝ አካባቢ በመካከለኛ አሜሪካ ጠፈፍ ተሰደዱ። የፈረንሳይ ሰዎች በ1711 ዓም ሠፈሩበት፣ ዩናይትድ ኪንግደም በጦርነት በ1746 ዓም ያዘው፣ እንደገና ከ1771 እስከ 1775 ዓም ድረስ ወደ ፈረንሳይ ተመለሰ፤ ከዚያም ጀምሮ የዩናይትድ ኪንግደም ቅኝ ግዛት ሆኖ እስከ 1971 ዓም ድረስ ቆይቶ ነበር።