ኅዳር ፰
Appearance
(ከኅዳር 8 የተዛወረ)
ኅዳር ፰ ቀን በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የዓመቱ ፷፰ተኛው እና የመፀው ወቅት ፵፫ኛው ቀን ነው። ከዚህ ዕለት በኋላ እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ፣ በ ዘመነ ሉቃስ ፪፻፺፰ ቀናት በ ዘመነ ዮሐንስ፤ በ ዘመነ ማቴዎስ፤ እና በ ዘመነ ማርቆስ ደግሞ ፪፻፺፯ ቀናት ይቀራሉ።
- ፲፭፻፶፩ ዓ.ም. - በእንግሊዝ ቀዳማዊት ንግሥት ማርያም ስትሞት እህቷ ቀዳማዊት ኤልሳቤጥ አልጋውን ወርሳ ዘውድ ጫነች።
- ፲፰፻፵፰ ዓ.ም. - ዴቪድ ሊቪንግስተን በዛሬዎቹ ዛምቢያና ዚምባብዌ ላይ የሚገኘውን ታላቅ ፏፏቴ በማየት የመጀመሪያው አውሮፓዊ ሆነ። ይሄንኑም ፏፏቴ ለንግሥቱ ክብር የቪክቶሪያ ፏፏቴ ብሎ ሰየመው።
- ፲፰፻፷፪ ዓ.ም. - የሜዲተራንያ ባሕርንና ቀይ ባሕርን ያገናኘው የሱዌዝ ቦይ በደመቀና በታላቅ ሥነ ስርዐት ተመረቀ።
- ፲፱፻፶፯ ዓ/ም - ፲፩ ነጥብ ፬ ‘ሜጋዋት’ የሚያመነጨው የጢስ እሳት መብራት ኃይል ማመንጫ በዚህ ዕለት ተመርቆ ሥራ ላይ ዋለ።
- ፲፱፻፷፩ ዓ/ም - የሶቪዬት ኅብረት፣ አሰብ ላይ በዓመት ፭፻ ሺ ቶን የድፍድፍ ነዳጅ ማጣሪያ ለመገንባት የሚያስችለውን ውል ከኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት መንግሥት ጋር ተፈራረመ።
- ፲፱፻፷፯ ዓ/ም - ሻለቃ መንግሥቱ ኃይለ ማርያም (በኋላ ኮሎኔል) የኢትዮጵያ ጊዜያዊ ወታደራዊ መንግሥት (ደርግ) አንደኛ ምክትል ሊቀ መንበር ስማቸው ለመጀመሪያ ጊዜ ይፋ ተደረገ።
- ፲፱፻፺ ዓ.ም. - በግብጽ ስድስት አመጸኛ አክራሪዎች በሉክሶር ጥንታዊውን የ”ሀትሼፕሱት መቅደስ” ለመጎብኘት የመጡ ሠላሳ ስምንት የስዊስ፤ አሥር የጃፓን ፤ ስድስት የብሪታንያ እንዲሁም አራት የጀርመን ዜጎችን ረሽነው ገደሏቸው።
- ፲፱፻፺፮ ዓ.ም.- የአውስትሪያው ተወላጅና የፊልም ተዋናይ አርኖልድ ሽቫርትዘኔገር የካሊፎርኒያ ሠላሳ ስምንተኛው ገዥ በመሆን መሀላውን ሰጥቶ ስልጣኑን ተቀበለ።
- (እንግሊዝኛ) P.R.O., FCO 31/165300 Ethiopia: Annual Review of 1961
- (እንግሊዝኛ) http://www.myviplife.com/lifestories/vipbusiness/Soichiro_Honda_bi.php?c=3 Archived ኦክቶበር 15, 2011 at the Wayback Machine
የኢትዮጵያ ወራት | |
---|---|
መስከረም - ጥቅምት - ኅዳር - ታኅሣሥ - ጥር - የካቲት - መጋቢት - ሚያዝያ - ግንቦት - ሰኔ - ሐምሌ - ነሐሴ - ጳጉሜ |