Jump to content

ሥላሴ

ከውክፔዲያ
(ከትምህርተ ሥላሴ የተዛወረ)
አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ
በአካል ሦስት በመለኮት አንድ
ሥሉስ ቅዱስ
አነዋወር የነበሩ ያሉ ለሁልጊዜ የሚኖሩ ፣ በአካል ሦስት ሲሆኑ በመለኮት በባሕርዪ አንድ የሆነ አምላክ
ለቀዳማዊነቱ መጀመሪያ የሌለው ለደኃራዊነቱ መጨረሻ የሌለው አምላክ
ወይም ትናንት የሌለበት ቀዳማዊ ዛሬ የሌለበት ማዕከላዊ ነገ የሌለበት ደኃራዊ አምላክ
፩ኛ ዋና የአምላክ ትዕዛዝ ለሰው ልጅ አምላክህን በሙሉ ልብህ በሙሉ ሀሳብህ በሙሉ ሰውነትህ በሙሉ ስሜትህ ውደድ
፪ኛ ዋና የአምላክ ትዕዛዝ ለሰው ልጅ ሌላውን ሰው እንደ ራስህ ውደድ
የመጀመሪያ ክስተት ፩ኛ የንግሥ በዓል ሐምሌ ፯
ሥላሴ በአብርሃም ቤት ሲስተናገዱ
፪ኛው ዓመታዊ የንግሥ በዓል ጥር ፯


ሥላሴ ማለት ሠለሰ ከሚል ቃል የመጣ ሲሆን ሦስትነት ማለት ነው፣ ቃሉም ግእዝ ነው። ይህ ቃል አምላክ አንድነትና ሦስትነትን ያመለክታል። የሥላሴ እምነት የክርስትና ሃይማኖቶች ተከታይ አንዷ ከሆነችው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ዋነኛ መሰረተ ትምህርት ነው።

ትምህርቱ በዐቢይ አብያተ ክርስቲያናት ሁሉ (ተዋሕዶምሥራቅ ኦርቶዶክስካቶሊክፕሮቴስታንት) ዘንድ ተቀባይ ሲሆን ማለትም በእንግሊዘኛ ሞኖቴዪዝም (Monotheism= በአንድ አምላክ ማመን) ይባላል፣ የሥላሴን አንድነት ያልተረዱ ወይም መረዳት የማይፈልጉ ፖሊቴዪዝም (በብዙ አምላክ ማመን= Polytheism) ብለው ይሰይሙታል ፣ ደግሞ ከማያስተምሩት ክፍልፋዮች መካከል አሪያኒስምየይሖዋ ምስክሮች፣ እና ሞርሞኒስም ተገኝተዋል።

ከድረ ገፃቸው አንዱን ለማየት እዚህላይ ይጫኑ

ትምህርተ ሥላሴ እንደሚለን፣ እግዚአብሔር ፈጣሪ አንድላይ በሦስት ቦታዎች ሊኖር ይችላል። ፩) በመሢሕ ይኖራል (ወልድ)፤ ፪) በልባችን ይኖራል (መንፈስ ቅዱስ)፤ ፫) በማይታይ ሰማያት የትም ቦታ ይኖራል (አብ)። በአትናቴዎስ ሃይማኖታዊ ድንጋጌ መሰረት ሁሉም ዘላለማዊ የሆኑ፣ እያንዳንዳቸው ሁሉን ማድረግ የሚችሉ፣ አንዳቸው ከአንዳቸው የማይበላለጡ፣ ሁሉም አምላክ የሆኑ ሦስት መለኮታዊ አካላት (አብ፣ ወልድ፣ መንፈስ ቅዱስ) አሉ። ይሁን እንጂ ሦስቱም አንድ አምላክ ናቸው እንጂ ሦስት አማልክት አይደሉም። ስለዚህ ቀኖና የተሰጡ ሌሎች መግለጫዎች እንደሚያመለክቱት እነዚህ ሦስት "አካላት" መለኮታዊው ህልውና የሚገለጥባቸው ሦስት መንገዶች ናቸው እንጂ የተለያዩና ግላዊ ሕልውና ያላቸው "አካላት" አይደሉም። በዚህም ምክንያት አንዳንድ የሥላሴ አማኞች ኢየሱስ እግዚአብሔር እንደሆነ ወይም ኢየሱስና መንፈስ ቅዱስ ይሖዋ እንደሆኑ አጥብቀው ያምናሉ። አምላክ አንድ ሲሆን ሶስት ሶስት ሲሆን አንድ ማለት ነው፤ በስም፣ በአካል እና በግብር ሶስት ሲሆን በህላዌ እና በመለኮት አንድ ነው።

ክርስቶስ ከመወለዱ በፊት የሥላሴ ሦሥትነትና አንድነት በብሉይ ኪዳን ብዙ ቦታ ተጽፎ ይገኛል። ነገር ግን በዛን ወቅት የነበሩ ነብያትም ሆኑ አስተማሪዎች ነገሩ አልተገለፀላቸውም ነበር። በግልፅ በመጻሕፍ ቅዱስ ውስጥ ከሚነበቡት፦

  • አዳምን በአምሳላችን እንፍጠር ፣
  • አዳም እንደኛ አንዱ ሆነ ፣
  • ሰናዖርን ሰዎች ቋንቋ በመለያየታቸው ፣
  • አብርሃም ቤት በመስተናገዳቸው
  • ዳዊት በመዝሙር [1]ብሎ በጻፈው…

ክርስቶስ ከመጣ በኋላ ግን የተሸፈነው ሁሉ ተገልጾ በተግባር አንድም ሦሥትም መሆናቸውን ኢየሱስ አሳወቀም አስተማረም

ጌታችን መድኃኒታችን እየሱስ ክርስቶስ ከዐረገ በኋላም፦

ሐዋ.ሥ.-ም፡፯ ቁ፡፶፭-፶፮ ላይ እንደተጻፈው[4]

እነዚህ ከብዙዎቹ ጥቂጦቹ ሲሆኑ በይበልጥ ለመረዳት ይህን ይጫኑ: ሰይፈ ሥላሴ ወይም እዚህ ይጫኑ

ደግሞ ይዩ፦

የሥላሴ እምነት ምንጭ

[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

የሥላሴ እምነት ደጋፊዎች በተለይ ማቴ. ፳፰፡፲፱ ያጠቁማሉ። ሆኖም ተቀራኒ ድምጾች እንደሚሉ ይህ ጥቅስ በኋላ ነበር ወደ ወንጌሉ የተጨመረው። ከዚህም ሁሉ በላይ የሥላሴ ትምህርት የሚቀበሉት አብያተ ክርስትያናት ፪ ቆሮንቶስ ፲፫፡፲፬ እና ፩ ቆሮንቶስ ፲፪፡፬-፮ ሲያመለከቱ፣ ይህ እምነት ከመጀመርያ ደቀ መዛሙርት ጀምሮ እንደ ተመሠረተ ለማስረዳት ይጣራሉ።

ዳሩ ግን ሌሎች መምህሮች ለነዚህ ነጥቦች ትልቅ ስፍራ አይሠጡም። በእንግሊዝኛ የተጻፈው ዘ ኒው ኢንሳይክሎፔድያ ብሪታኒካ እንዲህ ይላል፦ «ሥላሴ የሚለው ቃልም ሆነ በግልጽ የተብራራ የሥላሴ መሰረተ ትምህርት በአዲስ ኪዳን ውስጥ አይገኝም። ኢየሱስም ሆነ ተከታዮቹ በብሉይ ኪዳን ውስጥ የተጻፈውን፦ 'እስራኤል ሆይ ስማ፣ አምላካችን እግዚአብሔር አንድ እግዚአብሔር ነው' (ዘዳግም ፮፡፬) የሚለውን ለማስተባበል አላሰቡም። . . . የሥላሴ እምነት ቀስ በቀስ የተስፋፋው በበርካታ መቶ ዓመታት ውስጥ ከብዙ ንትርክ በኋላ ነው። . . . የሥላሴ መሰረተ ትምህርት አሁን ያለውን ቅርጽ የያዘው በአራተኛው መቶ ዘመን መጨረሻ ላይ ነው።» [5]

ሚስጥረ ሥላሴ

[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

የምሥጢረ ሥላሴን ትምህርት በምንማርበት ጊዜ ከሂሳብ ቀመር ህግ አስተሳሰብ ውጭ ሆነን ነው ። ይህን የምንልበት ሥላሴ አንድም ሦስትም ሦስትም አንድም ናቸው ስንል የሃይማኖት አባቶች በሒሳብ ቀመር ፩ ፫ እንዳልሆነ ፫ ፩ እንዳልሆነ ጠፍቶባቸው አይደለም ስሌቱ መንፈሳዊ ይዘት ስላለው ነው። ሌላው ምክንያት መንፈሳዊዉ ሥጋዊዉን ጥበብ ይመረምረዋል እንጅ መንፈሳዊ ጥበብና ምሥጢር በዓለማዊ ዕውቀት ምርምር ሊደረስበት አይቻልምና ። እግዚአብሔር በጥሩ መንፈስ፣ በቅን ልቦና፣ ፈሪሐ እግዚአብሔር ባለው ፍለጋ ከፈለጉት ለማንኛውም ሰው ፈላስፋም ይሁን ገበሬ ይገለፃል። እሱን ለመቃረን ፍለጋ ከተነሱ ግን ወደ ዋና አውሬ መሄጃውን መንገድ ያስይዛል ምክኒያቱም ሌላ ምንም ምርጫ ስለሌለ እንደተጻፈው "በተመኙት ላይ ጨምሮ ይሰጣል"።

እነዚህ ፭ አዕማደ ሚሥጥራት ሰለ ሥላሴ ቁልጭ ያለ አመለካከት እንዲኖረን ያደርጋሉ ፣ እንዲየውም ማንኛውም የተዋህዶ ኦርቶዶክስ ተከታይ ሚሥጥሮቹን ሁሉ ማወቅ ይጠበቅበታል።


  1. ^ "ጌታ ጌታዬን ጠላትህን የእግርህ መረገጫ እስካደርግልህ በቀኜ ተቀመጥ"
  2. ^ "በአባቴ ቤት መኖር እንዳለብኝ አታውቁምን"
  3. ^ መንፈስ ቅዱስ በነጭ እርግብ ተመስሎ በላዩላይ በመቀመጡ ፣ የእግዚአብሔርም አብ ቃል "ይህ የምወደው የምወልደው ልጄ ነው እሱ የሚላችሁን በሙሉ ስሙት"
  4. ^ መንፈስ፡ቅዱስንም፡ተሞልቶ፡ወደ፡ሰማይ፡ትኵር፡ብሎ፡ሲመለከት፡የእግዚአብሔርን፡ክብር፡ኢየሱስንም፡ በእግዚአብሔር፡ቀኝ፡ቆሞ፡አየና፦ እንሆ፥ሰማያት፡ተከፍተው፡የሰው፡ልጅም፡በእግዚአብሔር፡ቀኝ፡ቆሞ፡አያለኹ፡አለ።
  5. ^ ዘ ኒው ኢንሳይክሎፔድያ ብሪታኒካ (1976)፣ ማክሮፔድያ፣ ጥራዝ 10፣ ገጽ 126